የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትላንትናው ዕለት ሐምሌ 10, 2011 ዓ.ም በአንድ ቀን ብቻ 310 በረራዎችን በማድረግ 29 ሺህ 528 መንገደኞችን በማጓጓዝ አዲስ ክብረ ወሰን ማሻሻሉን ገለጸ።
አየር መንገዱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው አዳዲስ ዓለም አቀፍ ተሳፋሪዎች በአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በኩል መጓጓዝ ጀምረዋል።
የቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ አደራ የአየር ማረፊያውን አቅም ከሁለት እጥፍ በላይ የሚጨምረው አዲሱ ተርሚናል በከፊል መከፈቱን ገልፀዋል።
በዚህ የክረምት ወቅት ብዛት ያላቸው ተሳፋሪዎችን ማጓጓዝ በመቻላችን በጣም ደስተኞች ነን ብለዋል።
አየር መንገዱ በቅርቡ ባደረገው ማስፋፊያ በአመት 22 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረ ነው የተገለፀው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ70 አመታት ታሪኩ በአፍሪካ በፍጥነት እያደገ የመጣ አየር መንገድ ለመሆን በቅቷል።
©ፋና
Leave a Reply