ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን … [Read more...] about ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!
News
ዜና
“መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች "መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ" እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ ክፍል እንዳሰሯቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ አሁንም መረጃየን ሰብስቤ አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ 8 ቀናት ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ተጠርጣዎቹ በማዕከላዊ እየደረሰባቸው የሚገኘውን ሰቆቃ አስመልክተው ለፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የቀረበበትን አቤቱታ እንዲያስተካክል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በጎንደርና … [Read more...] about “መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”
ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞ አጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡ ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡ በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራው የደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ … [Read more...] about ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት
* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!! የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል። የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል። የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና … [Read more...] about የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት
በአርሲ ጅብ በሰውና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ
በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በሌሙና- ቢልቢሎ ወረዳ ሌሊት ላይ መኖሪያ ቤት የገባ አንድ ጅብ በሰውና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ጎሳ አማን እንደገለጹት፥ ጅቡ በሰውና እንስሳት ላይ ጥቃት ያደረሰው በሌሙዲማና ሁላሃሳ የገጠር ቀበሌ ነው። የካቲት 10 ቀን 2007 ከሌሊቱ 10 እስከ 11 ሰዓት በሁለት አርሶ አደሮች የእንስሳት በረትና መኖሪያ ግቢ በመግባት በሁለት አባወራና ስምንት የቤት እንስሳት ላይ ንክሻ መፈጸሙን ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የቤት እንስሳቱን ከጅቡ ለማስጣል በገጠሙት ግብ ግብ የተደናገጠው ጅብ ወደ ጭላሎ ተራራ ሊያመልጥ መቻሉን አስታውቀዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል አንደኛው ብልታቸው ላይ ሌላው አርሶ አደር ደግሞ በሆዳቸውና ሌላ አካላቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት አሰላ … [Read more...] about በአርሲ ጅብ በሰውና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ
በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ
ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት ዲፕሎማቶች ምንም ዓይነት መረጃ የላቸውም፡፡ አደጋው የደረሰባት ወጣት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኗን የሚናገሩ የዜናው አቀባዮች ወጣቷ እንደተራራ የገዘፈውን ህይወት በመጋፈጥ ቤተስቦቿን ከችግር ለመታደግ በወቅቱ ከነበሩ የኤጀንሲ ደላላዎች ጋር ተዋውላ ሳውዲ አረቢያ ለስራ መምጣቷን ይናገራሉ። በተጠቀሰው ውል መስረት ወጣቷ አሰሪዋ የወር ደሞዝዋን በየወቅቱ እንዲከፍላት ለማስረዳት ብትሞክረም ከኢትዮጵያ ከመጣች ጀምሮ ላለፉት ሁለት አመት ያለደሞዝ ለመቆየት መገደዷን ለመረዳት ተችሏል። ሰሞኑን ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ … [Read more...] about በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ
አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
ኢህአዴግ በ“አሸባሪነት” የከሰሳቸውና ከየመን ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ቅዳሜ በኦስሎ ኖርዌይ ተከብሯል፡፡ በሥፍራው የተገኘው ዳንኤል አለባቸው ለጎልጉል በኢሜይል በላከው መረጃና ፎቶ እንደገለጸው ዝግጅቱ የተደረገው እዚያው ኖርዌይ በሚገኝ “የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት” ነበር፡፡ በበዓሉ ወቅት የአቶ አንዳርጋቸውን ህይወት ታሪክና የትግል ዓመታት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ፎቶ (ስላይድ) የቀረበ ሲሆን ከኬክ መቁረሱ ሥነስርዓት በተጨማሪ ግጥምና የልደት መዝሙር ለበዓሉ ማድመቂያነት ቀርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ … [Read more...] about አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
“ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም የካቲት 3/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉን የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሰልፉ ወቅትም ነዋሪዎቹ መንግስት ለአካበቢው ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ 10 ከተሞች ላይ መብራት በራሳቸው ገንዘብ ማስገባታቸውን፣ ትምህርት ቤቶችን ራሳቸው እንደሰሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን የተዘረጋው በህዝቡ ወጭ መሆኑን፣ መንግስት ሰራሁት ያለው ውሃ ከሶስት ሳምንት በኋላ መበላሸቱ ሙስና እንደተበላበትና እንዳልተሰራ እንደሚያምኑ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰልፈኞቹ "ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል፣ ስራ አጥተው … [Read more...] about “ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!
* ኢንቨስተሮች “የደም ከፈን” ላለመግዛት ወሰኑ በኦሞ ሸለቆ ድሆችን ከመሬታቸው በማባረር የሚያመርተውን ጥጥ ወደ ውጭ ለመላክ ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢህአዴግ ባለፈው ሰሞን ያልጠበቀው ምላሽ ደርሶታል፡፡ ምላሹን ተከትሎ የጥጥ ግብይቱ የጨነገፈው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መሆኑን በገሃድ አመነ፡፡ በኢህአዴግ ስትራቴጂክ በሆኑ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድሞ የመልስ ምት በመምታት ፈተናው ውስጥ የከተታቸው አኢጋን እና መሪው ኦባንግ ሜቶ መዋቅራቸው ሊገኝ አለመቻሉ ኢህዴግን እንዳስጨነቀው ተሰማ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በሰማሁት ተዝናንቻለሁ ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አሜሪካ መከተል የሚገባትን አካሄድ በመዘርዘር ለፕሬዚዳንት ኦባማ ፖሊሲ ሊያስቀይር የሚችል ደብዳቤ ልከዋል፡፡ ኢህአዴግ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ በቦታቸው ላይ ጥጥ … [Read more...] about ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!
አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ
የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ … [Read more...] about አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ