በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ የፖለቲካ አካሄድ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያመጣል የተባለው የሰሞኑ ምርጫ ውጤት ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት የመንፈስ ልዕልና አጎናጽፏቸዋል፡፡ በበርካታ ችግሮች ለተወጠረችው ናይጄሪያ “ብሩህ ጊዜ” ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን በምክትልነት ናይጄሪያን እያገለገሉ በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዑማሩ ሙሳ ሕይወታቸው በማለፉ ወዲያው የፕሬዚዳንትነት መንበሩን ተረከቡ፡፡ ዑማሩ ሙሳን ተክተው ጥቂት እንዳገለገሉ በወቅቱ በተካሄደ ምርጫ ሙሐማዱ ቡሃሪን አሸንፈው ናይጄሪያን ለአምስት ዓመታት መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የዛሬ አምስት ዓመት ባሸነፏቸው መልሰው ተሸንፈው ሥልጣናቸውን በሰላም አስረክበው በናይጄሪያ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ተግባር በመፈጸም ስማቸውን ከመቃብር በላይ ህያው አድርገዋል - ፕሬዚዳንት ጉድላክ … [Read more...] about መጪው ጊዜ ለናይጄሪያ “ብሩህ” ይሆናል!!
News
ዜና
ሰማያዊ ቀን!
የሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መጋቢት 20 ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡ በትዕይንቱ የወጣው ሕዝብ ነጻነት እንደሚፈልግ፤ ስቃይ፣ አፈናና ስደት እንደበቃው ባሰማው መፈክር አሰምቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ ከፎቶዎች ጋር በማጀብ ከሰልፉ ዝግጅት ጀምሮ በየሰዓቱ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በጅማ፣ በአዲስ አበባ፣ በሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በጭሮ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልቂጤና ሌሎችም ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ እንደተለመደው የኢህአዴግ ፖሊስ ሰልፉን በማጨናገፍ፣ ተሰላፊው ሰልፉን ጀምሮ ለማብቃት የወሰነበት ቦታ እንዳይደርስ በመከላከል ድርጅታዊና ወገናዊ ሥራውን አከናውኗል፡፡ በየከተማው በተካሄደው ትዕይንተ ሕዝብ ሰልፈኞቹ የሚከተሉትን መፈክሮች አሰምተው እንደ ነበር ከዜናው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል፡ ነፃነት እንፈልጋለን፣ ነፃነት፣ … [Read more...] about ሰማያዊ ቀን!
“የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ። የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው። አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች … [Read more...] about “የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
ኦነግ ሲከተል የነበረው መንገድ ስህተት እንደነበር በይፋ በመናገር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የተሰኘውን አዲስ ድርጅትና ወኪሎች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት አቶ ሌንጮ ለታ ተቀባይ በማጣታቸው ወደመጡበት የተመለሱት ኦህዴድ ባቀረበው ተቃውሞ መሆኑ ታወቀ። የኢህአዴግ አፈ ቀላጤ የስላቅ መልስ ሰጡ። ኦዴግ (ኦዲኤፍ) በ2012 ምርጫ ሊጋበዝ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታል። የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በመነጠል ከኢትዮጵያ (“አቢሲኒያ አገዛዝ”) መገንጠልን አማራጭ አድርጎ ለግማሽ ምዕተ አመት ሲወድቅ ሲነሳ የኖረውን ኦነግ ሲመሩ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ተቃውሞ ደርሶባቸው ነበር። የቀድሞው የትግል ጉዞ ስህተት እንደነበር በይፋ አስታውቀው ለድርድር ኢህአዴግ ደጅ የዘለቁት አቶ ሌንጮ ከጉዟቸው በፊት የተነሳባቸውን ተቃውሞ … [Read more...] about ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
“ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ስልት ነው”
• የሶዶ ፖሊስ 8 የሰማያዊ ዕጩዎችን በማሰር ቅስቀሳውን አስተጓጉሏል • የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተዘርፏል ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ "የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም" ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት "ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ" … [Read more...] about “ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ስልት ነው”
“ስሉሱ” ዞረ እንዴ?!
ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግ ላይ ታዋቂ የዓለማችን ጋዜጦች የጀመሩት ተከታታይ ትችት፣ ማሳሰቢያና መፍትሔ ጠቋሚ ዘገባዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነዋል፡፡ ሚዲያዎቹ በዘገባቸው ኢህአዴግን ከቻይና አምባገነናዊና አክራሪ አገዛዝ ጋር አመሳስለዋል፡፡ ኢህአዴግ እከተለዋለሁ የሚለውን የኢኮኖሚ መርህ ከቻይና የተኮረጀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ሆነ መድረሻው ግራ የሚያጋባና የማይታወቅ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ጋዜጦቹ ኢህአዴግን በሚንከባከቡት መንግሥቶቻቸው እና በራሱ ኢህአዴግ ላይ የሰላ ሒስ መሰዘንዘር መጀመራቸው የፖሊሲ አውጭዎችን አስተሳሰብ የሚያስቀይር ከመሆን አልፎ ኢህአዴግ ላይ “ስሉሱ” ዞሯል የሚያስብል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ … [Read more...] about “ስሉሱ” ዞረ እንዴ?!
“ችሎት ደፍራችኋል” ተደፋሪው “ፍርድ ቤት”
"ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው" የሺዋስ አሰፋ "ችሎት ደፍራችኋል ካላችሁ ቅጣቱን ጨምሩብንና ሸኙን" ዳንኤል ሺበሽ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ተላለፈባቸው፣ ተጨማሪ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እንዲሁም የዓረና ትግራይ ፓርቲዎች አመራሮች "ችሎት በመድፈር ወንጀል" ጥፋተኛ በመባላቸው መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በሦስቱ አመራሮች ላይ እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡ የካቲት 26/2007 ዓ.ም ተከሳሾች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸውና ንብረትም እንደተወሰደባቸው በመግለጽ አቅርበውት ለነበረው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ … [Read more...] about “ችሎት ደፍራችኋል” ተደፋሪው “ፍርድ ቤት”
“ባንዲራ ጨርቅ አይደለም” የኢህአዴግ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን – ኢብኮ
• የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለአራተኛ ጊዜ በሚዲያ እንዳይተላለፍ ተከለከለ • ኢብኮ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት "አላስተላልፍም" ብሎ መልሷል • "ኢብኮ ከገዥው ፓርቲ ጋር ወግኗል" አቶ ዮናታን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት "አላስተላልፍም" ብሎ መመለሱን ዛሬ የካቲት 29/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኢብኮ በደብዳቤው "የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልዕክታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው ሰንደቅ አላማ ምስል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክልና ህገ መንግስቱን…. የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል" በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል "ይህ የኢብኮ ተግባር የሰማያዊን ፕሮግራም ላለማስተላለፍ … [Read more...] about “ባንዲራ ጨርቅ አይደለም” የኢህአዴግ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን – ኢብኮ
ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
ሰማያዊ ፓርቲ "ኢህአዴግ" የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹'ግንባር' ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው በላከው ደብዳቤ "በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ 52 አገራት ኢትዮጵያ 32ኛ!
* የናሚቢያው ፕሬዚዳንት የሞ ኢብራሂም ሽልማትን አሸነፉ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ በሚያወጣው የአፍሪካ መልካም አስተዳደር ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ52 አገሮች 32ኛ ወጣች፡፡ እ.ኤ.አ. የ2014 የሞ ኢብራሂም የመልካም አስተዳደር ጠቋሚ ከ30 ገለልተኛ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ታማኝ ምንጮች የተገኙ ከመቶ በላይ መለኪያዎችን በመገምገም ነው የአገሮች የመልካም አስተዳደር ደረጃን ማውጣቱን የገለጸው፡፡ ዋነኛ መለኪያዎቹ አራት ምሰሶዎች መሆናቸውን የሚገልጸው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፣ እነዚህም ሕዝቦች ከመንግሥታቸው የሚጠብቋቸውና መንግሥትም ማቅረብ የሚጠበቅበት ግዴታዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ምሰሶዎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የመናገር ነፃነት፣ የንፅህናና የንብረት ባለቤትነት መብቶች ጥበቃን የሚዳስሱ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ሞሪሺየስ፣ ኬፕ ቨርዴና ቦትስዋና ከአንድ እስከ … [Read more...] about በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ 52 አገራት ኢትዮጵያ 32ኛ!