በሊቢያ ታፍነው የነበሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል ነጻ አውጪነት መለቀቃቸውን የግብጽ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ ኢህአዴግ እንደተለመደው “የተለቀቁት ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አጣራለሁ” እንደማይል ተገምቷል፡፡ “ተይዘን የነበረው በሊቢያ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ነበር” ከተለቀቁት አንዱ ኢትዮጵያዊ፡፡ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሐሙስ በተሰራጨው የዜና መረጃ መሠረት በሊቢያ ደርና እና ምስራታ በተባሉ ከተሞች ታፍነው የነበሩ 30 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል እና በሊቢያ ድጋፍ ነጻ መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡ ዜናውን ከካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ የግብጽ የዜና አውታሮች በቀጥታ ለአገራቸውና ለዓለም ሕዝብ እንዲሰራጭ አድርገውታል፡፡ … [Read more...] about ምርጫው አዲስ “ጠቅላይ ሚ/ር” አግኝቷል
News
ዜና
አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው
በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡ አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡ የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት በላይ አስቆጥራለች። ሟቹ አቶ መለስ የቆሰቆሱት የሶማሊያ ችግር እስካሁን አልበረደም፤ የኢትዮጵያን ጦር ጨምሮ ከተለያዩ አፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ ወታደሮች የሶማሊያን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር እያደረጉ ያለው ጥረት መና ቀርቶ የእሳቱ ወላፈን ድንበር ተሻግሮ ለዜጎቻቸው ጦስ እስከ መሆን ርቆ የሄደበት አጋጣሚ የሰላም … [Read more...] about አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው
ሽብርን በማሸበር!!
* ሕዝብ ዋስትናና መተማመን አጥቷል ረቡዕ ዕለት ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ዜጎች ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ የተሰጣቸው ምላሽ ሽብርን በአሸባሪነት አመጣጥኖ የመመለስ አይነት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አጠቃላይ ገጽታና የሕዝብ ስሜት በአገሪቱ የዋስትና ማጣት ስሜት እየገዘፈ መሄዱን የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሊታረድ ነው፤ በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉት ይልቃል ላይ እዚያው እንዲቀሩ ተጽዕኖ ይደረጋል ተብሏል፡፡ በአይሲስ የታረዱትና የተረሸኑትን “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራሁ ነኝ” ሲል የነበረው ኢህአዴግ እንዴት እንዳጣራ ለሕዝብ ባያሳውቅም ወዲያው ሕዝባዊ ለመሆን በመመኘት በአገሪቷ ላይ የሐዘን ቀን ከማወጅ በተጨማሪ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ አንድ የጎልጉል አስተያየት ሰጪ “ሕዝቡ ለ24 ዓመታት በሐዘን ላይ ነው ሦስት ቀንማ … [Read more...] about ሽብርን በማሸበር!!
ቀላጤ ሬድዋን – ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸው” ይጣራልን!
አፈቀላጤ ሬድዋን “ጥቂት” በማለት የጠሯቸው ነገር ግን በዓለምአቀፍ ሚዲያ በብዙ ሺህ ተብሎ የተዘገበው የተቃውሞ ትዕይንት ከቪዲዮ ምስሎች ላይ ያውጣጣነው ፎቶ በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ቀላጤ ሬድዋን 7ፖሊሶች መደብደባቸውን ሲናገሩ ፖሊሶቹ ስላሸበሩት ሕዝብ ግን ምንም አለማለታቸው “እንዳያስገመግማቸው” ያስፈራል፡፡ ከ“ምርጫው” በኋላ የሚመጣውን የፈሩ ይመስላል ቀላጤ ሬድዋን ኅያዋንን ብቻ ሳይሆን ሰማዕታትንም ዜግነት በመንፈግ ትጋታቸውን ጨምረዋል፡፡ ስለዚህ ደብዳቢ ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ያጣሩልን” እንላለን፡፡ ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን … [Read more...] about ቀላጤ ሬድዋን – ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸው” ይጣራልን!
“እኛን ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው”
አይሲስ በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያንን መያዙን ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዮጵያዊ ለቪኦኤ ገለጸ፡፡ እርሱንና ሌሎችን በአይሲስ እንዳይወሰዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማስጣላቸውን ተናገረ፡፡ ይኸው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ወገን እንደተናገረው እኛን ከአይሲሲ ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው፤ በሀገራችን በፍቅር ነው የኖርነው ክርስቲያኖቹን ለይታችሁ አትወስዱም በማለት ሙስሊሞቹ እንደተከራከሩላቸው፤ እንደጮሁላቸው አስረድቷል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱና ሌሎች ላሁኑ ከመሞት ተርፈዋል፤ ከዚህ ወዲህ የሚሆነውን ግን ለመናገር እንደማይችልና ሁሉንም “እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው” በማለት በእምነት እየጠበቁ መሆናቸውን ከተሰወረበት ቦታ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡ ይኸው ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዮጵያዊ ከዚህ በፊት ቤንጋዚ ላይ ከሌላ የትግራይ ተወላጅ ጋር ተይዘው በኤሌክትሪክ … [Read more...] about “እኛን ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው”
“ሕገወጦቹ!”
አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡ አዲስ አድማስ እንዲህ ይላል፡- “በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው - በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡ “ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው - ስልክ ተደውሎ። … [Read more...] about “ሕገወጦቹ!”
“አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች
* “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን” ቴድሮስ አድሃኖም በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ የተጀመረው ጥቃት ያስቆጣቸው የናይጄሪያ እንደራሴዎች በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ የሩዋንዳውን ፕሬዚዳንት በማስተናገድ የተጠመዱት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ አፍሪካ “የተፈጠረው ጊዜያዊ ችግር ነው ብለን እናምናለን” በማለት አስተያየት ሰጡ፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴድሮስ ከየቦታው ሃሳብ እየሰበሰብኩ ነው፤ “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉ ድጋፍ እናደርጋለን” አሉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግን የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የተነሳው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ ብዙዎችን እኤአ በ2008 የተከሰተውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል፡፡ በወቅቱ ከስድሳ በላይ … [Read more...] about “አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች
“አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት
ደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ዓመጽና ግድያ ቦኮ ሃራም የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ግጭቱንና ግድያውን እንዲያስቆም ገደብ ሰጠ፡፡ "አይማረኝ አልምራችሁም" አዘል መልዕክት ማስተላለፉ ተገልጾዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ያዕቆብ ዙማ ልጅ የውጭ አገር ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ መባረር አለባቸው በማለት ከተናገረ በኋላ የተነሳው ዓመጽና አሰቃቂ ግድያ በርካታዎችን ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል፡፡ ከኤድዋርድ ዙማ በተጨማሪ የዙሉው ንጉሥ ተመሳሳይ ንግግር በማድረጋቸው አፍሪካውያን በአፍሪካውያን ላይ ለማመን የሚከብድ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለተለያዩ የውጭ አገር ዜጎች ዘግናኝ ሞት ምክንያት የሆነው ቀውስ በቶሎ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ የተለያዩ የዜና መዋዕሎች ዘግበዋል፡፡ እስካሁን በእርግጠኝነት … [Read more...] about “አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት
“የወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!
የዘመቻው ቃል አቀባይ መግለጫ . . . * የወሳኙ ማዕበል ሳውዲ መራሽ ዘመቻ በሁቲ አማጽያንን ላይ ከተጀመረ ወዲህ የአማጽያኑን የመከላከልና የማጥቃት አቅም ለማዳከም 1200 የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የዘመቻው ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በሶስተኛ ሳምንት በደፈነው ዘመቻ ገለጻቸው አስታውቀዋል * አማጽያኑ በተከፈተባቸው የህብረቱ አየር ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ የአየር ሀይልና የምድር ጦር መሽመድመዳቸውን ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ በየመን ግዛቶች በሸብዋን፣ አብያን፣ ላህጅና ያፍዕ በምድርም አማጽያኑን የሚቃወሙ ሀገር ወዳድ የጎሳ መሪ የመናውያን ጠመንጃ አንስተው እየተፋለሟቸው መሆኑን ጠቁመዋል። የህብረቱ ቃል አቀባይ በማከልም በምድር የተጀመረውን የየመናውያን እንቅስቃሴ ህብረቱ ድጋፍ እንደሚሰጠውም ተናግረዋል * የኢራንና የሂዝቦላህ ሁቲዎችን በመደገፍና በማሰልጠን … [Read more...] about “የወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!
“በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል” ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
በአሜሪካ ከሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ለፍሕትና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ አባላት ጋር በተለያዩ ስቴቶች ለመወያየት ወደዚያ ለማቅናት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያመሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ባላወቁት ምክንያት ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ጉዟአቸው እንደስተጓጎለ ገለጹ፡፡ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወደ አሜሪካ ለመብረር ሁሉን ነገር አሟልተው ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የአውሮፕላን መሳፈሪያ ሰዓት እስከሚደርስ ሊሸኟቸው አብረዋቸው ከነበሩ ጓደኞቻችው ጋር ሲጨዋወቱ አምሽተው ወደ ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ የመጨረሻውን ፍተሻ አልፈው ወደ አውሮፕላን መግቢያ በር ለማምራት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ፍተሻ ጋ ሲደርሱ ፓስፖርታቸውን … [Read more...] about “በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል” ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር