ታዳጊ ወጣት ሐና ላላንጎን ደፍረው ለሕይወቷ ማለፍ ምክንያት ሆነዋል የተባሉ አምስት ተከሣሾች ተፈረደባቸው፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በተበየነባቸው ወንጀለኞች ላይ ያሣለፈው ከ17 ዓመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ቅጣት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አንደኛና ሁለተኛ ተከሣሽ ሣምሶን ሺበሺና በዛብህ ገብረማርያም በሃያ ዓመት እሥራት፣ ሦስተኛ ተከሣሽ በቃሉ ገብረመድህን በ17 ዓመት እሥራት፣ አራተኛ ተከሣሽ ኤፍሬም አየለ በሃያ ዓመት እሥራት፣ አምስተኛ ተከሣሽ ተመስገን ፀጋዬ በ18 ዓመት እሥራት እንዲቀጡ ችሎቱ ፈርዷል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ተከሣሾች ፍርዱ ከተሰማ በኋላ ችሎቱን ዘልፈዋል፡፡ የሃና ላላንጎ አባትና የቅርብ ዘመዶቿ በቅጣቱ እንዳልረኩ ተናግረዋል፡፡ ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ (መለስካቸው አመሃ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ) … [Read more...] about በሐና ላላንጎ ጉዳይ የተከሰሱት 17-20 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
News
ዜና
የዳርፉሩ “ወንጀለኛ” ከደቡብ አፍሪካ አመለጡ
* አልበሽር አገራቸው ሲገቡ “ደማቅ” አቀባበል ተደርጎላቸዋል በዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ ወንጀል በመፈጸም እንዲያዙ ማዘዣ የተቆረጠባቸውና ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ በፍርድቤት የተወሰነባቸው የሱዳኑ ተፈላጊ ወንጀለኛ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር አምልጠው አገራቸው ገብተዋል፡፡ እሁድ ማምሻውን ከነበሩበት ቦታ በመሰወር ወደ ደቡብ አፍሪካ የአየር ኃይል ቤዝ በመደብ የቆዩት አልበሽር ሰኞ ዕለት ከተሰወሩበት አየር ኃይል ተነስተው አገራቸው ገብተዋል፡፡ እዚያም ሲደርሱ “ደማቅ” አቀባበል እንደተደረገላቸው ተነግሯል፡፡ አልበሽርን ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት የአይሲሲ ባለሥልጣናት ደቡብ አፍሪካ በፈጸመችው “ክህደት” በሚባል ተግባር እንዳዘኑ ገልጸዋል፡፡ ምክትል ዓቃቤ ሕጉ ጀምስ ስቴዋርት ለቢቢሲ እንዳሉት አሁንም ተስፋ በማድረግ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉና ፍትህ እንዲበየን … [Read more...] about የዳርፉሩ “ወንጀለኛ” ከደቡብ አፍሪካ አመለጡ
ኦማር አልበሽር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ ታገዱ
ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት የከሰሳቸውና እንዲያዙ ማዘዣ የቆረጠባቸው የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ከሄዱበት ደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ እዚያ የሚገኝ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሰጠ፡፡ በኢትዮጵያ በሰው ዘር ላይ ወንጀል ለፈጸሙ የህወሃት ሹሞች ይህ ታላቅ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል አይሲሲ የሚባለው ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር የዛሬ ስድስት ዓመት አካባቢ በዘር ማጥፋትና በጦር ወንጀለኝነት ክስ መስርቶ እጃቸውን እንዲሰጡ ወይም እንዲያዙ ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር፡፡ የተወነጀሉበት ክስም በደቡብ ሱዳን አማጽያንን ትረዳላችሁ በማለት ሦስት ጎሣዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም፣ ሴቶች እንዲደፈሩ፣ ነዋሪው እንዲፈናቀል፣ እንዲገደል፣ ወዘተ የጃንጀዊድ ሚሊሻዎችን በማስታጠቅ በሥፍራዎቹ … [Read more...] about ኦማር አልበሽር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ ታገዱ
በአዲስ አበባ መብራት እንዳይቋረጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
* የከተማዋ መብራት መቋረጥ ችግር የከተማዋ ዕድገት ነው * የችግሩ ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ነው * የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡና ግድቦች አለመሙላታቸው ነው ችግሩ * ለጥናቱ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል * ዕቅዱ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ተግባራዊ ይሆናል በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ 12 የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ከተሞች በየጊዜው የሚገጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል … [Read more...] about በአዲስ አበባ መብራት እንዳይቋረጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
“ብሄድም እመለሳለሁ”
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አራተኛ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ዌንዲ ሸርማን ሰኔ 23፤ 2007 ዓም ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ከተሰማ ጥቂት ሳምንታት የተቆጠሩ ቢሆንም ተመልሰው በከፍተኛ ባለሥልጣንነት ሊመጡ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ሸርማን በወቅቱ ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ያሰሙት ንግግር ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው ነበር፡፡ ባለሥልጣኗ ፈጽሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለኢህአዴግ በካድሬ ደረጃ ሙገሳ ቸረው ነበር፡፡ ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ያለውን ህዳሴ ካወደሱ በኋላ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጠ አስተዳደር ሥር እንዳለች ተናግረው ነበር፡፡ በመቀጠልም ይህንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን በኃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱ በሙሉ ሊጠነቀቁ እንደሚገባቸው አሳሰቡ፡፡ ሲቀጥሉም ግንቦት ሰባትን በስም … [Read more...] about “ብሄድም እመለሳለሁ”
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ “ሰላይ” ነው – ዲና ሙፍቲ
* “አቶ መለስ በጣም ይናፍቁናል” አሸባሪነት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ ያልቻለው ሕዝቡ በሙሉ ሰላይ በመሆኑን ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ ከአገር ተሰድደው የሚውጡት አብዛኛዎቹ ገጠሬ ወጣቶች እንደሆኑና ሟቹ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዳሴ አባት በጣም እንደሚናፍቋቸው ተናገሩ፡፡ ቀድሞ በቃል አቀባይነት ሲሰሩ የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኬኒያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ስታንዳርድ ዲጂታል ከተባለ የኬኒያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ድርጅታቸውን በመወከል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአልሸባብና መሰል ታጣቂዎች የአሸባሪነት ተግባር በኢትዮጵያ ለማድረስ ያልቻሉበት ምክንያት ምንድርነው ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱ ሕዝቡ ሰላይ እንዲሆን የሰለጠነ መሆኑን በመጥቀስ ማንኛውንም ተጠርጣሪ ድርጊት ህዝቡ ሲያይ ሪፖርት እንደሚያደር ተናግረዋል፡፡ ሠራዊቱም እስኪበቃው ድረስ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ “ሰላይ” ነው – ዲና ሙፍቲ
ምርጫ ቢቀርስ?!
* “በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል” * “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም” * ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ * ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ጠቅሰው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ442 የምርጫ ክልሎች ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ መግለጹን ተክትሎ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና መኢአድ የምርጫውን ውጤት አንቀበለውም ብለዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው … [Read more...] about ምርጫ ቢቀርስ?!
ሥልጣን ወደ ህወሃት?!
* “ግምገማ!” የኢህአዴግ ስድብ ሃይማኖት “ምግባረ ብልሹዎች ናችው፤ የሚታፈርባቸው ናቸው። እነሱን ብሆን ራሴን እንዳዋረድኩ ነው የምቆጥረው” ሲሉ የመድረክ ሊቀመንበር በየነ ጴጥሮስ ሃይለማርያምንና “ሌሎችም ቢሆኑ” ሲሉ የገለጹዋቸውን ባለሥልጣናት ምግባር ተቹ። ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ቢኖር ኢህአዴግ እንደሚሸነፍ ከ፱፭ በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውንም አመለከቱ። ተቃዋሚዎችን ሕዝብን ወዳልተፈለግ አቅጣጫ እየመሩ ነው በማለት በመወንጀል የማስጠንቀቂያ መልእክት ያስተላለፉትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ተከትሎ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ዶ/ር በየነ “የሞራል ብቃት የላቸውም” ሲሉ ሃይለማርያምን ክፉኛ ተችተዋቸዋል። “ለፓርላማ” ማብራሪያ ሲሰጡ “አንተ በምትሰጠው ውሳኔ እንገዛለን” በማለት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ሃይለማርያም የሰላ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ባለሙሉ ሥልጣን መሪ ባይሆኑም ኢህአዴግን … [Read more...] about ሥልጣን ወደ ህወሃት?!
በአሜሪካ የንቦች ሞት ቁጥር ጨመረ
በአሜሪካ በብሔራዊ ደረጃ በተደረገ ምርምር የንቦች ቁጥር 40 በመቶ እንደሚቀንስ ተነገረ፡፡ ለንቦቹ መሞት ዋንኛ ምክንያት ንቦቹ በከፍተኛ ሃሳብና ጭንቀት ውስጥ መግባታቸው እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ሰኞ (ግንቦት 10/ሜይ 18) ዕለት የሜነሶታ የሕዝብ ሬዲዮ (Minnesota Public Radio News) እንደዘገበው በአሜሪካ ውስጥ በአጠቃላይ በተደረገው አዲስ ጥናት 6ሺህ ንብ አርቢዎች መጠይቅ የተደረገላቸው ሲሆን በዚህም መሠረት የሟች ንቦች ቁጥር በተለይ በበጋ ወራት እንደሚጨምር ተገልጾዋል፡፡ በተቃራኒው በክረምት ወራት ቁጥሩ በመጠነኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በአሜሪካ ከሚገኙት ጠቅላይ ግዛቶች በሰሜን በምትገኘው የሜነሶታ ግዛት የሟቾቹ ንቦች ቁጥር ከፍ እንደሚል ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል፡፡ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑትና ጥናቱን የመሩት ዴኒስ … [Read more...] about በአሜሪካ የንቦች ሞት ቁጥር ጨመረ
መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች
በቅርቡ በሥልጣን ላይ እያሉ በምርጫ መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት የናይጄሪያው ጉድላክ ዮናታን በአፍሪካ የ65 ዓመታት የምርጫ ዴሞክራሲ ጉዞ ከሚጠቀሱ ጥቂቶች መካከል አንዱ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ይህም ተግባራቸው በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ታላቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የፖለቲካ ሰው አድርጓቸዋል፡፡ በአፍሪካ በተካሄዱ በርካታ ምርጫዎች የሕዝብን ድምጽ በማክበር ሥልጣናቸውን ለተቀናቃኛቸው በማስረከብ የሕዝባቸውን ድምጽ ያከበሩ መሪዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሁሉንም ለአሁኑ ማቅረብ ባንችልም የተወሰኑት ተጠቃሾች እነዚህ ናቸው፡- 1. ኤደን አብዱላ ኦስማን ዳር (ሶማሊያ) - በተለምዶ ኤደን ዳር ተብለው የሚጠሩት እኚህ ፖለቲካኛ የሶማሊያ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ በሥልጣን በነበሩበት ጊዜ ሶማሊያን እኤአ ከ1960 እስከ 1967 መርተዋል፡፡ (በዚህ ጽሁፍ … [Read more...] about መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች