በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ ከሦስት ወር በላይ አስቆጥሯል፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በጋራ ሙለታ ግራዋ ወረዳ ዛሬም የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደነበር፤ ዛሬ በአምቦ የአዋሮ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በጥይት መገደሉን የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል። በተጨማሪም እዚያው አምቦ ውስጥ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ቃጠሎ መነሣቱን፣ በተጨማሪም ምዕራብ አርሲ ውስጥ በሻሸመኔ ወረዳ አጄ በተባለች የገጠር ከተማ ውስጥ የሚገኝ እሥር ቤት ተሰብሮ እሥረኞች እንዲወጡ መደረጉን የሬዲዮው የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች … [Read more...] about በአምቦ የ9 ዓመት ልጅ በህወሃት ነፍጥ አንጋቢዎች ተገድሏል
News
ዜና
የእስራኤል ቀድሞው ጠ/ሚ/ር ወደ “ቃሊቲ” ወረዱ፤ የሃይማኖት መሪም ተከትለዋቸዋል
* “ማንም ከሕግ በላይ መሆን አይችልም” ታሳሪው ጠ/ሚ/ር የቀድሞ የእስራኤል ጠ/ሚ/ር ኤሁድ ኦልመርት ወደ እስር ቤት ወረዱ፡፡ በሃይማኖቱ ዓለም ታላቅ ዝነኝነትን የተጎናጸፉት ራባይ (ረቢ) ዮሺያሁ ፒንቶም ወደዚያው አምርተዋል፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የህወሃት/ኢህአዴግ “ሻኮችን” ማን ይንካቸው ሲሉ ጠይቀዋል? እስራኤልን ለሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት የሰባ ዓመቱ ኤሁድ ኦልመርት ከሙስና ጋር በተያያዘ የ19 ወራት እስር ተበይኖባቸው እስርቤት ወርደዋል፡፡ በአስተዳደር ዘመናቸው ከፍልስጤማውያን ጋር ስምምነት ለማድረግ ከፍተኛ እርምጃዎች ሲወስዱ የነበሩት ኦልመርት ወደ ወሳኝ ደረጃ ላይ ሲደርሱ በሥልጣን ላይ እንዳሉ በሙስና፣ ጉቦ፣ እና ሌሎች ገንዘብ ነክ ወንጀሎች መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡ በተለይም የአናፖሊስ ኮንፍራንስ በተባለው ስብሰባ በርካታ ውሳኔዎችን ለድርድር … [Read more...] about የእስራኤል ቀድሞው ጠ/ሚ/ር ወደ “ቃሊቲ” ወረዱ፤ የሃይማኖት መሪም ተከትለዋቸዋል
ምግባረ ብልሹዎቹ “የመልካም አስተዳደር” ሰባኪዎች
“የኢትዮጵያ ፓርላማ” እየተባለ በሚጠራው የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ አነጋገር “እስከ እንጥሉ ስለገማው ኢህአዴግና የመንግሥት ሌቦች” ጉዳይ (በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አጠራር “መልካም አስተዳደር” ጉዳይ) ከቀናት በፊት ሪፖርት ቀርቦ ነበር፡፡ አዲስ ፎርቹን ከፎቶው ጋር አያይዞ ያተመው ዜና እንደሚያስረዳው እና ፎቶው በገሃድ እንደሚያሳየው በሪፖርቱ መ/ቤታቸው በአስተዳደር ብልሹነት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙት የኢህአዴግ ሹመኞች አባተ ስጦታው (የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ) እና መድኀን ኪሮስ (የፍርድ ቤቶች ምክትል ፕሬዚዳንት) ከአፈጉባኤው አባዱላ ጋር በቃላት ሰይፍ “ሕዝባዊነታቸውን” ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ጋዜጣው ሹመኞቹን በጓደኞቻቸው ፊት “ሲያጉረመርሙ” ተሰሙ ቢልም፤ በርካታ ማኅበራዊ ሚዲያዎች “ዱላ ቀረሽ” ግብግብ ብለውታል፡፡ ጋዜጣው እንዳለው ከሆነ የአዲስ አበባ … [Read more...] about ምግባረ ብልሹዎቹ “የመልካም አስተዳደር” ሰባኪዎች
ሩሲያ ሙሰኞችን “በመሣሪያ” ልትመረምር ነው
በሩሲያ የሞስኮ ባለሥልጣናት ሙስናን ለመዋጋት በሚል ውሸታሞችን በመፈተኛ (lie-detector test) የመንግሥት ሠራተኞችን ልትመረምር ነው፡፡ ሰሞኑን የሩሲያው ኢንተርፋክስ እንደዘገበው በሞስኮ የሚገኙ የመንግሥት ሹማምንት በሙሉ ውሸታሞችን በሚመረምረው መሣሪያ ሞሳኞች መሆን አለመሆናቸው እንደሚመረመር አስታውቋል፡፡ የፖሊግራፍ መፈተኛ የሚባለው በተለምዶ ውሸታሞችን መመርመሪያ ተብሎ የሚጠራው መፈተኛ በወንጀለኝነት የተጠረጠሩ ሰዎች የሚፈተኑበት ነው፡፡ ተፈታኝ ሰው ላይ የሚገጠመው መሣሪያ ግለሰቡ ጥያቄዎች በቀረቡለት ጊዜ መልስ ሲሰጥ የሚከሰተውን የልብ ምት፣ የደም ግፊት፣ አተነፋፈስ፣ የቆዳ መቆጣት፣ ወዘተ ይመረምራል፡፡ በዚህም መሠረት ግለሰቡ ለተጠየቀው የመለሰው እውነት ወይም ውሸት መሆኑን መሣሪያው መጨረሻ ላይ በሚሰጠው ሪፖርት ያረጋግጣል፡፡ መሣሪያው ፍጹም እውነተኛ አይደለም … [Read more...] about ሩሲያ ሙሰኞችን “በመሣሪያ” ልትመረምር ነው
በሃዋሳ በሶስት ጥይት ስለተገደለው
ባፈው ሃሙስ በሃዋሳ ከተማ ከተማ ልዩ ስሙ ታቦር ት/ቤት በሚባል አካባቢ ፖሊስ በሦስት ጥይት አንድ ሰው መግደሉ በዕለቱ ወዲያውኑ ከሥፍራው መረጃ ቢደርሰንም እስካሁን ተጨማሪ መረጃዎችን ስናሰባስብ ቆይተናል፡፡ የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) የላኩልን በምስል የተደገፈ መረጃ እንደሚያመለክተው ድርጊቱ የተከሰተው ግለሰቡ ለቤ/ክ ወደተከራየ ጊቢ ለመግባት በር ላይ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ዘጋቢያችን ጠቁመዋል፡፡ ቤቱ ለቤተክርስቲያንነት ቢከራይም የቤተሰቦቹ የሆነውን ቤት እሱ ሳያውቅ የተከራ በመሆኑ እንዲለቁለት ተከራዮቹን በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበር መረጃ አቀባያችን ያስረዳሉ፡፡ እንደተለመደው በዕለቱም ይህንኑ ጥያቄውን ለማቅረብና ወደ ጊቢው ለመግባት በሚሞክርበት ጊዜ ተከራዮቹና ሌሎች ውስጥ የነበሩ ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ መጥራታቸውን ዘጋቢያችን በላኩልን መረጃ … [Read more...] about በሃዋሳ በሶስት ጥይት ስለተገደለው
በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም
በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታና ደኅንነት ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ አለመሆኑ ተነገረ፡፡ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ወደ መስክ የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ተከለከለ፤ የፕሮጀክት ሥራዎች ሊደናቀፉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ኢህአዴግ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን ወደተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን መረጃው የደረሳቸው ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለይ የአማራ ክልልና በምዕራብ ደግሞ የጋምቤላ ክልል አካባቢ ያለው ውጥረት እጅግ እያየለ በመምጣቱ በቦታዎቹ ላይ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ሊደርስባቸው ስለሚችል ጉዳት ተጠያቂ እንደማይሆን ኢህአዴግ በሰጠው ማሳሰቢያ አስታውቋል፡፡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል የካቶሊክ ዕርዳታ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም
መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
* “የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሊደርስ ይችላል” ነዋሪዎች * “የሞቱት 14 ሰዎች ናቸው” ኢህአዴግ ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በበኩሉ የሞቱት 14 ብቻ ናቸው ይላል፡፡ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያ እንደ “ገጸ በረከት” ያመጡት መለስ በየቦታው የጫሩት እሣት ለፍርድ ሳያቀርባቸው ሾልከዋል፡፡ እሣቱ ግን አሁንም እየነደደ ነው፡፡ ጎልጉል ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ ባገኘው መረጃ መሠረት በግጭቱ የሞቱት እስከ መቶ እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ግጭቱ ከመነሻው በቀላሉ የተነሣ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሥር የሰደደ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንኑ ዜና ኢሳት ሲዘግብ የሟቾቹ ቁጥር ከመቶ እንደሚያልፍ ምንጮቹን ጥቅሶ … [Read more...] about መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
ሥልጣን የያዙ ሰሞን ሞት የቀደማቸው መለስ ሲጠየቁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እመግባለሁ ወይም ሲመገብ አያለሁ የሚል የውሸት ተስፋ ሰጥተው ነበር፡፡ “የቀማኛ ኢኮኖሚ አቀንቃኝ” የነበሩት መለስ ለሥልጣናቸው ማራዘሚያ ጥቂቶችን በሃብት እንዲወጠሩ ሲያደርጉ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ቀርቶ በሶስት ቀን አንዴ የማይመገብ አድርገውት ተሰናብተዋል፡፡ “ሌጋሲያቸውን እንጠብቃለን፤ እናስጠብቃለን” የሚሉት ያሁኖቹ ዘራፊዎችና ተላላኪዎች አገር በሁለት አኃዝ አድጋለች፤ ኢኮኖሚው ዓለምን እያስደነቀ ነው፤ ህዳሴ ነው፤ ውዳሴ ነው፤ … በማለት በቁማቸው ይዋሻሉ፤ የጥቅም ተካፋዮቻቸውም ይህንኑ ይዘው በየቀኑ ሲያናፉ ይውላሉ፡፡ ህወሃት ስለዘረጋው የዘራፊ፤ የቀማኛ፤ የሌባ፤ ኢኮኖሚ ብዙ ሊባልበት ይቻላል፡፡ ሌብነቱን ደግሞ መለስ ራሳቸው መስክረው ነው የሞቱት፡፡ “ያስቸገረን የመንግሥት … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
“ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
"መንግሥት ስህተቱን ካመነ ኦሮምያ ውስጥ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ አጥፊዎች በገለልተኛ አካል ተለይተው ይቀጡ” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጠይቀዋል። “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” ሲሉም ተችተዋል። “ቀደም ሲል የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በኦሮምያ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋናው መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው” ማለታቸው ይታወቃል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ መለስካቸው አምሃ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር አለው፡፡ እዚህ ላይ ያዳምጡ። (ምንጭ: VOA) … [Read more...] about “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ ሊያስገባ”?!
* ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” አና ጎሜዝ * የቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያዊ ልመና” አልሰራም የአውሮጳ ፓርላማ ሐሙስ ዕለት ባለ 19 ነጥብ ውሳኔ ህወሃት/ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ላይ አስተላልፏል፡፡ ጉዳዩ ኢህአዴግ “ልክ ሊገባ ይሆን” የሚል አመለካከት ጭሯል፡፡ ረቂቁ ለውይይት እንዳይቀርብ የቻሉትን ያህል የጣሩት ቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያቸው” አልሠራም፡፡ ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” በማለት አና ጎሜዝ ተናገሩ፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው” ብለውታል፡፡ የአውሮጳ ፓርላማ ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ የቀረበለትን ረቂቅ ውይይትና ክርክር ካካሄደ በኋላ በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ ያለ አንዳች ማሻሻያና ለውጥ እንዳለ አጽድቆታል፡፡ ጉዳዩን ከሥሩ ሲከታተሉና ለኅብረቱ … [Read more...] about የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ ሊያስገባ”?!