ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ለ30 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቋሟል። የብሩኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት ባቀረቡት ጥናት በቅርብ ዓመታት ተጠቃሚዎች የሚገለገሉባቸውን የተወሰኑ አፕልኬሽኖች፤ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አሊያም መላውን የኢንተርኔት አገልግሎት መንግስታት ማቋረጥ እና መዝጋት እየተለመደ የመጣ ክስተት መሆኑን አትተዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ከሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ለ30 ቀናት በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ይኸው ጥናት ጠቁሟል። «መንግስታት ብሔራዊ እና የሕብረተሰብ … [Read more...] about ኢንተርኔት በመዘጋቱ በትንሹ 9 ሚሊዮን ኪሣራ ደርሷል
News
ዜና
“የጣዕር ጊዜ አዋጁ” እና ኢትዮጵያ
የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ህወሃት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስላወጀው "አትኑሩ" አዋጅና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ስለሰጡት አስተያየቶች ያቀናበረውን ከዚህ በታች እንዳል አስፍረነዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና ኢትዮጵያ * "በብሔራዊ ደረጃ የመጣ ጥፋት ነዉ" የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የሚያጠናክሩ ማብራሪያዎችን ይፋ ከተደረጉ ወዲህ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ስጋታቸዉን መግለጽ ጀምረዋል። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፤ ይደረጋሉ የተባሉት መሻሻሎች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትንታኔ ይፋ ሲደረግ በተቃራኒዉ መንገድ የሚጓዝ ነገር መኖር እንደሚያመላክት ነዉ የተጠቀሰዉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዉጭ የሚሰራጩ የሽብርተኛ ድርጅቶች ልሳን ያላቸዉን መገናኛ ብዙሃን ማዳመጥ ያግዳል፤ … [Read more...] about “የጣዕር ጊዜ አዋጁ” እና ኢትዮጵያ
የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ጊዜ ገድቦ መናገር ይከብድ ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ ስለመሆኑ ክርክር የለም (አንዳንድ የወያኔ አንጋሽ ምዕራባውያን ባለሙያዎች በጥቂት ወራት ይተምኑታል)። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንድ “የፖለቲካ መክለፍለፎች” ሊወድቅ የተቃረበውን አገዛዝ እንዲውተረተር ዕድል ሊሰጠው ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ወገኖች ከያቅጣጫው ብቅ እያሉ ነው። የስጋታቸው መንስኤ ደግሞ በዋናነት የግልጽነት፣ ያለመተማመን፣ የውድድርና “ጊዜን” የመጠቀም ተራ እሽቅድምድም እንደሆነ እነዚሁ ስጋት የገባቸው ክፍሎች ይናገራሉ። ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ“ሽግግር” ዜናዎች፣ ዳር ዳሩን በለሆሳስ ይሰማ የነበረው “የሃሜት በሽታ” ገልጠውታል። በዚሁ መነሻ ይመስላል ለኦሮሚያ የሽግግር ሰነድ እንደሚዘጋጅ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ሰፊና ግልጽ ያለ መልስ ከሚመለከታቸው የእነ በቀለ ገረባ ወኪሎች ህዝብ እየጠበቀ … [Read more...] about የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!
በሙት መንፈስ አገር እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በይስሙላነት ባስቀመጠው ፕሬዚዳንት አማካኝነት ፓርላማ ብሎ በሰየመው የራሱ ስብስብ በኢትዮጵያ ያለ አንዳች ልዩነት ለገደላቸው ወገኖች አስከሬን መግዣ ብር ሰይሜአለሁ ብሏል፡፡ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ላፈሰሰው መድቤአለሁ ያለው 2.4 ቢሊዮን ብር እስካሁን የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ የሙት (መለስ ዜናዊን) ፎቶ ከፊት አስቀምጦ አሁንም በአስከሬን አገሪቱን እንደሚመራ በገሃድ ያሳየው ህወሃት ለመለወጥም ሆነ ስለ ለውጥ ለማሰብ ፍላጎት እንደሌለው ነው በጥቅሉ ያመላከተው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በእስር እያማቀቀ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ፓርቲዎች እንዳንቀሳቀሱና ኅልውና እንዳኖራቸው በርካታ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ምርጫ ኮሚሽን ማዋቀር፣ … የሚሉ የጥገናዊ ለውጦች ስሜት እንኳን የሌላቸውን ጉዳዮች … [Read more...] about ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!
ህወሃት/ኢህአዴግ ዕድሜዬ ከ6 ወር አይበልጥም አለ
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት ላለፉት 25ዓመታት መብት በገፍ ሲሰጥ የቆየ ይመስል ህገመንግሥታዊ መብቶችን የሚገፍ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። አዋጁ ለስድስት ወር ይቆያል ማለቱ የህወሃት ዕድሜ ከስድስት ወር እንደማይቆይ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ከህወሃት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት እሁድ በሃገሪቱ “ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ” በሚል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን አስታውቋል። እንደ ኃይለማርያም ንግግር ህገመንግሥታዊ መብቶች የማይጣሱ መሆናቸው ቢነገርም እዚያው የኃይለማርያም ካቢኔ አባል የሆነው የጠቅላይ አቃቤ ሹመኛው ጌታቸው አምባዬ ህወሃት በቀጣይ እንደፈለገ የሚያደርጋቸውንና የሚገድባቸውን መብቶች በዝርዝር ተናግሯል። እነዚህም:- 1) ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንኛውንም ሰው ይታሰራል፤ … [Read more...] about ህወሃት/ኢህአዴግ ዕድሜዬ ከ6 ወር አይበልጥም አለ
የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከቢሾፍቱ ተጭነው ተወሰዱ
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ ቅዳሜ (8 ኦገስት) ሙሉ በሙሉ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማረጋገጥ ችለናል። የትግራይ ተወላጆቹ ከተማዋን ለቅቀው የወጡት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የአካባቢው ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በወውጣት እያካሄደ ባለው ሕዝባዊ አመጽ ሊመጣ ካለው አደጋ ለማምለጥ ነው። ህወሃት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በከተማዋ ያሉ ሁሉ ሲቃወም የትግራይ ተወላጆች ግን ዝም ማለታቸው ሕዝቡን በእጅጉ እንዳስቆጣው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የትግራይ ተወላጆቹ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉ ከተማዋን ለቅቀው ወዴት እንደሄዱ የታወቀ ነገር የለም። ላለፉት አራት ቀናት በደብረዘይት እንደ አብዛኞቹ ከተሞች የንግድ እና የስራ እንቅስቃሴ ቆሟል። ሱቆች ተዘግተዋል፣ ሕዝብም … [Read more...] about የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከቢሾፍቱ ተጭነው ተወሰዱ
የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
የትግራይ ህዝብ ከማን አገዛዝ ነጻ እንዲወጣ እንደሚፈለግ በውል ባይታወቅም ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” የሚለው ህወሃት በቢሾፍቱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ የሚዘክር ሃውልት እንዲቆም ሃሳብ መቀረቡ ተሰማ። የኢሬቻን ክብረ በዓል ለማክበር የተሰባሰቡ የኦሮሞና የሌሎች ቦታዎች ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ትውልድ ሁሉ በማንና እንዴት እንደተፈጸመ እንዲያውቅ፣ እንዲማርና የተከፈለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዳ፣ እንዲሁም ምስክር ሊሆን በሚያስችለው መልኩ ሃውልቱ እንደሚታነጽ ለማወቅ ተችሏል። ለመብታቸው የተነሱና በሰላማዊ መንገድ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን “በቃህ፣ ልቀቀን” በማለታቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላለፉት አስራ አንድ ወራት ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉና ሲሰቃዩ መቆይታቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ቢሾፍቱ የኢሬቻን ክብረ በዓል … [Read more...] about የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
አዲስ አበባ ተቆላልፋለች
ወቅታዊ ሪፖርታዥ በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል። አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ "ሕዝብ ላይ አልተኩስም" ማለታቸው የህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል። አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል። ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል። በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ሕዝባዊ አመጽ ለማዳፈን በህወሃት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በመወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶ … [Read more...] about አዲስ አበባ ተቆላልፋለች
“አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን ድፍን አገርን ማቅ ያለበሰው የጅምላ ጭፍጨፋ እያደር አጥንት የሚያደቅ መረጃ እየወጣበት ነው። ህወሃት የእርቅ መንገዶችን በሙሉ አሟጦ የቀበረበት ይህ “ይቅርታ የሌለው ወንጀል” እስካሁን የ678 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። የትዳር ጓደኛውን አስከሬን በግል ተሽከርካሪ ጭኖ እያነባ ወደ ቤተሰቡ የወሰደ አለ። ገንዘብ ተዋጥቶለት የሚስቱን አስከሬን ጭኖ ወደ ሱሉልታ የተጓዘ መኖሩ ተሰምቷል። እናትና ልጅ ባንድነት ቀብራቸው ተከናውኗል። በአንድ ቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወገኖች ከቤተሰባቸው ጎድለዋል። አስከሬን አሁን ድረስ እየተቆፈረ እየወጣ ነው። ሃይቅ ላይ የተንሳፈፉ አስከሬኖች እየተለቀሙ ነው። ህዝብ ቁጣው ገንፍሎ በተለያዩ ስፍራዎች እምቢተኛነቱን እየገለጸ ነው። ህወሃት ግን አሁንም ይዋሻል። በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ በታጣቂዎች … [Read more...] about “አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ
ዛሬ ጨለሞ ዋለ። ዛሬ አገር ማቅ ለበሰች። ዛሬ የሆነውን ማመን ይከብዳል። ቄጤማና ቅጠል ይዘው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተረሸኑ። "Down! Down! Woyane … Down! Down TPLF! …" በማለት ቁጣውን የገለጸ ሕዝብ እገዛሃለሁ በሚለው የትግራይ ህዝብ ተገንጣይ ቡድን (በህወሃት) ተጨፈጨፈ። ከአየርና ከምድር ጭስና ጥይት የተረጨበት ህዝብ፣ የሚገባበት ጠፍቶት የውሃ ራት ሆነ። ሞተ። ቆሰለ። በውሃ ተበላ። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሚባለው የወንበዴው ቡድን መሪ መለስ ሞት በድንገት እንደ ቡሽ ክዳን አፈናጥሮ ሲወስደው ጥቁር ለበሶ ሳግ እየተናነቀው ዜና ያወጀው ተመስገን በየነ፣ ዛሬ ነጭ በነጭ ለብሶ አኻዝ ባይጠቅስም የሰው ህይወት ማለፉን የተናገረው “ሰፊውና የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ” በማለት ነበር። ተመስገን ከጌታቸው የተላከለትን ሰዎች “በመረጋገጥ” … [Read more...] about በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ