ህወሃት የታሪኩ ካስማና ማገር ከአስከሬን ጋር የተጣበቀ ስለመሆኑ የሚመሰክሩበት የሩቅ ሰዎች አይደሉም። አብረውት በበረሃ የነበሩ፣ አብረውት አመራር ሲሰጡ የኖሩ፣ “በሚያራምዱት አቋም” ከድል በፊትና በኋላ የተለዩት በተለያዩ ሚዲያ ላይ እንደመሰከሩት ህወሃት ደም ምሱ፣ አስከሬን ትራሱ ነው። በነዚሁ የቅርብ ሰዎቹ የተሰሙት ምስክርነቶች ስም፣ ቦታ፣ ጊዜ በመጥቀስ በወቀቱ እዚያው እንደነበሩ በማረጋገጥ እንጂ እንዲሁ በመላ አልነበረም። እነሱ ለአብነት ተነሱ እንጂ ሰለባዎች በየጊዜው አዳዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ማለታቸው የተለመደ ነው። እዚህ ላይ ሌሎችም አይረሱም። ቅድሚያ ስለ ሌሎቹ። በቦታው የነበረ የዓይን እማኝ፤ ደደር 1983 የጅጅጋ ሆቴል ባለቤት ዓለምዘውድ እንዴት ሞተች? ዓለምዘውድ ቁመቷ ረጅም፣ ሰውነቷ ሙሉ፣ አሣ የምትመስል ጠይም፣ ደግና ርኅሩኅ እንደነበረች የሚያውቋት … [Read more...] about ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ
News
ዜና
“የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” ፕ/ር መረራ ጉዲና
"በውይይት የማይፈታ ችግር የለም። ስትወያዩ ግን የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱ ላይ አታተኩሩ። ትኩረታችሁን አሁን የተጋፈጥናቸው ችግሮች ላይ አድርጉ።" ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አስታወቁ። ፕሮፌሰሩ ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በኔዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ጋር በትላንትናው እለት 20 November 2016 በአምስተርዳም ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። በውይይቱ የኦሮሞ አክቲቪስቶችም ተገኝተው ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ስለ ሃገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ እና ስለወደፊቱ እጣ ፈንታ በስፋት ያብራሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ - ፕ/ር መረራ ጉዲና ከተሰብሳቢው ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል። "አዋጁ እና ኮማንድ ፖስቱ ሕዝባዊ አመጹን ያበርደዋል ወይ?" ተብለው ሲጠየቁ፣ ሃገሪቱ አሁን በመስቀለኛ መንገድ ላይ መሆንዋን ገልጸው አሁን ያለው ሁኔታ ላይ እንዲህ … [Read more...] about “የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” ፕ/ር መረራ ጉዲና
ኢህአዴግ ሲጨንቀው “አደገኛ ቦዘኔዎችን” ለስለላ እየመለመለ ነው
ሕዝባዊ ቁጣ ያንቀጠቀጠው ህወሃት/ኢህአዴግ በተለምዶ “የሰፈር ጉልበተኛ” የሚባሉ ወጣቶችን ለስለላ ስራ እየመለመለ እንደሆነ ተሰማ። ጥያቄውን ተቀብለው በየሰፈሩ ያሉትን የለውጥ አራማጆች ለመሰለል ፈቃደኛ ያልሆኑ እንደሚታሰሩ ለማወቅ ተችሏል። ከታሰሩት መካከል ከማዕከላዊ የተሰወረው ወጣት ጉዳይ በጥበቃ የተሰማሩትን ችግር ውስጥ ከቷቸዋል። አዲሱ ምልመላ የቀበሌ የስለላ መዋቅር መሰበሩን አመላካች እንደሆነ ተጠቁሟል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ዋቢዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ኢህአዴግ ቀደም ሲል “አደገኛ ቦዘኔ” ሲላቸው የነበረውን ወጣቶች ለስለላ ተግባር እየመለመለ ነው። የሚመለመሉት በሰፈር ውስጥ በተደባዳቢነት፣ በጉልበተኛነት የሚታወቁ ናቸው። በየሰፈሩ በተለምዶ “ጉልቤ” የሚባሉትን ወጣቶች የሚመለምሉት የህወሃት ሰዎች ናቸው። አመላመሉ በድንገት ከሚያዘወትሩበት ቦታ ወይም ከመንገድ … [Read more...] about ኢህአዴግ ሲጨንቀው “አደገኛ ቦዘኔዎችን” ለስለላ እየመለመለ ነው
የአሜሪካ ምርጫ እንደ ኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ
ለሁለት ዓመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሪፓብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የምርጫው ውጤት ለሒላሪ ክሊንተን ድምጻቸውን የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡ ምርጫው ለአንዳንዶች እንደ ኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ “ነጻነት” ወይም “ባርነት” የመምረጥ ያህል ተሰምቷቸዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሻለ አማራጭ የጠፋበትና ከሁለት ገዳይ ካንሰሮች አንዱን የመምረጥ ያህል ነው ተብሏል፡፡ ገና ከጅምሩ በሚሰጡት ከፋፋይ መልዕክት የመመረጥ ዕድል እንደሌላቸው ሲገመቱ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ለዚህ መድረሳቸው በርካታ የሚዲያ ሰዎችንና የፖለቲካ ተንታኞችን ያስደመመ ነው፡፡ ትራምፕ ፓርቲቸውን ወክለው ለመወዳደር ዕድል ካገኙ በኋላ እንኳን በታዋቂ ሪፓብሊካን ድጋፍ ተነፍጓቸው ቆይተዋል፡፡ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ሒላሪ ክሊንተን ጋር በምርጫ … [Read more...] about የአሜሪካ ምርጫ እንደ ኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ
ህወሃት/ኢህአዴግ የራሱን ሪፖርት ይፋ ማድረግ ፈርቷል!
ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት በሰኔ 2008ዓም “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ይህ በቃል “ለፓርላማው” የቀረበው ሪፖርት እስካሁን ድረስ ይፋ አልተደረገም፡፡ የሂውማን ራይት ዎችም እስካሁን በተደጋጋሚ ኢህአዴግ ሪፖርቱን “እንዲያወጣ” ጥሪ ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡ ጌታቸው ረዳ ከሂውማን ራይትስ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን ጋር በአልጃዚራ ላይ በቀረበ ጊዜ ሰብዓዊ መብት ድርጅቱን በመወከል ሚ/ር ሆርን ኢህአዴግ ሪፖርቱን ይፋ እንዲደርግ በይፋ ጠይቀዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመብት ድርጅቱ በወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” በኩል ለህወሃት/ኢህአዴግ … [Read more...] about ህወሃት/ኢህአዴግ የራሱን ሪፖርት ይፋ ማድረግ ፈርቷል!
“ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት
የለቅሶ ሳግ በያዘው አንደበት የመረረ ሃዘን ይሰማል። ተናጋሪዋ የሚሰሩት ድራማ ወይንም ዘጋቢ ፊልም ሳይሆን በትክክል የደረሰባቸውን ነው። የልጃቸው አስከሬን እንደ ምናምንቴ በማዳበሪያ ተደርጎ ነው የተሰጣቸው። ልብ ይነካል። ያማል። ጉዳዩ ከሃዘንም በላይ ይሆናል። አንድ ልጃቸው "መመኪያዬ" የሚሉት ተገደለባቸው፤ ሌላኛው ክፉኛ ተደብድቦ ታሟል፤ ሁለቱ ታስረዋል። እኚህ የ65 ዓመት አዛውንት ሲያልቅ አያምር ሆነና ባዶ ሆኑ። "ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ" አሉ። አስከትለው አስከሬኑ መበላሸቱንና ደም ይፈሰው እንደነበር ገለጹ። ወግ አይቀር ተቀበረ። አሁን አሁን "ወዴት እየሄድን ነው" ከማለትም ያለፈ ይመስላል። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የወረዳው አስተዳዳሪ "በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ያለ ችግር የለም" ማለታቸው፣ ዋና አስተዳዳሪውና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ሌላው … [Read more...] about “ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት
የቴድሮስ ቅሌት!!
ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት እየተወዳደረ ያለው የህወሃቱ ዕጩ ቴድሮስ አድሃኖም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አቅቶት በተደጋጋሚ ግልጹን ጥያቄ እንዲብራራለት ሲጠይቅ መዋሉ ብዙዎችን ያነጋገረና ያሳፈረ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ውርደቱ የከነከናቸው ትንታጉን አንደበተ ርቱዕ ኮ/ሎ ጎሹ ናፍቀዋል፡፡ በ2017 የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሚያገለግል ለመምረጥ ለ194 ዓባል አገራት በቀረበው ጥሪ መሠረት ህወሃት/ኢህአዴግ ከሚገዛት ኢትዮጵያ፣ ከጣሊያን፣ ከፈረንሣይ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከፓኪስታንና ከሃንጋሪ ስድስት ዕጩዎች አገራቱ አቅርበዋል፡፡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት ዕጩዎቹ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ የቃል መግለጫ ካቀረቡ በኋላ ከአባል አገራት ጥያቄዎች ቀርበውላቸውል፡፡ ቴድሮስ አድሃኖም ከአልጄሪያ፣ ከጀርመን፣ ከአውስትራሊያ፣ ከህንድ የቀረቡለትን ጥያቄዎች ጥቂቶቹን በቀጥታ … [Read more...] about የቴድሮስ ቅሌት!!
“ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የዓለም መገናኛዎች ርዕስ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ለቆ የመውጣቱ ጉዳይ ነው። የሶማሊያ ባለሥልጣናት ስለጉዳዩ የተነገራቸው አንዳችም ነገር እንደሌለ መግለጻቸው፣ አልሸባብም የሠራዊቱን እግር እግር እየተከተለ የተነጠቃቸውን ወረዳዎች መቆጣጠሩና ኢህአዴግ ጉዳዩን ያስተባበለበት አግባብ ጎልጉል የመረጃ አቀባዮቹን እንዲያነጋግር መነሻ ሆኗል። እንደ መረጃ ሰዎቹ ከሆነ በስም ተለይቶ ባይገለጽም ህወሃት በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ በጥርጣሬ መዝገብ ውስጥ ከገባ ሰነባብቷል። ሟቹ የኢህአዴግ ሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሠራዊቱ ወደ ሶማሊያ ሲንቀሳቀስ ፓርላማው ሳይወስን በመሆኑ ይህንን ለማብራራት በተጠራ ስብሰባ ላይ በዋናነት ያሰመረበት ጉዳይ የደህንነት ስጋትን ነበር። “የደህንነታችን ስጋት የሆኑትን አሸባሪዎች ከምንጫቸው ማድረቅ” በሚል … [Read more...] about “ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በሚል ስም የሚጠራ የፖለቲካ ድርጅት ዕሁድ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ በተፈረመ ስምምነት መቋቋሙ ተገለፀ፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲና የሲዳማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሆናቸውን አደራዳሪና አፈራራሚ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት በኢሊኖይ ቺካጎ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡ የንቅናቄው ዓላማ የግዛት አንድነቷ የተጠበቀ፣ ዴሞክራሲያዊ የሕዝብ መብቶች የተከበሩባት፣ የፖለቲካ ሥልጣን ከላይ እስከታች በተዋረድ ያሉትና በምርጫ የሚጨበጥ ሥልጣን የሚኖራትን ፌደላዊት ኢትዮጵያን መመሥረት መሆኑን ዶ/ር ጌታቸው ገልፀዋል፡፡ የትግላቸው ግብ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም፤ አዲስ ሕገመንግሥት እንዲቀረፅና ሁሉም ዜጋ እኩል የሆነባት … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ተመሠረተ
ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!
አሁን የሚፈለገው የሚያሻገሩ መሪዎችን ማግኘት ብቻ ነው። ሕዝብ በፖለቲካ መሪዎች ሃፍረትን እየተግሞጠሞጠና ደሙ ደመ ከልብ እየሆነ የሚኖርበት ዘመን እንዲያከትምለት ይፈልጋል። የአንተ ደም የእኔ ደም ነው በማለት የችግሩ ጉያ ውስጥ ሆኖ አጋርነቱን፣ አንድነቱን ሲያሰማ ሩቅ ተቀምጦ እንደ ቅጥረኛ የወገንን ሞራል ማላመጥ አግባብ አይሆንም። ውሎ አድሮ ከገዳዮቹ በላይ ያስጠይቃል። በቅጥረኛነትም ያስመድባል። ከአገራችንም ሆነ ከዓለም ዘመን የማይረሳቸው የውብ ስብእና ባለቤቶች ሕዝባቸውን አሻግረዋል። ክፉዎች የቀበሩትን የቂምና የጥላቻ ገመድ በጣጥሰው አገራቸው በልዕልና፣ ሕዝባቸው በሰላም እንዲኖር አስችለዋል። በቀናነት ጀምረው፣ በቀናነት ጨርሰዋል። በታማኝነት ሃላፊነትን ተረከበው በታማኝነት አለፈዋል። ዝርዝር ውስጥ ባንገባም በህይወት ያሉም አሉ። እንዲህ ያሉትን የሚያስቡ “እኛንስ ማን … [Read more...] about ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!