አሜሪካ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግን ከመውቀስ አልፋ እያስጠነቀቀች ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ የጉዞ ማዕቀቡ እንዲነሳለት እየወተወተ ስለመሆኑ በተለያዩ መገናኛዎች ተደምጧል። የጎልጉል መረጃ አቀባይ የዲፕሎማሲ ምንጮች እንዳሉት አሜሪካ ለኢህአዴግ ጥያቄ መልሷ “ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም” የሚል ሆኗል። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ የአራት ቀን የስራ ቆይታ ባደረገበት ወቅት “በግልጽ ተወያይተናል” የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ እንደሚባለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ለቪኦኤ አማርኛው ክፍል ብቻ መግለጫ የሰጡት ቶም ማሊኖዊስኪ “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት” እንደሆነ መናገራቸው የተደረሰና … [Read more...] about ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል
News
ዜና
በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
በጋምቤላ የአኙዋክ ተወላጆች ተጨፍጭፈውና ከመሬታቸው ተፈናቅለው “ለሰፋፊ እርሻ” በሚል ሲቸበቸብ ከነበረው መሬት “ወደ ሥራ የገባው” 15በመቶው ብቻ መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ አስታወቀ፡፡ ለ“እርሻ ልማት” በሚል 5ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቷል፡፡ የመሬት ካርታ “ከቢሮ ውጪ በመኖሪያ ቤቶችና በጫት ቤት ውስጥ” ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊ የነበረው ኢሳያስ ባህረ ከሥልጣኑ የተነሳው “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን በማድላቱ ነው” ተባለ፡፡ በጋምቤላ በደል ደረሰብን በማለት አቤቱታ ያሰሙ የትግራይ “ባለሃብቶች” ለሃይለማርያም የቀረበው ሪፖርት “የተዛባ ነው” አሉ፡፡ በጋምቤላ ይህ ነው የማይባል ግፍና የዘር ማጽዳት ተካሂዶ ከምስኪን ረዳተቢሶች የተነጠቀው መሬት ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡ ገና ከጅምሩ አሠራሩ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ ሪፖርቶች … [Read more...] about በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!
ዜናውን “መገጣጠም” ሲሉ በቁጭት ይገልጹታል። የትግራይ “ባለሃብቶች” በጋምቤላ መበደላቸውን ለውጭ አገርና ለአገር ውስጥ መገናኛዎች ያስታወቁበት ዕለትና የአኙዋክ ምስኪኖች በምድራቸው በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን ተሳሳመ። ደም እንደጎርፈ በፈሰሰበት፣ ንጹሃን እንደ እንስሳ የተቀሉብት ቀን ተዘንግቶ በሙታን ዱካ ተተክተው “ተበደልን” ያሉ የብሶት ዜና ተሰማበት - ታህሳስ 4፤ 2009 (ዲሴምበር 13 ቀን 2016)። ታህሳስ 3፤ 1996 ዓ.ም በጋምቤላ ለተጨፈጨፉት ንጹሃኖች ፍትህና ርትዕ የሚሰጥ አካል እስካሁን አልተገኘም። በስደት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና የተለያዩ አገራት የሚኖሩ የአኙዋክ ተወላጆች ያንን ቀን ሲያስቡት አሁን ድረስ ያነባሉ። በመለስ አመራር ሌሎች በፌዴራል መንግሥት ስም የሚታወቁ የህወሃት ሰዎች ትዕዛዝ ከ400 በላይ አኙዋኮች ተረሽነዋል። አሁን እነሱ አፈር ውስጥ ሆነው ደማቸው … [Read more...] about ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!
ተመስገን “ሰባት ስምንት ፖሊሶች” ከብበውት ወንድሙ አየው
ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ፡፡ ቤተሰቦቹ “ተመስገን ዝዋይ የለንም ተብለናል” ሲሉ አቤቱቻቸውን ለተለያዩ አካላት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬ ለጥቂት ደቂቃዎች ተመስገንን መመልከት እንደቻሉና ጤንነቱ መቃወሱን ተናግረዋል፡፡ በጻፋቸው እና ባሳተማቸው ጽሁፎች ክስ ቀርቦበት እና ተፈርዶበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት እስሩን እየገፋ ይገኝ የነበረው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደብዛ መጥፋት የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ፡፡ ከሰብዓዊ መብት ተቋማት እስከ ጋዜጠኛ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ለጉዳዩ አጽንኦት ሰጥተው መግለጫ እስከ ማውጣት እና በማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ እስከመክፈት ደርሰዋል፡ የተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች በዝዋይ ማረሚያ ቤት “ተመስገን እዚህ የለም” ተብለናል … [Read more...] about ተመስገን “ሰባት ስምንት ፖሊሶች” ከብበውት ወንድሙ አየው
ህወሃት “ተቃዋሚዎችን” በዓመት ሦስቴ ደጄን ከረገጣችሁ ይበቃችኋል አላቸው
በጥልቅ እየታደስኩ ነው የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በየቀኑ በጥልቅ መበስበሱን እና ለመታደስ ፈጽሞ የማይችል መሆኑን የሚመለክቱ ተግባራትን ሲፈጽም እየታየ ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆችን ወደኋላ በማድረግ ከመድረኩ በማውጣት የፊት ገጾች እንዲሆኑ ከትግራ ውጭ ያሉ ግለሰቦችን በማስቀመጥ ሥራውን በምክትሎቻቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲሠራ እደረገ ነው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ፣ አሳታፊ እሆናለሁ፣ … እያለ የፖለቲካ አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ኃይላትን ያስራል፤ ሕዝቡን ያሰቃያል፣ ይገድላል፡፡ አዲስ አድማስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው በውይይት እንዲሳተፉ ለማድረግ ማኑዋል እየተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ “ተቃዋሚዎች፤ ሳንመረጥ ፓርላማ አንገባም አሉ” በሚል ርዕስ የዘገበው እንዲህ ይነበባል፤ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው … [Read more...] about ህወሃት “ተቃዋሚዎችን” በዓመት ሦስቴ ደጄን ከረገጣችሁ ይበቃችኋል አላቸው
ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
አምልኮተ መለስ የተጠናወተውና የህወሃት አባል የሆነው ዛዲግ አብርሃ "የጥልቅ ተሃድሶ" ውጤት ተብሎ የተመደበው የነገሪ ሌንጮ ምክትል ሆኖ በሃይለማርያም ደሳለኝ መሾሙን Ethiopia Observer ዘግቦታል። ኦሮሞው ሌንጮ በአፈቀላጤነት በየሚዲያው ፊቱን ሲያስመታ የድርጅት ሥራውን የሚያከናውነው መለስን ማንነቴ ነው መንፈሴን ይቀሰቅሰዋል የሚለው ህወሃቱ ዛዲግ ይሆናል። ከዚህ በፊት ስለ መለስ የተናገረውን እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል። "ጥልቅ ተሃድሶ" በጥልቅ መበስበስ ይቀጥላል! ጎልጉል … [Read more...] about ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
“የነጭ ወያኔዎች” ሥልጣን መልቀቅና የተቀሩት “የዳግም ውልደት” ክህደት
የህወሃትና የአሜሪካ ፍቅር ቀደም ሲል ይወራ እንደነበረው “በመካከላቸው ንፋስ ገባ” ከሚባልበት ደረጃ ባለፈ እየሰለለ መምጣቱን የሚጠቁሙ እውነታዎች እየታዩ ነው። ራሱ ህወሃት ይህንኑ ፍትጊያ የሚያጎሉ ጉዳዮች እያከናወነ ይገኛል። ለልዩነቱ መክረር ፍንጭ እየታየ ነው። ከኦባማ ዘመን ማብቃት ጋር ተያይዞ የቀድሞ ወዳጆቹ የነበሩት “ነጭ ወያኔዎች” ሥልጣን መልቀቅ እውን ሊሆን ሲቃረብ የተቀሩት "በዳግም ውልደት" እየከዱት ነው የሚል መረጃ ሲነገር ይደመጣል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያወጣው መግለጫና ማሳሰቢያ ክብደቱ መጨመሩ፣ የአገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናትና ቁልፍ አማካሪዎች፣ እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያዎች ህወሃትን እያብጠለጠሉትና ክፉኛ እየነቀፉት ነው። ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ በውይይት ህወሃት “አደረጋለሁ” እያለ ማጨበርበሩ አሜሪካኖቹን … [Read more...] about “የነጭ ወያኔዎች” ሥልጣን መልቀቅና የተቀሩት “የዳግም ውልደት” ክህደት
የዶ/ር መረራ እስር፤ ህወሃትና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች
ከአውሮጳ ስብሰባ ወደአገራቸው ሲመለሱ የታፈኑትና በኋላ መታሰራቸው የተሰማው ዶ/ር መረራ ጉዲና የአሜሪካና የአውሮጳ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ጉዳይ የከረረ አቋም እንዲወስዱ እያደረጋቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ [ህወሃት] "ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አስተዳደር እያመራ" ሲሉ አንድ የአሜሪካ ሴናተር ተችተዋል፡፡ መታሰራቸውን እንደሰሙ “I am very upset with this” ያሉት የአውሮጳ ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ የዶ/ር መረራ እስር በጣም እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ ለስቃይና እንግልት እንደሚዳረጉ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም “በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በጣም ጥብቅ የሆኑ አካሄዶች ከአውሮጳ ኅብረት በኩል ሊደረግ ይገባል” የሚል ማሳሰቢም ሰጥተዋል፡፡ (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)፡፡ በመቀጠል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ይህንን መግለጫ አወጣ፤ “የኦሮሞ … [Read more...] about የዶ/ር መረራ እስር፤ ህወሃትና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች
ኮንሶ – የግፍ ምድር!
አንደኛዋ ባለቤታቸው ሶስት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጋለች። ሌላኛዋ ባለቤታቸው ከአንድ ልጇ ጋር ሁሉም እስር ላይ ናቸው። እመጫትም ከእርጥብ ልጇ ጋር ታስራለች። እነዚህ ማሳያ እንጂ በኮንሶ ከእስር የተረፉ ተሰደዋል። በወረዳው ያሉት 43 ትምህርት ቤቶች እስር ቤቶችና የወታደሮች ካምፕ ሆነዋል። ወደ አጎራባች ቀበሌ ወይም ጫካ የመሸጉ ሰዎች ህይወታቸውን የሚገፉት በመከራ ነው። ይህ ሁሉ ምሬት ሲሰማ ክልሉ ምንም ነገር እንደሌለ ነው የሚናገረው - ኮንሶ ግን ፍጹም ግፍ የሚፈጸምባት ሆናለች! ህዳር 27 ቀን 2016 ቪኦኤ ያናገራቸው ሁለት የኮንሶ ነዋሪዎች “ኮንሶዎች የሚኖሩት በሌላዋ ኢትዮጵያ ነው” ይላሉ። በኮንሶ መተንፈስ አይቻልም። መቃወም አይፈቀድም። ጥያቄ ማቅረብ ክልክል ነው። የሚማርበትን ዩኒቨርሲቲና የራሱን ስም ለጥንቃቄ ሲል በመደበቅ አጭር ቃለ ምልልስ ያደረገው የኮንሶ ተወላጅ … [Read more...] about ኮንሶ – የግፍ ምድር!
ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣ ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ … [Read more...] about ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?