“አህያ ሲጠፋ እህል ማን ሊሸከም ነው? ሴት?!” የአህያ ሥጋና ቆዳ ንግድ እንደ ህገወጡ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ እንዳይሆን ተሰግቷል “አህያ ልባችን ነው። አህያ ህልውናችን ነው። አህያ ቤተሰባችን ነው። አህያ ውለታውና ተግባሩ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ገዢዎቻችንም ቢሆኑ የአህያን ጥቅም በአግባቡ ያውቁታል። በበረሃ ሁሉን ችሎ እዚህ ያደረሳቸው አህያ ነው። እናም ጉዳዩ ከወሬ በላይ ነውና በሰከነ መልኩ ለማሰብ ፍላጎቱ ካለ ጊዜው ገናነው” ሲሉ የቱሉ ቦሎው ነዋሪ ይናገራሉ። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያናገራቸው የቱሉ ቦሎ ነዋሪ እህል ነጋዴ ናቸው። እንደ ምሳሌ የሚያነሱት ጉዳይ የሚደመደመው በጥያቄ ነው። እንዲህ ይላሉ “አህያ ሲመናመን ከገጠር ማን ተሸክሞ ወደ ገበያ ያመጣ? ያው የፈረደባት ሴት በወገቧ ልትሸከም?” ለወትሮው “ሴት፣ የሴቶች መብት፣ የሴቶች የህግ … [Read more...] about “ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች
News
ዜና
ተራዛሚው የኦሮሚያ ድርቅ እና ያዘለው አደጋ!
በኦሮሚያ በሦስት ዞኖች ብቻ 241 ት/ቤቶች ተዘግተዋል፤ 114,751 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! በቦረናና በጉጂ ዞኖች 127,010 ከብቶች በዘንድሮው ድርቅ ሞተዋል! ድርቅ ከፍ ሲልም ችጋርና ረሃብ ለኢትዮጵያ ተጠባቂ የስጋት ምንጭ ሆነው እንደቀጠሉ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ካሳለፍነው አስከፊ የርስ በርስ እና ከጐረቤት አገራት ጋር ከተደረጉ ጦርነቶች ጐን ለጐን ድርቅ፣ ችጋር፣ ረሃብ ሌላኛው የኢትዮጵያ አስከፊ የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በቀደሙት ጊዜያት በየአስር ዓመታት ልዩነት ኢትዮጵያን በሰፊው ይጐበኛት የነበረው ድርቅ፤ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት አገሪቱን ደጋግሞ ሲያጠቃና የከፋ ማኅበራዊ ቀውስ ሲያስከትል ታይቷል፡፡ በተራዛሚው ጦርነት ፍፃሜ ማግስት በአገሪቱ የተከሰተው የ1988 ዓም ድርቅ የአማራ፣ የሶማሌ፣ የአፋር እና … [Read more...] about ተራዛሚው የኦሮሚያ ድርቅ እና ያዘለው አደጋ!
የብአዴን መክዳትና የ“በቀል” ፍርሃት የወለደው “የኢኮኖሚ አብዮት” በኦሮሚያ፤
“ህወሃት የፈጸመው ግፍ በየትኛውም ዘመን የሚረሳ አይሆንም” በህወሃት ገደብ የለሽ የሥልጣን ፍቅርና የቁስ ሰቀቀን ውልቅልቋ እየወጣ ያለችው ኢትዮጵያ ከፍታው ርቋት የቁልቁለቱን ጉዞ ተያይዛዋለች። ለወጣበት ዘውግ ልዕልና የሚተጋው ህወሃት ህግና ሞራል በማይዳኘው ድርጅታዊ ቀኖናው እየተመራ ኢትዮጵያን ማድማቱን ቀጥሎበታል። እስር፣ ቶርቸር፣ ስቃይ፣ ስደት፣ ሞትና የግዞት ኑሮ ከህወሃት ዘውግ ጥላ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እድል ፈንታ ሆኗል። ከነዚህ በመከራ ከሚዳክረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል አንዱ የኦሮሞ ሕዝብ ነው። እውነታው ግን ሰፊና ለም የሆነ መሬት ላይ የሰፈረው የኦሮሞ ሕዝብ በቁመቱ ልክ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱ ሊከበርለት እንዳልቻለ ወራሪው ህወሃት ራሱ ለፖለቲካ ፍጆታም ቢሆን ያመነውና ማንም ሊከደው የማይችል የአደባባይ ሃቅ ነው። በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ … [Read more...] about የብአዴን መክዳትና የ“በቀል” ፍርሃት የወለደው “የኢኮኖሚ አብዮት” በኦሮሚያ፤
“ፋሲል ከነማ” – የትውልድ ዓመጽ አርማ!
“ቸቸላ” - በጎንደር የአማራ የልብ እሳት ማብረጃ ማማ!! ፋሲል ከነማ - ቶራ ቦራ! ማስታወሻ፤ ቶራ ቦራ አፍጋኒስታን ውስጥ ያለና ቢንላደን የሚደበቅባቸው ተራራዎችና የዋሻ ምሽጎች ናቸው። ፋሲል ከነማም የቶራ ቦራ ምሳሌ ነው። ቶራ ቦራ ብዙ ጊዜ ይደበደባል ግን ጉዳት አይደርስም። ቢደርስም ይህ ነው የሚባል አይደለም። ፋሲል ከነማም ምሽግ ነው! ቶራ ቦራ! በተቃራኒው ዱሮ ትልቅ የፖለቲካ ዋሻ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ቶራ ቦራነቱ ቀርቶ ሜዳ ሆኗል። ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭበት ግልብ ሜዳ! ሁሉም ባይሆኑም አስገራሚና ሊፋቅ የማይችል የምስረታ ታሪክ ያላቸው ክለቦች አሉን። አሁን አዲስ አበባ ስታዲየም የሚንከላወሱት ብቻ ሳይሆኑ በመላው አገሪቱ፣ በየሰፈሩ፣ በየከተማው ... ተቋቁመው የከሰሙት ክለቦች የምስረታ ታሪክ የሚያጠናው ቢገኝ ከቅሪላው ጀርባ ያለውን ጉዳይ … [Read more...] about “ፋሲል ከነማ” – የትውልድ ዓመጽ አርማ!
በህወሃት የታፈነው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ነው፤ ት/ቤቶች ተዘግተዋል!
የኢትዮጵያ ሶማሌ ዘጠኙም ዞኖች ሙሉ በሙሉ የድርቁ ሰለባ ሆነዋል! በክልሉ 437 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ተዘግተዋል፤ 183,090 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! የእርስበርስ ዕልቂት ያሰጋል! የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለት ወራት ውስጥ ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ምስራቅ አፍሪካ የከፋ ድርቅ መከሰቱንና ዓለም የዕርዳታ እጆቹን ለአገራቱ እንዲዘረጋ በተከታታይ ሪፖርቶቹ ተማጽኗል፡፡ እንደ በዘገባው ከሆነ ድርቁ የከፋባቸው ተጠቃሽ አገራት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሱት መንግሥታት ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት፤ በተባበሩት መንግሥታት በኩል የአውሮጳ ህብረትና ሌሎች ለጋሾች በከፋ ድርቅ ላይ ለሚገኙት አገራት ዕርዳታ እየሰጡ ናቸው፡፡ በተባበሩት መንግስታት … [Read more...] about በህወሃት የታፈነው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ነው፤ ት/ቤቶች ተዘግተዋል!
አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሦስት “ምኒልክ የእኛ ነው”
ከዝግጅት ክፍሉ:- “አድዋን የሚያህል ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?” በሚል ርዕስ ተከታታ ጽሁፎች ስናትም ሰንብተናል፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ሙሉ ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ እርግማን ሁለት “ሚኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ” የሚለው ሁለተኛው ክፍል ደግሞ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ በሦስተኛው ክፍል የመጨረሻውንና ማጠቃለያውን ይዘን ቀርበናል፡፡ አፄ ምኒልክ ባልዋለበት ማዋል የዘመናችን “ፖለቲከኞች” ከታሪክ የሚያገኙት ግብር - አልባ ትርፍ ሆኗል፡፡ የአፄውን አገር የማቅናትና የግዛት አንድነትን የማስከበር ዘመቻ በ“ቅኝ ግዛት” የሚተረጉሙት እንዳሉ ሁሉ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ ከትግራይ ወደ ሸዋ በመዞሩ ምኒልክን “ባንዳ” እና “አገር ሻጭ” እያሉ የአባቶቻቸውን ዝንፈት በአደባባይ ምኒልክ ላይ የሚለጥፉ ብልጣብልጥ “ፖለቲከኞች” … [Read more...] about አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሦስት “ምኒልክ የእኛ ነው”
የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”
የግፍ ክምር ናዳው ምን ያህል የሚከፋ ይሆን? አዲስ አበባ ቃላት የማይገልጹዋት፤ ስሟ ግብሯን የማይወክል የግፍ ከተማ ናት፡፡ በአንድ በኩል ሥጋ በል ለሆኑ የቤት እንሰሳዎቻቸው የዕለት ተዕለት ምግብ ከሱፐርማርኬት የታሸገ ሥጋ ገዝተው የሚመግቡ ባለጠጎች፤ በሚስታቸውና በልጆቻቸው እንዲሁም በደርዘን ውሽሞቻቸው ሥም የተንጣለሉ ቪላ ቤቶችንና ግዙፍ ህንፃዎችን የገነቡ የገዥው ኃይል ማኅበራዊ መሰረት የሆኑ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ የከተማ ዘራፊዎች (Marauders’ city) “ወጋ ትበለይኪ” እያሉ የሚምነሸነሹባት፤ ደሃ-ገፊ መሐል አሟቂ፤ የቁስ ሰቀቀን የተጫናቸው የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ዘዋሪ ልሒቃን ከተማ ናት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዕለት ምግባቸውን ከቆሻሻ ገንዳ የሚለቅሙ አንጀታቸው በረሃብ የታጠፈ ጐስቋላ ምንዱባን በጐዳና የሚኖሩባት፤ የወር ደመወዛቸውን ለአልቦ-አንጀት (ርህራሄ የለሽ!) … [Read more...] about የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”
አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሁለት: “ምኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ”
ከዝግጅት ክፍሉ:- "አድዋን የሚያህል ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?" በሚል ርዕስ የመጀመሪያውን ክፍል ማቅረባችን ይታወሳል፤ ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህኛው ክፍል ሁለት ዕትም እርግማን ሁለት “ሚኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ” የሚለው ርዕስ ዳሰናል፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊነት ታሪክ ተፃሪሪ ትርጓሜና የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ምስረታ ሂደት የተመዘዙ መንታ ሰበዝ ናቸው፡፡ “ቅኝ ግዛት” vs “አገር ምስረታ፣ ማቅናት/ግንባታ” የሚሉ ተፃራኒ ትርጓሜዎች እንዳሉ ሁሉ፤ “አገር ሻጭ” እና “ባንዳ” የሚሉ የፖለቲካ እርግማኖች የዘመናዊት የኢትዮጵያ የታሪክ ገጽታ አካል ሆነው ቀርበዋል፡፡ ማንነትን የታከከ የታሪክ ትርጓሜ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ብያኔዎች ሊጠፉ የማይችሉ የታሪክ ፍም እሳቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ በገዥዉ ኃይል ፊት … [Read more...] about አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሁለት: “ምኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ”
አድዋን የመሰለ ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?
እንደ መግቢያ በታወቀ ምክንያት የኢትዮጵያ ታሪክ አወዛጋቢነት ቀጥሏል፡፡ “ታሪክ የሞተ ፖለቲካ ነው” የሚለው አባባል ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን አይሰራም፡፡ ይልቁንስ “ታሪክ የነበረ፣ ያለና ወደፊትም ሊቀጥል የሚችል ፖለቲካ ነው” በስሜት በሚነዳ የዘውግ (የዘር፣ የጎሣ) ፖለቲካ ውስጥ ታሪክ ትልቅ ማገዶ ሆኖ ቀርቧል፡፡ እንዲህ ባሉ የታሪክ ውርክቦች ውስጥ ይበልጥ አትራፊው ገዥዉ ኃይል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ታሪክ የአሸናፊዎች ደንገ-ጡር በሆነችባት ኢትዮጵያ ገዥው ኃይል ለአገዛዙ በሚያመቸው መልኩ ታሪክን በርዞና ከልሶ ሲያቀርብ ታሪክን ሳያላምጡ የሚመጡ ደቃቅ “ፖለቲከኞች” በርክተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ አተራረክ በአጥቂነትና በተከላካይነት የሚበየን የውዝግብ መድረክ ሆኗል፡፡ የአንድ ዘውግ ጉዳይን ሁልግዜ በተጠቂ ስሜት፤ ሌላኛውን ዘውግ በአጥቂነት የማየት ዝንባሌም በታሪክ … [Read more...] about አድዋን የመሰለ ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?
የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤
የህወሓት-እስራኤል ቀጣይ የፖለቲካ ቁማር! አሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለህወሓት/ኢህአዴግ ቁልፍ የስጋት ምንጩ የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ጎራ ነዉ፡፡ የድህረ-ምርጫ 97 ዉርስ ዕዳ የሆነዉ የዲያስፖራዉ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንደ ሀገር ቤቱ ሁሉ በዘዉግ ፖለቲካ የሚታመስ ቢሆንም በጋራ ጠላት (ህወሓት/ኢህአዴግ) መዉደቅ ላይ ያለ አንዳች የልዩነት መስመር ይስማማል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሀገር ቤት ያሉት የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከሚያሰሙት ጩኅት በላይ ከባህር ማዶ የሚሰማዉ ሹክሹክታ እንቅልፍ ይነሳዋል፡፡ የህዝብ ድምጽና የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ መሳ ለመሳ መሄድ የቆላ ቁስል ሆኖበታል፡፡ እናም የዲፕሎማሲ ታርጋን እንደ ሴራ ፖለቲካና ድርጅታዊ ጠቀሜታነት አብዝቶ ለመጠቀም የጨዋታዉን ህግ ያሻሻለ ይመስላል፡፡ የዲያስፖራ ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማይካድ ደረጃ … [Read more...] about የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤