እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም "እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ። "አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም" የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ። በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው … [Read more...] about ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!
News
ዜና
ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?
ላለፉት 5 ዓመታት ያህል ከልጆቿና ባለቤቷ ተለይታ በእስር ስትማቅቅ የነበረችው ሌሊሴ ወዳጆ መፈታቷ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስደሰቱ ተጠቆመ፡፡ የጋዜጠኛ ሌሊሴን መፈታት አስመልክቶ Ayyaantuu News Online ለንባብ ባበቃው ዜና እንዳመለከተው በስደት አውስትራሊያ ከሚኖረው ከባለቤቷና ከልጆቿ ጋር ተቀላቅላለች፤ ድረገጹ ዜናውን በምስል በማስደገፍም አቅርቦታል፡፡ በጋዜጠኝነት ሲያገለግል የነበረው ባለቤቷ ዳቢሣ ዋቅጂራ አገር ጥሎ መሰደዱን ተከትሎ በማታውቀው ምክንያት የኦነግ አባል ነሽ በማለት ኢህአዴግ 10ዓመት ያለ አመክሮ ፈርዶ ወኽኒ እንዳወረዳት ይታወሳል፡፡ ይህንን ህዝብን ያበሳጨና ያስቆጣ ጉዳይ ሌሊሴ ከታሰረችበት ጊዜ ጀምሮ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ጥበቃ ድርጅት (CPJ) ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲያወግዙትና እንድትፈታ ሲሟገቱ መቆየታቸው … [Read more...] about ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?
ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”
''የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል" በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ። በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት … [Read more...] about ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”
ከእሁድ እስከ እሁድ
መንግስት በምእራብ አርሲ ዞን የተገደሉትን ሙስሊሞች ቁጥር መቀነሱን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ በምእራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አካባቢዋ የፌደራል ፖሊሶች በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸውና 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የኦሮምያን ፖሊስ በመጥቀስ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቢዘግቡም የኢሳት ምንጮች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ18 እስከ 25 ይደርሳል ይላሉ። በአካባቢው የሚገኝ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሟቾችን ቁጥር 18 መሆኑን ሲገልጽ፣ ወደ ኮፈሌ እና ዋቢ ከተሞች ለመግባት ሙከራ አድርጎ በፖሊሶች ፍተሻ ተንገላቶ ሳይሳካለት የቀረው ዘጋቢያችን ከከተሞች ሲወጡ ያገኛቸውን ሰዎች አነጋግሮ እንዘገበው የሟቾች ቁጥር ከ15 እስከ 20 ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል። መንግስት ሙስሊሞቹ የጦር መሳሪያዎችን እንደያዙ አድርጎ ያቀረበው ዘገባ ትክክል አለመሆኑና … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም
ባለፈው ዓርብ በመላው አገሪቱ አንድ ወጥ የ"ድምጻችን ይሰማ" የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት የወጣውን መርሃ ግብር ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ እስከ ግድያ ሊደርስ የሚችል ርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የሚያመላክት መግለጫ አውጥቶ ነበር። የድምጻችን ይሰማ አመራር መሆናቸውን የሚገልጹት ክፍሎች ፌደራል ፖሊስ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ተቃውሞው እንዲቀር መመሪያ ማስተላለፋቸውን ይናገራሉ። በዋቤ መስጊድ ቦንብ ያፈነዳው ማን ነው? ለምን እንዲፈነዳ ተደረገ? ፖሊስ በከረሩ ቃላቶችና በማስጠንቀቂያ አጅቦ ባወጣው መግለጫ " … አክራሪ ወሃቢ ሰለፊዎች ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረጉ ፖሊስ ለሚወስደው ርምጃ ተገቢውንና የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን" በማለት አስፈራርቶ ነበር። "ምንደኛ፣ ከውጪ በሚላክላቸው ንዋይ ዓይናቸው ታውሮ አርብ በመጣ ቁጥር በተመረጡ መስጊዶች … [Read more...] about በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም
እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር "… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል። "ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ" በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ … [Read more...] about እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!
የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡ “ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) … [Read more...] about ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!
በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ተጠርጣሪዎቹ ሽፈራው ጃርሶ የሚመሩት ቦርድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ናቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ከእነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች 15 የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ፍለጋ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥና የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ ባልተከተለ መንገድ ኪራይ ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን፣ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባካሄደው ጥናታዊ ምርመራ በዚህ የሙስና ወንጀል መንግሥትን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዳሳጣው ለጉዳዩ ቅርበት የኮሚሽኑ ምንጮች … [Read more...] about በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
አጠገብ ያሉ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ እንዲለቁ ተነገራቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ለማድረግ ስምምነት ሊያደርግ ነው በግዙፉ የጀሞ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች መንደር ውስጥ በአንድ በኩል በመስመጥ ላይ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሕንፃ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሕንፃው እንዲለቁ ተነገራቸው፡፡ በሁለቱ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሕንፃዎቹ እንዲለቁ የተጠየቁት በክፍለ ከተማው የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት አማካይነት መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የውሳኔው መነሻ ወደ አንድ ጐን በማዘንበል ላይ የሚገኘው ሕንፃ አጠገብ ያሉት ሁለት ሕንፃዎች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው በሚል ቢሆንም፣ በሕንፃዎቹ ላይ በዓይን የሚታይ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ሕንፃዎች ተመሳሳይ መሰነጣጠቅ በውስጥ አካላቸው … [Read more...] about ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!
ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ረቡዕ ለት በጭንቅ እንዲያርፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ አደጋው ከአምስት ደቂቃ በፊት ቢከሰት ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡ 78 መንገደኞችንና ሠራተኞችን አሣፍሮ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Bombardier Q400) አውሮፕላን ከክንፎቹ በአንዱ ጭስ መነሣቱን የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ በመደወሉ እጅግ አስጨናቂ በሆነ መልኩ እንዲያርፍ መደረጉን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው ስማቸው ከመግለጽ የተቆጠቡ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደጻፈው አውሮፕላኑ ከማረፉ ከአንድ ደቂቃ በፊት የግራው ክንፍ እየጨሰ መሆኑን ማስጠንቀቂያው ማመልከቱንና አንዱ ሞተር ደግሞ እንደሚገባው ይሰራ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በስልክ ያነጋገራቸው ተሳፋሪ ጭስ … [Read more...] about በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!