አስራ ሦስት ዓመት ባልሞላው ሕፃን ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ፈፅሟል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተበት የ23 ዓመቱ ወጣት ሳሙኤል መርዕድ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ20 ዓመት እሥራት እንዲቀጣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ ታህሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈበት። ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎት በየካቲት 06 ቀን 2006 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ላይ እንደዘረዘረው፤ የ23 ዓመቱ ወጣት ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ፆታ ባለውና ዕድሜው ከ13 ዓመት በታች በሆነው ታዳጊ ልጅ ላይ የግብረ-ሰዶም ጥቃት ለማድረስ አስቦ ተንቀሳቅሷል ይላል። በዚህም መሠረት በጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02/03 ክልል ልዩ ቦታው ጌሾ ተራ ተብሎ … [Read more...] about በ5 ዓመቱ ሕፃን ላይ የግብረ-ሰዶም ጥቃት የፈፀመው በ20 ዓመት እሥራት ተቀጣ
News
ዜና
ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ!
በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡ አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡ ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት … [Read more...] about ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ!
ሃናን በመድፈር የተጠረጠሩት ክስ ተመሰረተባቸው
በ16 ዓመቷ ታዳጊ ሃና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀም ለሞት አብቅተዋታል በተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተባቸው። ዐቃቤ ሕግ ትናንት ማክሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ሁለት ሲሆን፤ ለአካለመጠን ያልደረሰችን ሴት በአሰቃቂ ሁኔታ መድፈር እና ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የሚሉት ክሶች ተጠቅሶባቸዋል። ከትናንት በስቲያ ሜክሲኮ በሚገኘው በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የነበረውን የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ያጠናቀቀው ይህ ጉዳይ ከዚህ በኋላም በልደታ ፍርድ ቤት መታየቱን ይቀጥላል። በመሆኑም በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰው አምስቱ ተጠርጣሪዎች 1ኛ ተከሳሽ ሳምሶን ስለሺ ሙያ ሹፌር፣ 2ኛ ተከሳሽ በዛብህ ገ/ማርያም ሾፌር፣ 3ኛ ተከሳሽ በቃሉ ገ/መድህን … [Read more...] about ሃናን በመድፈር የተጠረጠሩት ክስ ተመሰረተባቸው
መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን አካሄደ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እሁድ ዕለት ያቀደውን ሰላማዊ ሠልፍ በ37 መፈክሮች በማጀብ አካሂዶዋል፡፡ አብዛኛዎቹ መፈክሮች ምርጫን፣ ምርጫ ቦርድን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁኔታን፣ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች መቆራረጥና መንግሥትን ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲወጣ የሚጠይቁ ነበር፡፡ ከመፈክሮቹ መካከልም "ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፖጋንዳ፣ በኃይልና በተፅዕኖ አይገነባም"፣ "የአገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል ዕርምጃ አይፈቱም"፣ "ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር ይካሄድ"፣ ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ተካተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕዝቡ በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ … [Read more...] about መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን አካሄደ
አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!
* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት” ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡ “አገር … [Read more...] about አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!
ዓይን አጥፊው የዓይን “ማከሚያ ቤት”
* “ብዙ ብር ከፍለን የዓይን ብርሃናችንን አጥተን ተመልሰናል” - ታካሚዎች * ከመነሻው የማዕከሉ አደረጃጀት አዋጁን የሚቃረን ነው - የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ * ማዕከሉ በየዓመቱ የሚታደስ የህክምና አገልግሎት ፈቃድ አልተሰጠውም ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የተሻለ የአይን ህክምና ለመስጠት፣ ለኢትዮጵያውያን ሀኪሞች የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርግና በዘርፉ ምርምርና ጥናት እንዲያካሂድ ታስቦ በዘውዲቱ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የተገነባው የህንድ የአይን ህክምና ማዕከል በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ታካሚዎች እንደተናገሩት በማዕከሉ በተሰጣቸው ህክምና ሳቢያ የዓይን ብርሃናቸውን አጥተዋል፡፡ በማዕከሉ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ፣ በዘርፉ በቂ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎችና ደረጃውን የጠበቀ … [Read more...] about ዓይን አጥፊው የዓይን “ማከሚያ ቤት”
ልማታዊ ሙስና?
ባለፈው ዓርብ በተከፈተው የመሬት ሊዝ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ቀረበ፡፡ ይህ ዋጋ በከተማው ታሪክ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሊዝ ጨረታን የወቅቱ አነጋጋሪ ክስተት አድርጓል፡፡ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ አካባቢ 449 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ በካሬ ሜትር የቀረበው ገንዘብ ሲሰላ ይህ አነስተኛ ቦታ 136.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሆኗል፡፡ 20 በመቶ ብቻ የተከፈለበት ይህ መሬት ከነወለዱ እስከ 300 ሚሊዮን ብር በ30 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክስተት ለአዲስ አበባ ሊዝ ሥሪት ባለሙያዎች እንዲሁም በጨረታው ለታደሙ ባለሀብቶች የቀረበው ዋጋ ብዥታን ፈጥሯል፡፡ በጨረታው ላይ ሁለተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋም ከዚህ ቀደም ቀርቦ የማያውቅ ሲሆን፣ የቀረበውም በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ነው፡፡ "በአዲስ አበባ የሊዝ ዋጋ … [Read more...] about ልማታዊ ሙስና?
በአዳር ሰልፉ ኢህአዴግ “ተሸብሯል”
* የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ * የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡ አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ “መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!” ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል … [Read more...] about በአዳር ሰልፉ ኢህአዴግ “ተሸብሯል”
የጣሊያን ፖሊስ ሰዉ አስተላላፊዎችን ያዘ
የጣሊያን ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንግድ ወደ አዉሮጳ ያሸጋግራሉ በማለት የተጠረጠሩ 10 የኤርትራ ተወላጆችን በቁጥጥር ሥር አዋለ። የካታኒያ-ሲሲሊ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ የሚያሸጋግር ሕብረ-ሐገራት መረብ መኖሩን የሚጠቁም መረጃ ከደረሰዉ በኋላ ባደረገዉ አሰሳ ነዉ። በፖሊስ መግለጫ መሠረት ስደተኞቹን የሚያሻግረዉ መረብ ኤርትራ፤ ሊቢያ፤ ሌሎች ሰሜን አፍሪቃ ሐገራት እና ኢጣሊያ ድረስ የተዘረጋ ነዉ። ለአሸገጋሪዎቹ ገንዘብ እየከፈሉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ በርካታ ስደተኞች ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ እየሰመጡ ሞተዋል። ፖሊስ ሰሞኑን የያዛቸዉን ተጠርጣሪ አሸጋጋሪዎች ካለፈዉ ግንቦት እስከ መስከረም ድረስ 23 የባሕር ላይ ጉዞዎችን አቀነባብረዋል በማለት ከሷቸዋል። ከተጓዦቹ ቢያንስ 240 ስደተኞች ሞተዋል። ከአስሩ ተጠርጣሪዎች ዘጠኙ ኅዳር 16 … [Read more...] about የጣሊያን ፖሊስ ሰዉ አስተላላፊዎችን ያዘ
በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው ክስ ተሰማ
በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ከትላንት በስቲያ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ በጠበቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ … [Read more...] about በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው ክስ ተሰማ