“የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንደደረሱ ቢያጠፉ ሆቴሉን ማትረፍ ይቻል ነበር” የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰ፡፡ “በተደወለልን በሁለት ደቂቃ ውስጥ ደርሰናል፤ (የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን) 113 ሠራተኞች በ12 ተሽከርካሪዎችና በአምስት አምቡላንሶች ታግዘው፣ 236,300 ሊትር ውኃና 500 ሊትር ፎም በመርጨት ቃጠሎውን መቆጣጠር (ችለዋል)” አቶ ሰለሞን መኰንን የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ፡፡ “በፍጹም በሁለት ደቂቃ አልደረሱም፤ በሁለት ደቂቃ ወይም በሌላ ማለቱን ትተው በደረሱበት ወቅት ማጥፋት ቢጀምሩ ኖሮ፣ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሕንፃ ሳይዛመት ጃዝ አምባ ላውንጅ ላይ እያለ ማጥፋት ይችሉ ነበር፡፡ ስልካቸው አልሠራ በማለቱ በመኪና እዚያው ድረስ ተሄዶ እንደተነገራቸውና ነጋሪው መጥቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደርሰዋል፡፡ እንደደረሱም … [Read more...] about የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?
News
ዜና
ኢህአዴግ የምርጫው ስጋቱ አይሏል
* ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል የአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ የስልጠናው ዋና አላማ በቀጣዩ ምርጫ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራውን አመጽ መቆጣጠር እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ ምንጮች በተለይ ፖሊስና ፀጥታ ጉዳይ ከ“ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ” ጋር በመተባበር የደፈጣ ውጊያን ለመከላከል “የደፈጣ ውጊያ ስምሪት” በሚል አጭር ስልጠና እየወሰዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም … [Read more...] about ኢህአዴግ የምርጫው ስጋቱ አይሏል
የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት
ወይዘሪት ወይንሸት፣ ንፋስ ስልክ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች ከረፋዱ 5፡30 ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባት ለፍኖተ-ነፃነት የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡ ወይዘሪት ወይንሸት፣ ነፍሰጡር መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ደብዳቢዎቹም ሆዷን በመርገጥ ድብደባውን ሲፈፅሙባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብዳቢዎቹ ድብደባውን ፈፅመው የተሰወሩ ሲሆን ወይዘሪት ወይንሸት፣ በአሁኑ ሰዓት ራሷን ስታ ሆስፒታል መግባቷን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ወይንሸት፣ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ድምፅ የአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆና በመመረጥ በምርጫው ላይ ጉልህ ሚና በመጫወት ድርሻዋን መወጣቷ ይታወሳል፡፡ በእለቱ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአንድነት ስም የሚነግዱትን ግለሰቦች በማውገዝ አስተያየቷን መሰንዘሯን ተከትሎ ድብደባው ሊፈፀምባት እንደተቻለ … [Read more...] about የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት
ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው
ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን "የምርጫ ግብረ ኃይል" በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን "አልወስድም ስትል ፈርም" እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ "የምርጫ ግብረ ኃይል" በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን … [Read more...] about ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው
“ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ መደምሰስ ነው”
“ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ሰዎች ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ በመደምሰስ ነው” የሚለው የእንስሶች እርሻ ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ብሒል ሰሞኑን ከፍተኛ መነጋሪያ ሆኗል፡፡ ለዚሁም መነሻው በየተራ እንዲወድሙ ከተደረጉት የሕዝብ የማንነት መገለጫዎች መካከል አንደኛ ቅርስ የሆነው የጣይቱ ሆቴል መውደምን ተከትሎ ነው፡፡ የእንስሶች እርሻ መጽሐፍ ህወሃት በተሰነጠቀበት ወቅት የእነ መለስ መገለጫ ነው ተብሎ በስፋት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲነበብ የነበረ መጽሐፍ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የውኅዳኑ ደጋፊ ሪፖርተርም በየሳምንቱ እየተረጎመ ያቀርበው እንደነበር ጋዜጣው ምስክር ነው፡፡ ጋሼ ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው “አጤ ምኒልክ” መፅሐፍ ገጽ 328-330 የሆቴሉ ታሪክ እንዲህ ይነበባል፡፡ በአዲስ አበባ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ተሠርታ በምትመረቅበት ጊዜ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ … [Read more...] about “ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ መደምሰስ ነው”
ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ
የቀድሞው የጋንቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸው ታስሮ ጨለማ ክፍል መታሰራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አቶ ኦኬሎ ቂሊንጦ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በእስር በሚገኙበት እስር ቤት እጅና እግራቸውን ታስረው ብቻቸውን ጨለማ ክፍል እንዲገቡ እንደተደረጉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ቂሊጦ ማረሚያ ቤት እስረኞችን ሊጠይቁ ሄደው እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ እዚያው በእስር ላይ ካሉ ሰዎች አቶ ኦኬሎ ያሉበትን ሁኔታ መረዳታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል የ18 አመት እስር ፍርደኛው ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ሌላ ሰው መጠየቅ እንደተከለከለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ) … [Read more...] about ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ
“ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ
በተለይ ምርጫ ሲደርስ ቀለማዊ ነክ ነገሮችን በጣም የሚያስፈራው ህወሃት/ኢህአዴግ በመጪው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ሰማያዊ ቀለም እንዳይታይ መከልከል መጀመሩ ተዘግቧል፡፡ የደኅንነትና የፖሊስ አባላቱን በማሰማራት በግልጽ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ያለው ኢህአዴግ ለዘመናት በቆየው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የጨመረው ባለ ሰማያዊ መደብ ኮከብ በበዓሉ ላይ እንዳይታይ አብሮ ካልከለከለ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማነት የሰየመውን የኢህአዴግ ዓርማ መቀየር አለበት በማለት አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡ በሰማያዊ መደብ ቢጫ ኮከብ ያለውን የኢህአዴግ ዓርማ በቲሸርት በማሰራት “ለኢህአዴግዬ ያልሆነ … ይበጣጠስ” በማለት “አምረውና ደምቀው” በበዓሉ ለመታየት ያሰቡ ካድሬዎቹና አፈቀላጤዎቹም በዚህ ጉዳይ ላይ አመራር ካልተሰጣቸው “ከኑግ የተገኘ …” የመሆን ዕጣ እንዳይደርሳቸው “ያስፈራል” ተብሏል፡፡ ጉዳዩ … [Read more...] about “ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ
“ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ
የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት የገለፀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ በጉዳዩ ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡ መድረኩ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ ምርጫውን ለማስፈፀምና ለመታዘብ ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ገለልተኛ የሆኑ ሠዎች መመረጥ ያለባቸው ቢሆንም በቅርቡ የተመረጡት አስፈፃሚዎች አብዛኞቹ የገዥው ፓርቲ አባላት መሆናቸው እየታወቀ “የማንም ፓርቲ አባላት አይደለንም” እያሉ ፈርመው ወደ አስፈፃሚነቱ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ሲል ፓርቲው ቅሬታውን ገልጿል፡፡ መንግስት ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጐማ በተመለከተም ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ፓርቲዎች ብቻ … [Read more...] about “ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ
“እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
ከቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አብርሃ ደስታና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ኦኬሎ አኳይ፣ ስለ እስራቸው ሁኔታ እንዲህ ይላሉ:: በቅድሚያ አብርሃ ደስታ:- "እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡ "ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ "እኔ እስር ቤት እንድገኝ … [Read more...] about “እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
ለጠ/ሚ/ሩ ጥሪ – የኦባንግ ጥሪ
“ዕርቅ ብቸኛ አማራጭ ነው” በሚል እምነታቸው ሁሉንም ወገኖች ነጻ ለሚያወጣ ትግል ራሳቸውን የሰጡት ኦባንግ ሜቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ የመልስ ጥሪ አሰሙ፡፡ ከአቶ ሃይለማርያም የሰሙትን የእንነጋገር ጥሪ በአዎንታዊነቱ ተመልክተውታል፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ይህንን የተናገሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ያቀረቡትን “ለጋራ አገራችን በጋራ እንወያይ የሚል ጥሪ ማቅረብ ግን እፈልጋለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር በተናጠል መወያየት አንደማይቻል የገለጹት ሃይለማርያም፤ በሦስት ደረጃዎች የመደቧቸውን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ባወገዙበት መግለጫቸው ማገባደጃ ላይ የእንነጋገር ጥሪ አሰምተዋል፡፡ በግልጽ ተለይቶ ያልቀረበው የእንነጋገር ጥሪ ለአኢጋን … [Read more...] about ለጠ/ሚ/ሩ ጥሪ – የኦባንግ ጥሪ