ባለፈው ሳምንት ከ21/01/2014 ዓ.ም እስከ 27/01/2014 ዓ.ም ድረስ ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፣ የገቢ ኮንትሮባንድ 43 ሚሊዮን 12ሺ 009 ብር፤ ወጪ ደግሞ 1ሚሊዮን 437ሺ 851ብር፣ በድምሩ የ44ሚሊዮን 449ሺ 860ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡
አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሊያዙ ችለዋል፡፡
ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
“እንደሁልጊዜው ህብረተሰባችን፣ የክልልና የፌደራል የጸጥታ አካላት እንዲሁም ሰራተኞቻችን ኮንትሮባንድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላበረከታችሁ እያመሰገንን ወደፊትም አብራችሁን እንድትሆኑ እንጠይቃለን” ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply