• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል!

March 2, 2020 11:24 am by Editor 1 Comment

ስለ ዓድዋ ጦርነት አንዳንድ እውነታዎች❗️

ቀን: የካቲት 23, 1888
ቦታ: አድዋ፤ ኢትዮጵያ
አሸናፊው ሀይል: ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
አጤ ምኒልክ
እቴጌ ጣይቱ
ተክለ ሀይማኖት
ራስ መኮንን
ራስ ሚካኤል
ራስ መንገሻ
ፊታውራሪ ገበየሁ
ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ
ፊታውራሪ ዳምጠው
ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ
ኒኮላ ሊዮንቴቭ

በጣልያን በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
ኦሬስቴ ባራቴሪ
ቪቶሪዮ ዳቦርሚዳ
ጁሴፔ አሪሞንዲ
ማቲዎ አልቤርቶኒ
ጁሴፔ ኤሊና

በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
80,0000 መሳርያ የታጠቅ
20,000 ጦርና ጎራዴ የታጠቀ
8,600 ፈረሰኛ

በጣልያን በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
24,804 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቅ ወታደር
56 ረጅም ርቀት ተወርዋሪ መሳርያዎች

በኢትዮጵያ በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
3867 የሞቱ
ከ8000 በላይ የቆሰሉ

በጣልያን በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
6394 የሞቱ
1428 የቆሰሉ
ከ3000 በላይ የተማረኩ

© መልካም 74 Radio

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    March 2, 2020 04:09 pm at 4:09 pm

    የዛሬን አያርገውና የአድዋ ድል ለመላው ጥቁር ህዝብ የድል ጮራ እንደሆነ በየትምህርት ቤቱ እንማር ነበር። አስታውሳለሁ አንድ ጊዜ በአንድ ትምህርት ቤት ግርማ ፍስሃ የተባለ የጀርመን ኗሪ አባቱን ሊጠይቅ ብቅ ይላል። ጊዜው ክረምት ነበረ። እኛም ተማሪዎች የክረትም ትምህርት እንድንማር (ሃገርህን እወቅ) አይነት ነገር ደ/ች መንገሻ ይልማ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተኮልኩለናል። ሰብሰብ ብለን በኦሮምኛ እየዘፈንን ስንቀላለድ ደወል ተደወለና ገባን። በቀኑ ግርማ ፍስሃ ተጋባዥ አስተማሪ ነበር። ሰላም ልጆች በማለት ራሱ ካስተዋወቀ በህዋላ ለዛሬ የማስተምራችሁ “አርሙኝ” ከተሰኘ መጽሃፍ ውስጥ ” አልሞትም ብዬ አልዋሽም የተሰኘውን ታሪክ በማንበብ እጀምራለሁ በማለት የአቶ ተማቹንና የወ/ሮ ጽጌረዳን በጣሊያን ወረራ ጀግንነት ማንበብ ጀመረ። በማህሉ ሲቃ ያዘውና ማልቀስ ጀመረ። ክፍሉም ሁሉ አብሮት አለቀሰ። ያ ጊዜ እንደ አሁኑ በዘር ዙሪያ ሰው ያልተሰፈረበት ሁሉም በሰላምና በህብረት የሚኖርበት የመልክዓ ምድር የመማሪያ መጽሃፋችን አርዕስት “አብሮ መኖር በዓለም ዙሪይ” የሚል እንደነበር ትውስ ይለኛል።
    ወደ ዛሬው የዘር ፓለቲካ ስንመለስ ደግሞ ሌቦች ጀግና የሚባሉበት፤ ወንድም እና እህቱን ገድሎ ሰው የሚፎክርበት፤ ለዘሬ፤ ለጎሳዬ፤ ለክልሌ በማለት ሰው ሁሉ በየጎራው የሚፎልልባት፤ በብሄር ነጻነት ስም ባርነት ውስጥ የምንኖርበት በጥቅሉ የደንበር ገተር ጊዜ ላይ እንገኛለን። አድዋ ከሃገሪቱ አራት ማዕዘናት ሃበሾች ተጠራርተው ጠላትን ያሳፈሩበት የድል ጎራ ናት። የአድዋው ድል የጋራ ድል ነበር ነውም። ሼሁ ከመስጊድ፤ ቄሲ ከመንበሩ፤ ገበሬው ከእርሻው፤ ነጋዴውና ሌላውም ተጠራርተው የነጭ መንጋን ያሳፈሩበት የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ጮራ! ታሪክን ሰርተው በታሪክ ውስጥ ያለፉ ጀግኖች ደምና አጥንት ዛሬም በአድዋ ሸለቆና ተራራዎች ይጣራል፤ ይናገራል። የሚሰማ ግን የለም። የክልል ፓለቲካ ያሰከረው የእብድ ክምችት ያፈራች ሃገር። ሲያሳዝን! በአዲስ አበባ ለሰላም ገቡ የተባሉ ጠበንጃ አንጋችና አፋዊ ፓለቲከኞች በለመድት የፓለቲካ የሾኬ ጠለፋ ሰውን ያተራምሳሉ። መማር ማለት እንዲህ ነው። ነጻ እናወጣሃለን የሚባለውን ሰው እሳት ውስጥ እየገፉ መክተት። ዶ/ር አብይም እየቆ መንግሥቱንና አቶ መለስን ለመምሰል ጥቂት ጊዜ የቀረው ይመስላል። በቅርቡ ከብዙ ውጣ ውረድ በህዋላ አንድ የደረስኩበትን መረጃ አልባ የሆነ የራሴን አስተያየት ልስጥ። ሁልጊዜ ኢንጂኒየር ስመኘውን ማን ገደለው በማለት እጠይቅ ነበር። መልሱ ጠ/ሚሩ ናቸው። እንዴት ለሚል። ባፋቸው። ግድቡን በጊዜው ሄደው ከጎበኙ በህዋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እጠቅሳለሁ ” ግድቡ በአስር ዓመት ጊዜም አያልቅ” ይህ ይፋዊና ፌዚያዊ ንግግር ኢንጂኒየሩን ጎድቶታል። በዚህም የተነሳ ራሱን ለማጥፋት ተገዷል። የእኔ ድምዳሜ እሱ ነው። አብይ የማያውቀው የእውቀት ሚዛን የለም። መለፍለፍ ልምድ አድርጎታል። ቃልም ተግባርም በሚዛን ሲሆን መልካም ነው። እንዲሁ ራስን እንደ (chameleon ) ከከባቢ ጋር እየለዋወጡ ቢዘላብድት ዋጋ የለውም። የሚገርመኝ ነገር ባለስልጣኖች እየቆዪ የንጉስ አይነት መልክና ባህሪን ይላበሳሉ። መታመም ነው። ንጉስ ድሮ ቀረ። ይህን አስቀድመው ያዪት እውቁ የወረሂመኖው ሸህ ሁሴን ጅብሪል እንዲህ ብለው ነበር።
    ያምናን ቀን አማሁት ላፌ ለከት የለው፤
    የዘንድሮው መጣ እጅ እግር የሌለው፤
    ቀን ይወጣል ብየ ብጠብቅ ባስጠብቅ፤
    እንኳን ቀን ሊወጣ ጨለማ ነው ጥቅጥቅ፡፡
    ይህ ግጥም የሚያሳየው ትሻልን ትቼ ትብስን እንዲሉ አይነት ነው። ብቻ የጋራ የሆነ ድላችንን እያንቋሸሽን የአንድ ቀን አውሎ ንፋስ የሚደረምሰውን የክልልና የቋንቋ አጥር ስንገነባ ኖረናል ተብለን አፈር ይመለስብናል። አታድርስ ነው። ድንበር ተሻጋሪ ሥራ ከመስራት ላስን አጥቦና አሳንሶ መሞት! እንትፍ ይቅርብኝ!
    አድዋ የጀግኖች የድል ሥፍራ። አድዋ የብዙሃን መቃብር ቦታ። አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ጮራ። ኑሪ ለዘላለም ለህያዋን ተስፋ ለወደቁልሽ ሰማእታት የክብር ሥፍራ!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule