• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቤተልሔም ፕላዛና ደብረወርቅ ታወር አገልግሎት እንዳይሠጡ ተከለከሉ

July 17, 2013 09:22 am by Editor 2 Comments

(ከጎልጉል አዘጋጅ – ለመስታወቱ ብቻ ቤተልሔም 9ሚሊዮን ብር ደብረወርቅ ደግሞ ከ15ሚሊዮን ብር በላይ አውጥተው እዚህ እስኪደርስ ድረስ የከንቲባ ኩማ መስተዳድር የት ነበር? ላዲሱ ከንቲባ ድሪባ የከተማውን ቁልፍ ሲያስረክብ ይሆን?)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ የሆናቸው ሁለት ሕንፃዎች ደረጃቸውን deribaአልጠበቁም በሚል ምክንያት የመጠቀሚያ ፈቃድ ከለከላቸው፡፡ሁለቱ ሕንፃዎች መገናኛ ድልድይ አካባቢ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛና ሜክሲኮ አካባቢ ከቡናና ሻይ ሕንፃ ፊት ለፊት የሚገኘው ደብረ ወርቅ ታወር ናቸው፡፡

ሁለቱ ሕንፃዎች የተጠቀሙበት የውጭ መስታወት አንፀባራቂ ነው በሚል ምክንያት አስተዳደሩ መስታወታቸው እንዲነሳ ማዘዙ ታውቋል፡፡

መገናኛ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛ ባለ ሰባት ፎቅ ነው፡፡ ያረፈው በ800 ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ ለግንባታው በአጠቃላይ 40 ሚሊዮን ብር መውጣቱን፣ ለመስታወቱ ብቻ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ከሕንፃው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሕንፃው ከሦስት ዓመት በፊት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ በርካታ የንግድ ተቋማት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ለመቆየት የኪራይ ውል ፈጽመው ሥራቸውን እያከናወኑበት ነው፡፡

አስተዳደሩ ያሳለፈው ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ተከራዮቹ ለቀው እንደ አዲስ የመስታወት ነቀላና ተከላ መካሄድ ይኖርበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሕንፃው ባለቤት የጣፋጭ ቤተልሔም ባለቤት አቶ ነጋሽ ባልቻ ናቸው፡፡

የደብረ ወርቅ ታወርም ይኸው ውሳኔ ተግባራዊ እንደሚሆንበት ተነግሯል፡፡ ደብረ ወርቅ ታወር ከፍታው 13 ፎቅ ሲሆን፣ ለወርቃማው መስታወት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣ ይነገራል፡፡

ደብረ ወርቅ ታወር በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሕንፃ ሲሆን፣ ለሕንፃው የወጣው ወጪ ተሰልቶ እንዳለቀ ባለቤቱ አቶ ተመስገንን ከፍያለው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ሕንፃዎች ባለቤቶች የአስተዳደሩን ውሳኔ አልተቀበሉትም፡፡ ምክንያታቸውም ሕንፃዎቹ የተገነቡት በግልጽ እየታየ ነው፡፡

ከተከራዮች ጋር ውል ገብተው ከሁለት ዓመታት በላይ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ መከራከራቸውን ቀጥለዋል፡፡ አቶ ተመስገን እንዳሉት፣ ሕንፃቸው ወርቃማ ቀለም እንዲኖረው ያደረጉት ለውበት ብለው ነው፡፡ በዚያ ላይ ደረጃውን የጠበቀና ድርብ በመሆኑ ሙቀት የለውም፣ አያንፀባርቅም ይላሉ፡፡

የሊዝ አዋጅና የሕንፃ አዋጅ በሕንፃ የመጠቀሚያ መስፈርትን በሚመለከት ድንጋጌ አውጥተዋል፡፡ ማንኛውም ሕንፃ በዲዛይኑ መሠረት ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሲሆን በሕንፃ የመጠቀም ፈቃድ ጠይቆ ሲያገኝ አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ አዋጆች ሕንፃዎች ማሟላት ስለሚኖርባቸው ቁም ነገሮች የሚናገሩ ቢሆኑም፣ ይህ አሠራር ብዙም ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል፡፡

እነዚህ ሁለት ሕንፃዎች የድንጋጌዎቹ የመጀመሪያ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ እነዚህ ሕንፃዎች በአንፀባራቂነት ቢፈረጁም በከተማው ውስጥ በርካታ ሕንፃዎች በዲዛይናቸው ለፓርኪንግ የተተወውን ቦታ ለሱፐር ማርኬትና ለመሳሰሉት ሥራዎች እያዋሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በዲዛይኑ ላይ የሌሉ ተቀጥላዎችንም እንደሚጨምሩ ይስተዋላል፡፡

አስተዳደሩ በቀጣይነት በእነዚህ መሰል ግንባታዎች ላይ ፊቱን እንደሚያዞር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ (ሪፖርተር)

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    July 17, 2013 08:40 pm at 8:40 pm

    Are they owned by hodam Amharas who did not properly weep when Fascist Meles Zenawi died? or hodam Amharas/Oromos/Guraghies etc who did not pay enough Money for woyane Grand theft Programme called – DAM

    Reply
    • selam says

      July 19, 2013 01:59 pm at 1:59 pm

      Ante qoshasha Erterawi neh what ur trying is an old Game so its over try some thing ealse u b$%# hodam malet ertrians nach edemi lekachewon ethiopian lemebelat afachew wuha moleto eyalegegu 21amet beqezzet yasalefu so menem yehun men it is not ur f….ing problem diqala.

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
Copyright © 2026 · Goolgule