
በአሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋገሩንና መንግስት በቡድኑ ላይ የሚወስደው እርምጃም አጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሚያ ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ አስታወቁ።
አቶ ሀይሉ የክልሉን ሰላምና ልማት አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ የክልሉን ሰላም እያናጋ ያለው የሸኔ ሽብር ቡድን ከሁሉም በማስቀደም በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ በአባ ገዳዎችና በሀዳ ሲንቄዎች በተደረገው ጥሪ 312 የቡድኑ አባላት ተመልሰዋል። 540 የሚሆኑት ደግሞ በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከታህሳስ 16 እስከ 30 ዓ.ም በተወሰደው እርምጃ 876 አባላት ሲደመሰሱ ኮማንድ ፖስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ በጥቅሉ ሁለት ሺህ 439 የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሰላማዊ መልኩ ወደ ሰላማዊ ትግል ለመመለስና ላለመመለስ በቡድኑ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋገሩን አቶ ሀይሉ ገልጸዋል።
አቶ ሀይሉ በዚሁ መግለጫቸው በክልል ደረጃ በርካታ የልማት ስራዎች የመስኖ ስራዎችን ጨምሮ ውጤታማ ስራዎች እየተሰራ መሆኑንና በድርቅ የተጎዱ እንደ ቦረና: ጉጂና ባሌ ከእንስሳት መኖ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎች እየቀረቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። (ኢ ፕ ድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሸኔዎች የሰው ደም እየጠጡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ናቸውና ከነዚህ ጋር መደራደርም ሆነ መስራት ኣይቻልም። ይህ የፓለቲካ ድርጅት ሳይሆን የጥልቁ ዓለም የማፊያ ድርጅት አሰራር ቀምቶ፣ገድሎ፣ኣስፈራርቶ ለመግዛት የሚፈልግ የካዛሪያና የሮም ማፊያና የኤሪያን ዘር ከሚያራምዱት የምስጥር መክበርያና ሰዎችን በባርነት የመግዛት ዝንባሌ ያለው የሕወኣት ፊት ወይም ጀርባ ነው። የሰለጠኑት በጥልቁ ዓለም ሰራዊትና ምልምሎች ስለሆኑ በዕፃናት መስዋዕትና ከዕፃናትና ከእንስሳ ጋር ዝሙት የሚያደርገው የዝሙቱ የጥልቁ ዓለም ከሚያደርጉት ጋር ተመሳሳይ ድርጊት የሚፈፀም መሆኑን ቀአካባቢው ያሉ ሰዎች የሚያዩትና የተመለከቱት ሸኔ የሚያደርገው ግዲያ ሁሉ ለሰይጣን የመሰዋት ተግባር በመሆኑ ይህ በምድራችን በተለይም በሆሮሞ ሕብረተሰብ ሊወገዝ የሚገባ ኘደገኛ ተግባር ነው። የሰው ስጋና ደም መጠጣት እጅግ ዘግናኝ ሲሆን ይህን የሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆኑ ሬፕታሊየን ተብለው የሚጠሩ የጥልቁ ዓለም ሰው መሳይ የወደቁ መላዕክት ናቸው።