መግቢያ አቡነ ፋኑኤል በዜና ቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲሰፍር ያደረጉት ሸፍጥ፤ ቢጤያቸውን ለመጋረድና የዘረጉትን የጥፋት መረብ ለማዳን ያደረጉት ሙከራ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። በዚህ ሸፍጥ ቢጤያቸውን ጋርደው ማዳን ይቅርና፤ ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያናችን አውጥተው መጣላቸውን ለማሳየት የምእመናኑን ውግዘት በቅዱሳት መጻህፍት መዝነው ካወጁት ቀሳውስት፦ ፩ኛ፦ ከሊቀ ማእምራን ዶክተር አማረ ካሣየ ፪ኛ፦ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ፫ኛ፦ ከአባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ ተክለ ሃይማኖት የተሰጠ መግለጫ እዚህ ላይ ይገኛል። … [Read more...] about አባ ፋኑኤል ራሳቸውን ወጉ
Religion
ሃይማኖታዊ
ዘዳግም!
የደመራ ዋና ዓላማ፤ “ሲቃወምና ሲጻረር የነበረውን የዕዳ ጽህፈት ክርስቶስ ከነ ሕግጋቱ በመደምሰስ በመሰቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው” (ቆላ ፪፡፲፬)። ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው፤ የተደበቀውን እውነት ለመግለጥ፤ በሰው ላይ ተጭኖ የነበረውን ዕዳ ለመደምሰስ፤ ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነቱን ነገሮች ለማስወገድ ነው። [በሰፊው መረዳት ከፈለጉ ይህን ሰንሰለት ይጫኑ። ደመራ] ሙሴ አራቱን የኦሪት መጻሕፍት ከጻፈ በኋላ፤ በአራቱም መጻሕት የገለጻቸውን ጠቅለል አድርጎ በድጋሚ ያቀረበበት አምስተኛው መጽሐፍ ዘዳግም ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነውን ለማስወገድ የገለጸባቸውን ኃይለ ቃላት ለማስጨበት “አማን አማን እብለክሙ” እያለ በመደጋጋም ተናግሯል። በጸሎተ ቅዳሴያችንም “ተንስኡ ለጸሎት” የሚለውን እንደጋግማለን። ቃጭልም … [Read more...] about ዘዳግም!
የቀሳውስት ድምጽ
በሀገር፣ በሕዝብና በቤተ ክርስቲያን ላይ በደል ሲፈጸም የጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት የሚያሰሙት ድምጽ “ዘወሀብከነ ሥልጣነ በመንፈስ ንኪድ ኩሎ ኃይሎ ለጸላኢ ከመ ንፍታህ ዘኢይትፈታህ” ማለትም፦ “ጠላት ሰይጣን እንዳይፈታ አርጎ የቋጠረውን የችግር ሰንሰለት እንፈታ ዘንድ የቅስናዋን መንፈሳዊት ሥልጣን የሰጠኸን አምላክ” እያልን በምንገልጻት ተልእኮ በጥንታዊት ኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያሰማራንን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን እያልን፤ እኛ ቀሲስ ዶ/ ር አማረ ካሳዬ እና ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ/ ምህረት በዋሸንግተን ዲስ በተደረገው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ይህችን የቤተ ክርስቲያን ድምጽ አቀረብን። ከኛ በፊት በህዝባችንና በአገራችን ላይ መከራና ስቃይ በደረሰባቸው ጊዜዎች ሁሉ፤ አባቶቻችን ቀሳውስት የእምነትና … [Read more...] about የቀሳውስት ድምጽ
አራዊታዊ መንግሥታት
አራዊታዊው ኢሀደግ እና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ዶክተር ቀሲስ አማረ ካሣየ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አባ ኃ/ሚካኤል የሰጡት መግለጫ፦ በአገራችን ላይ ክፉ ዘመን የወለደው አራዊታዊው መንግሥትና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር በፈጣሪና በፍጡሩ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው፤ የሰው ጥንተ ጠላት የሆነው የሰይጣን ተግባር ስለሆነ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን የሚወገዝ ነው። ሕዝባችንም የዜግነት ከለላ ከሰጣቸው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋራ በመተባበር አቶ አንዳርጋቸውንና በተመሳሳይ አራዊታዊ አደና የተያዙትን ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለማስለቀቅ የጀመረውን ጥረት አስፈላጊ በሆነው ሁሉ መንገድ እንዲቀጥል እግዚአብሔር የሚቀበለውና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም … [Read more...] about አራዊታዊ መንግሥታት