መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመበጥበጥ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መሳሪያም ተገኝቶባቸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው። የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ … [Read more...] about የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Religion
ሃይማኖታዊ
ኦሮሞዎች በየዓመቱ ለሚያከብሩት ኢሬቻ በዓል ቦታ ተሰጠ
የኦሮሞ ተወላጆች በየዓመቱ ለሚያከብሩት የኢሬቻ በዓል መከበሪያ ቦታ በአዲስ አበባ መስጠቱን አስተዳደሩ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢሬቻ በዓል (ሆረ ፊንፊኔ) ማክበሪያ ቦታ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ለአባገዳዎች በዛሬው ዕለት አስረክቧል። ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ ከአባገዳዎች ጋር በመሆን በመጎብኘት ዝግጁነቱን አረጋግጠዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት የዘንድሮ በዓል በአባገዳዎች በሚወሰን ትንሽ የሰው ቁጥር ብቻ እንደሚከበር ከስምምነት ላይ መደረሱን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል። የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር የተጣመረ ነው፤ ይህም ሃይማኖታዊ ክብረበዓል የገዳን ሥርዓት ሃይማኖታዊ ያደርገዋል፤ ስለዚህ የገዳ ሥርዓት እንደ ትምህርት በመንግሥት ትምህርት ቤቶች መሰጠት አይገባውም … [Read more...] about ኦሮሞዎች በየዓመቱ ለሚያከብሩት ኢሬቻ በዓል ቦታ ተሰጠ
ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጥያቄዎቿን እንዲቀበላት ጠየቀች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚነገረው “በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ” ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይሆኑ፣ የተሳሳቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ትርክቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ በተቀነባበረና በተደራጀ ሥልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የማፅዳት እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ቤተ ክህነት ገለጸች። የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊው ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች በስድስት ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ 25 ወረዳዎች በሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የገለጸችው ቤተ ክህነት፣ በጥቅምት ወርና በጥር ወር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሃጫሉ ሞት ምክንያት በአቢያተ ክርስቲያናትና … [Read more...] about ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
እንደ መግቢያ ሰሞኑንን ከኮቪድ - 19 ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሓኖም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ከሚያራምደው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር ካደረገ፣ በጅምላ ሴቶች እንዲደፈሩና ከነነፍሳቸው ለአውሬ እንዲጣሉ ካደረገ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ትህነግ ቴድሮስ የተቀዳ አመራር እንደነበር አይዘነጋም። የተመረጠው በኃያላኑ ዓላማና መልካም ፈቃድ ነበር፤ ኃያላኑ አሁን ፍጥጫ በሚመስል ውዝግብ ውስጥ ይገኛሉ፤ የተመረጠበትን ዓላማ የፈጸመ ከሆነ መወገዱ የማይቀር ይሆናል፤ ካላለቀ ደግሞ ዕድሜ ማራዘሚያ ይሰጠዋል። የቴድሮስ የWHO ምርጫ ወቅቱ የዛሬ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር … [Read more...] about የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?