ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች “የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች። በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን … [Read more...] about “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?
በዛሬው (ማክሰኞ) የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው፤ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤ አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤ ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን፤ ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች” ብለው ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል። ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ተጨባጭ ሳይንስ ነው? የብሄራዊ … [Read more...] about በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?
በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ
በትግራይ ክልል የተካሄደውን ሕግ የማስከበር ተግባር ተከትሎ በሴቶች ላይ ጥቃት ስለመፈጸሙ የሚያጣራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ መቀሌ መግባቱን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ግብረ ኃይሉ በክልሉ ያሉ የሴቶችና ህጻናት ቢሮዎችን የማደራጀትና አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የመለየት ተጨማሪ ኃላፊነቶች እንዳሉትም ተገለጸ፡፡ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አድነው አበራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የተቋቋመው ግብረ ኃይል ከጤና ሚኒስቴር፣ ከሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከመከላከያና ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተውጣጣ ነው፡፡ ግብረ ኃይሉ በዋናነት በትግራይ ክልል የተካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በመቀሌና በሌሎችም የትግራይ አካባቢዎች ተፈፅሟል እየተባለ በውጭ አካላትና በማህበራዊ ሚዲያ … [Read more...] about በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ
በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ
በአዲስ አበባ 1 ሺሕ 338 ሄክታር መሬት አሁንም በወረራ ተይዞ እንደሚገኝ አስተዳደሩ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በህገወጥ መሬት ወረራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ ካሉ 121 ወረዳዎች ውስጥ በ88ቱ የመሬት ወረራ ተፈጽሟል። በአጠቃላይ በከተማዋ 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት የተወረረ ሲሆን በተደረገው የህንጻ ቆጠራ 322 ህንጻዎች እና ቤቶች ባለቤት አልባ መሆናቸውን ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 ቤቶች የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም። 850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ … [Read more...] about በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
በአድዋ ጦርነት ወቅት ለእናት ሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23/2013 ይከበራል፡፡ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡ በዓሉ የተነቃቃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የጎላ ሚና እያበረከተ ነው ተብሏል፡፡ (አብመድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ ስምምነትን የክልሎቹ መሪዎች ተፈራርመዋል።በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰላም እና የጋራ የልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል።ጽ/ቤቱ በሁለቱ ክልሎች 12 አዋሳኝ ዞኖችች ላይ ሰላምን በማስፈን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ጥናቶችን ይፋ አድርጓል።በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተዋቀረው የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ በቀጣይ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለመተግበር ማቀዱን ነው የኦሮሚያ ክልል ያስታወቀው።የኦሮሞ እና ሱማሌ ሕዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት የተሳሰሩ እና ከ 1 ሺህ 872 ኪ.ሜ በላይ ወሰን የሚጋሩ … [Read more...] about የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በሰፊው ታስቦ እንደሚውል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።በዓሉ ሲከበር በወረዳዎች በመሰረተ ልማት ቦታዎች ላይ የጀግኖች ስም የሚሰየም እንደሚሆንና የመደመር የኪነጥበብ ትርኢቶች እደሚዘጋጁ የምሁራንና የህዝብ የውይይት መድረኮችም እንደሚካሄዱአድዋን ለአባይ በሚል መሪ ሀሳብም የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳልም ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ወቅት ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት አከባበር መለያ አርማ (Logo) ይፋ አድርጓል፡፡የአርማው መግለጫ፦- ጋሻ ጎራዴና ጦር፦ አባቶቻችን ጠላትን የተዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎች፤- … [Read more...] about 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
በመቀሌ ከተማ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ክምችት እንዳለ የፌደራል መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ። በትግራይ ክልል የመድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ተነግሯል። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከሆነ በትግራይ ክልል ለ47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ ወደ ክልሉ በመድረስ የማሰራጨት አገልግሎት ማከናወኑን አስታውቋል። ቅርንጫፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 የጤና ተቋማት ግብዓቶቹን በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን በተለይም በመቀሌ ለሚገኙ 4 ሆስፒታሎች ለዉቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድሰት ማርያም፣ ኮረምና ሌሎች ሆስፒታሎች መድሃኒቶችን አሰራጭቻለሁ ብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ አንዲሁም በማዕከል በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና … [Read more...] about በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
“አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። ቃፍታ ሁመራ ከተማ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ ነጻ ከወጣች ሶስት ሳምንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣ ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል። ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን … [Read more...] about የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል። ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል። በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው … [Read more...] about “የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል