የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 27, 267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 376 ተፈታኞች በቡድን፤ 483 ተፈታኞች ደግሞ በግል ጥፋት ፈጽመዋልጥፋቶቹም፤ለሌላ … [Read more...] about ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም
የኢትዮጵያ ክብርና ነፃነት በቆራጥ ልጆቿ መሥዋዕትነት የተገኘ መሆኑ የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለሀገራችን ሠላም፣ ለሠንደቅ ዓላማችን ክብር ሲሉ መሥዋዕትነት ከከፈሉ ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም አንዱ ናቸው፡፡ ዛሬ ጳጉሜ 2 ለኢትዮጵያ ሀገራቸው መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች የሚታሰቡበት እና የሚዘከሩበት ቀን እንደመሆኑ በዛሬው የአውደ ሰብ አምዳችን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያምን ባለታሪካችን አድርገናቸዋል፡፡ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ተወልደው ያደጉት በጉራጌ ዞን ከቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሲሰ መንደር ውስጥ ነው፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን እዚያው እምድብር ከተማ የተማሩ ሲሆን፣ በ1948 ዓመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትነው በጥሩ ውጤት … [Read more...] about ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም
ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በመኪና ሻግ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ። በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመኪና ሻግ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭነው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለጊዜው ባለቤቱ ባልታወቀ ተሽከርካሪ 202 ፍየሎችን ከላይ፣ ከሥር ደግሞ በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የብር ጌጣጌጦችን በሻግ ጭነው ከያቤሎ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ብርጭቆ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር … [Read more...] about ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
ነብርን ያላመዱ እናት
ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ ይባላሉ፤ በቦረና ዞን የዲሎ ወረዳ ቃዲም ኦላ ጫጩ ገልገሎ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ የዱር እንስሳት የሆነውን ነብርን በማላመድ አብራቸው እየኖረ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ጂሎ በዞኑ ድርቅ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ለከብቶች ሳር ለመፈለግ ወደ ዱር ባቀኑበት ጊዜ የነብር ግልገል ማግኘታቸውን ይናገራል። ወይዘሮዋ ግልገሏን እነርሱ የሚመገቡትን ምግብ በመመገብ እንዳሰደጉትና አሁን ላይ ተላምዶ ከፍየሎችና ህፃናት ጋር እያደገ ነው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ነብርን ያላመዱ እናት
ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ሥራዎች የሚታወቅ ወጣት ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰራ። በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ስራዎች የሚታወቅ ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያ 360° ዞር መምታት የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰርቶ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ እና የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በተገኙበት ለእይታ አቅርቧል። ሮኬቱ ከስድስት እስከ 10 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል መሆኑን ወጣት ዘካሪያ በመገለጽ በአንዴ አራት ቀላዮችን የሚይዝና መወንጨፍ የሚችል ሮኬት መሰራቱን ገልጸዋል። ያለሰው ንክኪ በራሱ ማዘዣ 360° ዲግሪ በመዞር በአየር ክልል የሚንቀሳቀስና ጥሶ የሚገባ የጠላት ዒላማን መምታት የሚችል ሮኬት መሆኑንም አስታውቆ ቦታው ከተመቻቸ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የተሳካ … [Read more...] about ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው
በኢትዮጵያ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ከፍተኛ” የሚባለውን ደረጃ ያሟሉ፤ አራት ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ካሉ 47 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራቱ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ወላጆች፣ የቀድሞ ተማሪዎች እና መምህራንን የሚያሳትፍ፤ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሀገር አቀፍ የትምህርት ዘመቻ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 15፤ 2015 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው። ሪፖርቱን ለፓርላማ አባላት ያቀረቡት … [Read more...] about በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው
በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
ጦርነት ባሕላችን ነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ወዘተ በሚሉ ባዶ ዲስኩሮችና ከንቱ ልፈፋዎች ትውልድን በስሁት ትርክት ሲነዳ የኖረው ትህነግ የሚፈራው ጥያቄ እየቀረበለት ነው። "ልጆቻችን የት ናቸው?" "ልጆቻችንን መልሰን ማግኘት እንፈልጋለን" ወዘተ የሚሉ የወላጆች ጥያቄ በትግራይ እየተሰማ ነው። አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል። አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ … [Read more...] about በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
“የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል። በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች … [Read more...] about “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ … [Read more...] about አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
ሕጉ ምን ይዟል ? ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው (LGBTQ+) ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ የረጅም ጊዜ እስር ይጠብቀዋል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ፣ በቤተሰብ ደረጃ ያስጠለለ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል። በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል። "በተመሳሳይ ጸታ መብት" ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት … [Read more...] about የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ