በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቪላ ቤቶችንና አፓርትመንቶችን በተወሰነ ጊዜ ሠርተው ለማስረከብ ሩብ፣ ግማሽና ሙሉ ክፍያ ከተቀበሉ በኋላ፣ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ከአገር የወጡት የአክሰስ ሪል ስቴት የቦርድ ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ወደ አገር ቤት እንደሚመለሱ ተጠቆመ፡፡ አቶ ኤርሚያስ ከአገር ከወጡ በኋላ ሳይመለሱ በዚያው የቀሩት፣ ቤት ሊገነቡላቸው የተዋዋሉዋቸው ሰዎች ቁጣና ዛቻን ብቻ ፈርተው ሳይሆን፣ አገር ቤት በነበሩበት ጊዜ ‹‹ግንባታው ይቅርብን ገንዘባችንን መልስ›› ላሏቸው ቁጥራቸው በውል ለማይታወቅ ሰዎች በጻፉት ደረቅ ቼክ ምክንያት መሆኑን ላነጋገሯቸው የቅርብ ጓደኞቻቸውና ወዳጆቻቸው መናገራቸው ተገልጿል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ለደንበኞቻቸው የሰጧቸው ቼኮች ደረቅ … [Read more...] about አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚመጡ ተጠቆመ
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
በሰሜን ኮሪያ የደናግላት ቁጥር መመናመን ፕሬዚዳንቱን አሳስቧል!
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ እን ለሚያካሂዱት የዳንስ ስኳድ በቂ ደናግልት ለማግኘት መቸገራቸውን የደቡብ ኮሪያ ዜና ቾሱን ኢልቦ ገለጸ፡፡ ሰሜን ኮሪያ ለፕሬዚዳንቷ ክብር የምትጠቀምባቸው ዳንሰኞች የሚውጣጡት ከደናግልት ሴቶች ነው፡፡ ለዚህ ፕሬዚዳንቱን ለማዝናናት የሚደረገው የዳንስና ሙዚቃ ሙያ አባል ለመሆን የሚችሉ ድንግል ሴቶች በአብዛኛው ወጣቶችና የኮሌጅ ተማሪዎች እንደሆኑ ተዘግቧል፡፡ ክብረንጽህናን መጠበቅም ዋንኛው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ሰሜን ኮሪያ ካለባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ባሻገር አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያን በጣሉባት የኢኮኖሚ ማዕቀብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ አሽመድምዶታል፡፡ በመሆኑም ሴቶች የትምህርት ወጪያቸውን ለመደጎም እንዲሁም የኑሮውን ውድነት ለመቋቋም በሴተኛ አዳሪነት በመሰማራታቸው የደናግልቱ ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ ለማሽቆልቆሉ እንደ ምክንያት … [Read more...] about በሰሜን ኮሪያ የደናግላት ቁጥር መመናመን ፕሬዚዳንቱን አሳስቧል!
እነ “ሻኪራ” በአሞራ ገደል
የዛሬ ሳምንት ሀዋሳ ነበርኩኝ፡፡ የወትሮዋ ሳቂታዋ ሀዋሳ አልነበረችም፡፡ አኩርፋለች፡፡ ሌላ ችግር ገጥሟት ግን አይደለም፡፡ ክረምቱ ነው ያስኮረፋት፡፡ ዝናቡ፣ ቅዝቃዜውና ደመና የሸፈነው ሰማይ ተጫጭነዋት ነበር፡፡ እንደኔ እንደኔ ሀዋሳ ደርሶ አሞራ ገደልን ሳይጐበኙ መመለስ ካለመሄድ እኩል ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ዓሳ እንደጉድ ይበላል፡፡ ያውም ቁጥር - ልክ እንደ ስጋ፡፡ የአሳ ቁርጥ ተመጋቢዎች በእንጨት ግድግዳ በተከበበው ዳስ መሳይ ቤት ውስጥ ግፊያውና መረጋገጡን ተያይዘውታል፡፡ በሀዋሳ ሀይቅ ዳር ባለው በዚህ ስፍራ ሰው ከአንድ ቦታ አሳውን ይገዛና እዛው ዳስ ቤት ውስጥ የአሳውን እሾክ እያስወጣ ቁርጡን በሳህን እየያዘ ማባያውን ለማግኘት ሁለት ጐን ለጐን የተቀመጡ ማባያ አቅራቢዎች ጋር መገናኘት ይጠበቅበታል፡፡ አንዱ “ዳጣ” የተባለው እና ከሚጥሚጣ እንዲሁም ከሌሎች ቅመሞች የተሰራ … [Read more...] about እነ “ሻኪራ” በአሞራ ገደል
የብዙኃኑ መገናኛዎች የያዙት አቋም ሕዝብና ሀገርን እንደሚጎዳ ሳያውቁ ቀርተው ወይስ?
ሰላም ጤና ይስጥልኝ አንባቢያን እንደምን አላችሁ? ይሄውላችሁ እንደምታውቁት ጥቂት ከማይባል ዓመታት ወዲህ ቀድሞ ከነበረን የሥነ-ኪናችን አትኩሮት በተለየ መልኩ አልፎ አልፎ ብቅ ከሚሉ አንዳንድ ዘፈኖች ወይም ሙዚቃዎች በስተቀር (በነገራችን ላይ ሙዚቃ የሚለው ቃል አማርኛ አይደለም፡፡ ሙዚክ ወይም ሚዩዚክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በአገርኛ ለዛ ሲጠራ ነው፡፡ ልክ አፍሪካ አፍሪቃ፣ ስኩል አስኳላ እንደተባለው ማለት ነው፡፡) እናም ከጥቂት ዘፈኖች በስተቀር የዘፈኖቻችን በአንድ ነጠላ ርእሰ ጉዳይ ማለትም ጾታዊ ፍቅር ላይ እንዲያተኩሩ መደረጉ ሥነ-ኪን ወይም በዘልማድ ኪነጥበብ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ልታበረክተው የምትችለው የማይተካ ሚና ሀገራችን እንዳታገኝ መሆኗ እንደ ዜጋ አሳስቦኝና የድርሻየን ለመወጣት በዜጎች ሰብአዊ ልማት ላይ ያተኮረ “ፋሽን” የተሰኘ አንድ ዘፈን ዜማና … [Read more...] about የብዙኃኑ መገናኛዎች የያዙት አቋም ሕዝብና ሀገርን እንደሚጎዳ ሳያውቁ ቀርተው ወይስ?
የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . .
የሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት የ42 አመት እመቤት በምድረ አሜሪካ በቤት ሰራተኛቸው መብት ገፈፋ ተከሰው ለፍርድ ቀርበዋል። ልዕልቷ ኬንያዊዋን የቤት ሰራተኛቸውን በአነስተኛ ክፍያ ከ16 ላላነሱ ሰአታት በመክፈል እና የኬንያዊቷን ሰራተኛ ፖስፖርት ለባለቤቷ ባለመስጠታቸው ተከሰው በምድረ አሜሪካ ለወህኒ ከተዳረጉበት በ5 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ቢፈቱም ዛሬም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሰምተናን። ይህንን ዜና ሳነብ ያን ሰሞን " ጋዜጠኛ ነህ አሉ እርዳኝ? " ብላ ከወደ ደማም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወለች የምታነባዋ ኢትዮጵያዊት እህት ፍዳ አስታወስኩ ! ዛሬ ረፋዱ ላይ ያነጋገርኳት ይህች እህት የሚደርስባት ግፍ ሳያንስ የተሰደደች የምትገፋበትን የወር ደመወዟን ላለፉት በርካታ ወራት እንዳልተሰጣት ገልጻልኛለች ። ዛሬ በጣሙን ከፍቷት እያለቀሰች ከገባችበት ስቃይ እታደጋት ዘንድ … [Read more...] about የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . .
የንባብ ባሕል ለምን እንዴትስ ይፈጠራል?
ስለ ንባብ ባሕል ስናነሣ በሀገራችን ያለው የንባብ ባሕል በዓለማችን ብቸኛውና የመጠቀ የረቀቀ የመጨረሻው ደረጃም ላይ የደረሰ ነው፡፡ይህም ማለት መጻሕፍትን ጥሬ ንባባቸውን ብቻ ሳይሆን ከነምሥጢራቸው ጥጥት አድርጎ በቃል እስከ ማነብነብ ወይም መያዝ የደረሰ ፡፡ ሀገራችን ስላሏት እሴቶች ምንጭ ወይም አድራሻ ስናስስ ዞረን ዞረን የምንደርሰው አንድ ቦታ ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከላይ የጠቀስኩትን የራሳችን የሆነን የንባብ ባሕል የፈጠረች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ ብዙ ዓይነት መጻሕፍት አሉ የሚገርመው ታዲያ ከእነዚህ መጻሕፍት በሊቃውንቱ በቃል ያልተያዘ መጽሐፍ አለመኖሩ ነው እንዲኖርም አይጠበቅም፡፡ ይሄ ዓይነት የተለየ የንባብ ባሕላችን ታዲያ ሀገራችን በተደጋጋሚ በጠላት በተጠቃችና መጻሕፍት በወደሙ፣ በጠፉ፣ በተቃጠሉ ጊዜ … [Read more...] about የንባብ ባሕል ለምን እንዴትስ ይፈጠራል?
ለፈገግታ፤ ለጨዋታ ከቁም ነገር ጋር …
ዛሬ ጠዋት ታክሲ የምጠብቅበት ቦታ መንገድ ላይ ዕቃ ዘርግተው ከሚሸጡ ነጋዴዎች መካከል አንዱ፤ ጆሮ ገብ ማስታወቂያ ሲሰራ ሰምቼ ዞር ብዬ አየሁት፡፡ ‹‹የሴቶች ፓንት ከነቂጡ በ20 ብር ብቻ!›› በበእውቀቱ ስዩም አባባል ‹‹ማቄጥ ለተሳናቸው›› ሴቶች የተሰራውን እንዲህ ያለውን ‹‹ግልገል ሱሪ›› ካየሁት ሰነባብቻለሁ፡፡ እንዲህ ሲሸጥ ግን ሰምቼ አላውቅምና ሳቅሁ፡፡ የግዜያችን ሴቶች፤ ፀጉራችን፣ ጡታችን፣ አሁን አሁን ደግሞ መቀመጫችን ሳይቀር ከመንገድ ላይ የሚገዛ መሆኑ አስገራሚ ነው፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች የምናወራው ወሬም የዚያኑ ያህል ግራ የሚያገባ እየሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ አስቧት አንዷን ከባሏ ጋር እንዲህ ስትባባል… ‹‹የኔ ቆንጆ እንውጣ፤ ረፈደ›› ይላታል እሱ፡፡ ‹‹እሺ..እስቲ ከዚያ …ከኮመዲናው ላይ ፀጉሬን … [Read more...] about ለፈገግታ፤ ለጨዋታ ከቁም ነገር ጋር …
በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለው ግብረሰዶማዊነትና ሴራው
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቀድሞ የተናቁና የተዘነጉ አንዳንድ ዘመን አመጣሽ ከባዕድ የገቡ ችግሮች እጅግ አሳሳቢ አደጋ እየጋረጡ እንደመጡ በተለይ በዚህ ወቅት በግልጽ ዕየታዩ ነው፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ቀስ እያለ የሞቀና እያላመደ የተባባሰ የመባባስም ባሕርይ ስላለው የህልውና አደጋ የመጋረጥ ደረጃ (boiling point) ሲደርስ ሁሉ እዛ ደረጃ መድረሱን ሳናስተውለው በፍላት ኃይሉ ተቀቅለን ልንፈራርስ የምንችልበት አጋጣሚ ሰፊ ሆኗል፡፡ ይሄንን አዚማም የችግሩን ባሕርይ ከወዲሁ የተረዱ ግለሰቦችና አንድ ማኅበር በሀገራችን ግብረሰዶማዊነትና የጋረጠውን አደጋ፣ የደረሰበትን አሳሳቢ ደረጃ ለሕዝብ የማሳወቅ እንቅስቃሴ በዜግነታቸው ለሀገራቸው ወይም ለሕዝባቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ማንም ምንም ሳይላቸው ለሀገርና ለሕዝብ ባላቸው ፍቅር በግል ተነሣሽነት ብቻ በመንቀሳቀስ … [Read more...] about በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለው ግብረሰዶማዊነትና ሴራው
ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
አጠገብ ያሉ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ እንዲለቁ ተነገራቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ለማድረግ ስምምነት ሊያደርግ ነው በግዙፉ የጀሞ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች መንደር ውስጥ በአንድ በኩል በመስመጥ ላይ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሕንፃ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሕንፃው እንዲለቁ ተነገራቸው፡፡ በሁለቱ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሕንፃዎቹ እንዲለቁ የተጠየቁት በክፍለ ከተማው የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት አማካይነት መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የውሳኔው መነሻ ወደ አንድ ጐን በማዘንበል ላይ የሚገኘው ሕንፃ አጠገብ ያሉት ሁለት ሕንፃዎች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው በሚል ቢሆንም፣ በሕንፃዎቹ ላይ በዓይን የሚታይ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ሕንፃዎች ተመሳሳይ መሰነጣጠቅ በውስጥ አካላቸው … [Read more...] about ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
የቤተልሔም አበራ የሥነ-ምግባርን ቅጥር የመናድ ተልእኮ
ትናንት ቅዳሜ 2-10-2005 ዓ.ም ፌስ ቡክ ላይ ተጥጄ በነበርኩበት ሰዓት አንዱ ጓደኛዬ አንድ ከቪዲዮ (ከትዕይንተ ኩነት) የተወሰደ ፎቶ (ምስለ ኩነት) ለጥፎ እዚያው ላይም አስተያየቱን ጽፎ ሌሎቹም ይጽፉ ዘንድ ጋበዘ፡፡ ነገር ግን ይህ ጓደኛዬ ስለጉዳዩ ትክክለኛ መረጃ አልነበረውም ነበርና በአስተያዬቱ ላይ ለሕዝብ በቀጥታ በሚታይ መድረክ ላይ ከወገብ በታች እርቃን መታየት ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የወጣና መወገዝ እንዳለበት በ3 መስመር ጽፎ ነበር፡፡ እኔም ፎቶውን(ምስለ ኩነቱን) ዓይቼ በነገሩ ተደናግጬና ግራ ተጋብቼ ከስር (is she a crazy woman? I am sure she is a escapee from the Amanuel mental institution) ጤነኛ ነች ግን? እርግጠኛ ነኝ ከአማኑኤል የእዕምሮ ሕሙማን የሕክምና ማዕከል ያመለጠች ነች ብዬ ጻፍኩ፡፡ ለካ ነገሩ እንዲህ … [Read more...] about የቤተልሔም አበራ የሥነ-ምግባርን ቅጥር የመናድ ተልእኮ