አገራችንን ለቅቀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ በባዕድ አገር በርካታ የምንማራቸው፤ የምንለምዳቸው ባህሎች አሉ፡፡ የዚያኑ ያህል መማር የሌለብን ወይም እንዳልተማርን መሆን ያለብንም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ከበርካታዎቹ ሸግዬ ባህሎች መካከል የምስጋና ቀን “Thanksgiving Day” የሚጠቀስ ነው - ወደ ታሪኩና ዝርዝሩ ሳልገባ እንደው በደፈናው ማመስገን መልካም ነው፤ ለዚያም ቢያንስ በዓመት አንዴ ቀን መመደብ ተገቢ ነው በሚለው እሳቤ ብቻ፡፡ ከማማረርና ማጉረምረም አንዳንዴም ባርኮትን ቆጥሮ (ጥቂትም ቢሆን) ማመስገን ሸጋ ነው - ምስጋናው ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፤ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ፣ ለትዳር ጓደኛ፣ ለልጆች፣ ለወገን፣ ላገር ልጅ፣ … ማብቂያ የለውም፡፡ ታዲያ “ሃሎዊንስ”? የመሰልጠናችን፣ የፈረንጁን ባሕል የመልመዳችን፣ ከኋላ ቀርነት የመላቀቃችን፣ … ምልክት ስለሆነ ይሆን … [Read more...] about ዳያስፖራና “Halloween”
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
“ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ለአዲስ አበባ ከተማ ክብር ያላችሁ እንስማማለን። አዲስ አበባ አንጀቷ ርህሩህ ነው። ከገዢዎች ክፋት በተጨማሪ አዲስ አበባ ፊቷን ብታጠቁር ምን ይኮን ነበር? ሎሬት ጸጋ ስለ አዲስ አበባ ተቀኙት ወደው አይደለም። በውነት ላስተዋለው የአዲስ አበባ ቆዳና ያዲስ አበቤዎች ትከሻ “ላይችል አይሰጥም” የሚሉት አይነት ነው። በየቀኑ አዲስ አበባ በማለዳ በትና በምሽት የምትሰበስባቸው ልጆቿ ተቃምሰው ማደራቸው ባዲሳባ በረከት እንጂ በገዢዎች አቅርቦት አይመስልም። ከአራቱም ማዕዘን የሰው ደራሽ ወደ አዲስ አበባ ይንፎለፎላል። አዲስ አበባ ሞልታ የምትፈስ አትመስልም። እምዬ ምኒሊክ ሲቆረቁሯት ጀምሮ አዲስ አበባ ተቀባይ ነች። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና፣ የሰው ልጅ እምብርት፣ አዲስ አበባ፣ ፊንፊኔ። ምንም ትባል ምን አዲስ አበባ ሁሉም ጓዳ የተባረከች ናት። … [Read more...] about “ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) “በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም። እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው … [Read more...] about የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች
“ጣጣ የለውም!” ሌላው ግሽበት
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ዛሬ ዛሬ ባገራችን በተለይም አዲስ አበባ በየቀኑ የሚመረቱት ቃላቶች የሚሰበስባቸው ቢገኝ አንድ ራሱን የቻለ ቋንቋ ይመሰርታሉ። ለተረብ የሚወረወሩት ቃላቶች ደግሞ ፈጠራቸው እስኪገርም ድረስ ያንተከትካሉ፤ ያስቃሉ። ወሬ ከሚፈላባቸው ቦታዎች መካከል ጫት ቤቶች ይጠቀሳሉ። በጫት ቤት ወሬ ይበለታል፤ መንግስት ይገሸለጣል። ጫት ቤት ሆነው ከፍተኛ መመሪያ የሚያስተላልፉ ጥቂት አይደሉም። ጫት ቤት ቁጭ ብለው መንገድ እንዲወጠር የሚያዙ የፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎች አሉ። ከአቶ መለስ ጠባቂዎችም መካከል መርቃኞች የነበሩ፣ ለስራ ሲፈለጉ ሸሚዝ ቀይረው በኮብራ የሚበሩ አሉ። ጫት ቤት የማይሰበስበው ሰው የለም። ዶክተሮች፣ የህግ ሰዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ልማታዊ የህዝብ ግንኙነቶች፣ ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ የደህንነት ሰዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ ከንቲባዎች፣ ዞንና የቀበሌ ሰራተኞች… … [Read more...] about “ጣጣ የለውም!” ሌላው ግሽበት