ቦሳሶ፣ ሶማሊያ ቦሳሶ በገልፍ ባህረ ሰላጤ ደቡባዊ ክፍል፣ሶማሊያ ጠርዝ ላይ የምትገኘው ከተማ፣ ካርታ ላይ ሲመለከትዋት፣ ያፍሪካ ቀንድ ላይ የተቀመጠች ዝምብ ትመስላለች። አፈ ታሪክ ስለከተማዋ አሰያየም እንዲህ ይላል። ቦሳሶ የቀድሞ ሥያሜዋን ያገኘችው ካንድ ታዋቂ ነጋዴ ሥም ነበር - ባንዳር ቃሲም ከተባለ ነጋዴ። ቃሲም ከተማ እየተባለች ትታውቅም ነበር። ነጋዴው፣ ባንዳር ቃሲም ደግሞ እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ቡሳስ የተባለች ግመል ነበረችው። ሥለዚህ ከተማዋ ከጊዜ በኋላ በቃሲም ተወዳጅ ግመል ቡሳስ ተብላ ተሰየመች። እያደር ከቡሳስነት ወደ ቦሳሶ ተቀየረች። አለምሰገድና ባለቤቱ ምህረት፣ ምህረትያንድ አመት ልጃቸውን አቅፋ፣ ከቦሳሶ ተነስተው ከሦስት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማሬሮ ገብትዋል። ማሬሮ ገደላማ ናት። ካርቶን አንጥፈው የሚቆረቁረው መሬት ላይ ተቀመጡ። አለምሰገድ ለራሱና ለምህረት … [Read more...] about ሥደት
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
ሥደት
የእኔ፣ ያንተ፣ የእናንተ፣ የእኛ ተጠቂዎች!
የብላቴናው መሀመድን እናት እርዳታ አድራጊ ወገኖቸ የቻልኩትን እርዳታ ለመሰብሰብ ወጣ ባልኩበት አጋጣሚ ስልክ ተደወለልኝ። አነሳሁት፣ ከሰላምታ በኋላ "ጠፋህ? የት ነው ያለህ?" ከሚለው አጭር የተለመደ የሰላምታ ማጀቢያ በኋላ ወዳጀ ወደ መልዕክታቸው ገቡ ... "አንተ ነብዩ የት ጠፋህ?" ሲሉ ደገሙና ስመለጥፋቴ ጠይቀውኝ ሲቀጥሉ "ናና አንድ እህት ከጅዳ ቆንስል በር ወድቃለች፣ ጸሀይ እየደበደበ አድክሟታል! እነሱ (የቆንስል ሰዎች ማለታቸው ነው) ቢነግሯቸው አይሰሙም። ሌላም ሶስት እህቶች ከቆንስሉ አጠገብ ካለው ንጉድ ፉአድ ሆስፒታል ያለ ጠያቂ ተኝተዋል። ጎብኟቸውና ችግራቸውን ተረዱ ወይ መፍትሄ ፈልጉ ወይ ወደ ሀገር ስደዷቸው ብል የሚሰማ የለም! አንተን ከሰሙህ ናና እያቸው!" ብለው ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት አስተላለፈውልኝ ተጣድፈው ስልኩን ዘጉት ... ! የእኒህ ወንድም … [Read more...] about የእኔ፣ ያንተ፣ የእናንተ፣ የእኛ ተጠቂዎች!
የኮንትሮባንድ ንግድ እንደ ተቋም
በሻሸመኔ አካባቢ የኮንትሮባንድ ንግድ ተቋማዊ ቅርጽ መያዙን የሚያሳይ መረጃ ጠቆመ፡፡ ሌሎች በኮንትሮባንድ ንግድ እንዳይሳተፉ የሚከለክለው ሕግ የሚጸናባቸው ከህወሃት ራቅ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸው ድርጊቱን “ማስመጥ” አሰኝቶታል፡፡ ዜጎችም “የኮንትሮባንድ ንግድ ትርጉሙ ምን ይሆን?” እያሉ ነው፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ በህጋዊነት በተለይ የሚፈጸመው ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም ላለፉት 25 ዓመታት በግፍ እየገዛ ባለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ህወሃትና በአፍቃሪዎቹ መሆኑን በማረጋገጥ የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በዓይን ምስክርነት የታዘቡትን በፎቶ የተደገፈ መረጃ ልከውልናል፡፡ ዜናውን እማኝ ዘጋቢው ይላኩት እንጂ በድፍን አገሪቱ ህወሃቶች፣ የህወሃት አገልጋዮች፣ የህወሃት ሽፋን ሰጪዎች፣ ነባር ተጋዳላዮች፣ ተላላኪዎች፣ ወዘተ በዚህ ሥራ እንዲሰማሩ … [Read more...] about የኮንትሮባንድ ንግድ እንደ ተቋም
ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ ኤሊ ውሃ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም ስለተፈጸመው ግድያ መረጃ ልከውልናል፡፡ ከመረጃ አቀባያችን ጋር በተደጋጋሚ በተላላክነውና ባቀረብነው በርካታ ጥያቄዎች መሠረት ያገኘነው መረጃ ይህንን ይመስላል፡- እጅግ ዘግናኝ የሚባለው ግድያ የተፈጸመው ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ በሚገኘው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የእማኝ ዘጋቢው በራሳቸው አገላለጽ እንዲህ ዘግበውታል፡- (የላኩልን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም ሲሆን ወዳማርኛው እንዲህ መልሰነዋል) “ወንጀሉ የተፈጸመው ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ በኤሊውሃ ከተማ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ ነው፡፡ የተቃጠለው ልጅ ወልዱ ይባላል፡፡ በ(ፕሮጀክቱ) … [Read more...] about ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
“ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ላይ ኅብረተሰቡ የሚያሰማው እሮሮ ኤሌክትሪኩ መጥፋቱ ብቻ አይደለም፡፡ መብራቱ ሄዶ ሲመጣ የሚያደርሰው ጥፋት የትየለሌ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል መጠን ከመደበኛው ውጭ ከፍና ዝቅ ሲል የሚያደርሰው ጥፋት ቤት ይቁጠረው፡፡ ማቀዝቀዣው፣ ቴሌቪዥኑ፣ አምፖሉ፣ ልዩ ልዩ "ቻርጀሮች" የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ተቃጠሉብን የሚል የሕዝብ እሮሮ በየጊዜው ይሰማል፡፡ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አገልግሎት የማይሰጠውን "905" ላይ ደውላችሁ አስመዝግቡ ከማለት ያለፈ መልስ የለውም፡፡ "የኤሌክትሪክ ምሰሶው ሊወድቅብን ነው፣ ዘሟል፣ ኧረ ድረሱልን" እያሉ ለሚወተውቱም ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳልተቻለም ማስረጃ ከሚሆኑ ትዕይንቶች (በፎቶዎቹ የሚታዩት) መካከል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እንደራሴ አካባቢ ያሉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች … [Read more...] about “ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
ሰቆቃ በማዕከላዊ
‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡›› አበበ ካሴ እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት … [Read more...] about ሰቆቃ በማዕከላዊ
የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አህዛዊ መረጃ በመዲናዋ ውስጥ 1671 የሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ መረጃው ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ኮሌጅ መሰናዶ ድረስ ያሉትን የግል ትምህርት ቤቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ ትምህርት ቢሮው በ2006 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ወራት ላይ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፣ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሚሆኑ ተማሪዎች ይማራሉ፡፡ ትምህርት ቢሮው የ2007 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ አህዛዊ መረጃ አጠናቅሮ በድረ ገፁ ይፋ ባያደርግም ቁጥሩ ካለፈው የትምህርት ዘመን ሊልቅ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ከሚጠናቀቀው የሚሊንየሙ የልማት ግቦች አንዱ የሆነውን ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ዕድሜቸው ለትምህርት ለደረሱ ህፃናት የማዳረስ ዕቅድ ያላት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚሊንየሙን የልማት ግቦች … [Read more...] about የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
ክብር ከደቡብ አፍሪካ ለደራርቱ ቱሉ
በኢትዮጵያም ሆነ በጥቁር አፍሪካ ኦሊምፒክ ታሪክ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ ቱሉ ባለፈው ሳምንት ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበለች፡፡ ከኦሊምፒክ በተጨማሪ በዓለም ሻምፒዮንም ሆነ በተለያዩ አህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ቁንጮ በመሆን ታላቅነቷን ማስመስከሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ለመጀመርያ ጊዜ በባርሲሎና ኦሊምፒክ (1984 ዓ.ም.) በ10,000 ሜትር ተወዳድራ የወርቅ ሜዳልያውን ያገኘችው የቅርብ ተፎካካሪዋንና የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ የነበራትን ደቡብ አፍሪካዊቷን ኤሌና ሜየርን በረዥም ርቀት ጥላት በማሸነፍ ነበር፡፡ ፎቶግራፉ ደራርቱ የክብር ዶክትሬቷን ከተቀበለች በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሐኔኮም (በግራ) እና ከዩኒቨርሲቲው ሬክተር ፕሮፌሰር ብሪያን አ ኮኔል ጋር ሆና ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ፎቶ በባርሴሎና ኦሊምፒክ … [Read more...] about ክብር ከደቡብ አፍሪካ ለደራርቱ ቱሉ
ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
ያለሁት ካናዳ፤ ቶሮንቶ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ትላንት ማታ አንዱ የኢትዮጵያ ምግብና ዳንኪራ ቤት ለማምሸት ከዘመድ እና ሰሞኑን ከተዋውቅኳቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ሄድኩ፡፡ ቤቱ በአንድ ሰሞን በአንድ ዜማ እጅግ ታዋቂ ሆኖ በነበረ ወጣት ድምፃዊ የሚተዳደር ነው፡፡ ስገባ ወጣቱን ድምፃዊ አየሁት፡፡ እንግዶቹን ዞር ዞር እያለ ሰላም ይላል፡፡ ከማውቀው ወፍሯል፡፡ ዘመናዊም ባህላዊም ዘፈን በዲጄ ሲለቀቀቅ ጠባቧ ቤት ንዝረቷ ይጨምራል፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰአት ገደማ ቤቷ ሞላች፡፡ ከሀበሻ ውጪ ሌላ ዘር ያለው ሰው ግን አላየሁም፡፡ ስድስት ሆነን ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ጀርባ ባለጌ ወንበርና ጠረጴዛ ላይ አንዲት በህንድ ዘዬ የተሰራ “እዩኝ እዩኝ” ሆደ- ግልብ ብልጭልጭ ልብስ የለበሰች ረጅምና ቀጭን፣ ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣ ቢራ ትጠጣለች፡፡ አላግባብ ተከምሮ ሳር ከጫነ መኪና … [Read more...] about ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
ጠመዝማዛ ባላዎች ላይ የቆመው ክፍል በደደሆ ዛፍ ቅጠል የተሠራ ጣሪያ አለው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከ20 የማይበልጡ ትንንሽ ድንጋዮች ላይ ኩርምት ኩርምት ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ ደብተሮቻቸውን በየጉልበታቸው ላይ አድርገው ከፊት ለፊታቸው ያለውን መምህር ያዳምጣሉ፡፡ ከመሬት ብዙም የማይርቀው የክፍሉ ጣሪያ መምህሩን ጐንበስ ብሎ እንዲያስተምር ግድ ብሎታል፡፡ መምህሩ ለማለቅ በተቃረበ ነጭ ጠመኔ ያረጀ ሰሌዳ ላይ ቁጥሮች እየጻፈ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሒሳብ ያስተምራል፡፡ የክፍሉ ጣሪያ በሳሳበት አቅጣጫ የተቀመጡ ተማሪዎች ጸሐይ ይመታቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ድንጋዩ ጐርበጥ ሲያደርጋቸው ወደ አንድ ወገን ገደድ እያሉ ለመመቻቸት ይጣጣራሉ፡፡ እነዚህ በዛፍ ጥላ ስርና በዳስ የሚማሩ ተማሪዎች የመኪና ድምጽ በሰሙ ቁጥር አንገታቸውን አጠማዘው ይመለከታሉ፡፡ ግድግዳ በሌለው ክፍላቸው አቅራቢያ … [Read more...] about የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች










