የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው "ለሚ ፓርክ" የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል። ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው። አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ "ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው" ብሏል። ፕሮጀክቱን በየመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦ ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ለሚ ፓርክ የሚኖሩት:የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች … [Read more...] about ሁለተኛው መስቀል አደባባይ
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅንጅት በተከናወነ ኦፕሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡ ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና በተለያየ መልኩ ባደረገው ጥናት መነሻነት በየካ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሺሻ በሚጨስባቸው ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ እርምጃ ተወስዷል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 3 በተለያዩ አካባቢዎች በአጠቃላይ … [Read more...] about ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ
ድሮ ገና ከዓመታት በፊት በ12 ዓመቱ ነበር ሰውን የመርዳት ፅንስ በትንሽ ልቡ ውስጥ የተጸነሰው። ሳድግ የራሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኖሮኝ ሰዎችን እረዳለሁ እያለ ያወራ ነበር። የእድሜ አቻዎቹ ዶክተር፣ ኢንጅነር፣ ፓይለትና ሌሎችም እሆናለሁ በሚሉበት ለጋ እድሜ የሱ ትንሽ ልብ መሻት አድጎ ሰውን መርዳት መቻል ነበር። ዛሬም በሕይወት ጉዞው ላይ በብዙ ካደገም በኋላ የየቀን ንግግሩ የዘወትር ውዳሴው “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የሚል ቃል ነው። ሰው ስለሆነ ብቻ ሰው ይረዳልና። የራስን ሕይወት ትቶ ስለሰው በሚኖረው ባሕሪው ከሰዎች መካከል ይለያል። የሥጋ ሕመሙ የነፍሱን ቁስል በሻረለት መልካም ሥራው ይታወቃል። ድንቅ የመልካምነት ምሳሌ፣ የመቻል አብነት፤ የደግ ልብ ጌታ ነው። የጥሩዎች ዕንቁ የደጎች አውራ ነው። ብዙዎች በተለያዩ ጊዜያት ደጋችን ነህ ሲሉ በይፋ … [Read more...] about “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ
የወሲብ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሥርጭት ከኢትዮጵያ እንዲታገድ ዘመቻ ተጀመረ
በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ በአንድ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ። በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።በአንድ ግለሰብ ተነሳሽነት የተጀመረዉ እንቅስቃሴዉ አሁን ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በሆኑ 15 በሚደርሱ ሌሎች አባላትም ድጋፍ ማግኘቱን ጣቢያችን ሰምቷል። የማስታወቂያ ባለሙያ በሆነዉ አለማየሁ አጥናፍሰገድ በተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድህረገጾቹን ለማሳገድ እንዲሁም በህጻናት እና ወጣቶች አእምሮ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና በማስተማር እና ማህበረሰብን የማንቃት እንቅስቃሴ አንድ ብሎ መጀምሩን ለብስራት ራዲዮ … [Read more...] about የወሲብ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሥርጭት ከኢትዮጵያ እንዲታገድ ዘመቻ ተጀመረ
“ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
የትህነግ 10 በደሎች - በተለይ በአማራ ሕዝብ! "ትህነግ"... (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ። የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ። 1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ … [Read more...] about “ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
በሕወሓት ማጎሪያና ጭፍጨፋ እስር ቤቶች የተፈፀመው ዘግናኝ ታሪክ እንደ ሚከተለው ይቀርባል። እንደ አቶ ገብረ መድኅን ገለፃ በወቅቱ ሕወሓት ሓለዋ ወያነ (የወያኔ እስር ቤት) ወይም 06 (ባዶ ሸድሸተ -ባዶ ስድስት) ብሎ በማቋቋም በተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ማጎሪያና ጭፍጨፋ ‘ካምፖች’ ነበሩት። እነዚህን የማጎሪያና የጅምላ የመጨፍጨፊያ ‘ካምፖች’ የመሰረተው ህቡር ገ/ኪዳን በሚባል ታጋይ (በኋላ በስኳር ኮርፖሬሽን ግዥ ክፍል ቡድን መሪ እና የሕወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አባል ሆኖ ሲሰራ የነበረ) ነው፡፡ አቶ ገብረ መድህን አርአያ እያንዳንዱ እስር ቤት (ሓለዋ ወያኔ 06) የተቋቋመበት ዓላማ የወልቃይት አማሮችን በጅምላ ለመፍጀትና የሕዝቡን መሬት ለመንጠቅ፣ ሕወሓትን የሚቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን ለመግደል እንደሆነ ያብራራሉ። የግለሰቡ ገለፃ እንደሚከተለው አጥሮ ይነበባል። 1) … [Read more...] about የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
በሴቶች ጭፈራ ደምቆ በወንዶች የሚታጀበው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራን ለማስተዋወቅ የሁለት ቀን ፌስቲቫል በደሴ ከተማ ተካሂዷል። እራሷን ተሰርታ ወለባ ስጋለች፣ እንሶስላ ሙቃ ሎሚ ጨብጣለች፣ ያች ያገሬ ልጅ እሷዉ ትሆናለች። ሲሉ ጨዋታውን ደመቅ ያደርጉታል የወሎ ወይዛዝርት። ታዲያ በዚህ ጭፈራ ጊዜ ወንዶቹ ሴቶቹን ተቀላቅለው ጭፈራውን ደመቅ ያደርጉታል። አኾላሌ በሃይማኖታዊና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ክብረ በዓላት የሚከናወን ብዙ ጊዜ ጥር ወር ላይ በአርሶ አደሩ የዕረፍት ወቅት፣ በመተጫጫና ጋብቻ እንዲሁም የመዋቢያ ጊዜ የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። በአብዛኛው በወሎ በተለይም በተውለደሬ የሚከወነው ተዉኔት አዘል ባህላዊ የወጣቶች ጭፈራ ሃይማኖት ሳይለይ በክርስትናም በእስልምና ተከታዮችም ይካሄዳል። አሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የኾነ የመከወኛ አጋጣሚዎች እና ወቅቶችም … [Read more...] about ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ። በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል። በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት … [Read more...] about መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
“እናቴን ገድለው በጅብ አስበሏት”
አይሻ ሰይድ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪ ናት። በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የደረሰባትን ግፍ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተናግራለች። "አሸባሪው ህወሓት በአካባቢያችን ላይ ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ያገኘውን ሁሉ መግደል ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪም በመደናገጥ እግሩ ወደመራው ሸሸ። እኔም የ75 ዓመት አዛውንት የሆነችውን እናቴን ይዤ ለመሸሽ ሞከርኩ። ነገር ግን አቅሟ ደከመ ብዙም መጓዝ አልቻለችም። አውሬዎቹ የአሻባሪው ታጣቂዎች ደረሱብን። እናቴን መንገድ ላይ ገደሏት፤ እኔ እንደምንም ብዬ ነብሴን አተረፍኩ" ትላለች አይሻ "ሁሌም ሀዘኔ ከውስጤ እንዳይወጣ የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር መተኪያ የሌላት እናቴን እንኳን መቅበር አለመቻሌ ነው" የምትለው አይሻ፤ የእናቷን አስከሬን ጅብ እንደበላው ትናገራለች። "... እናቴን … [Read more...] about “እናቴን ገድለው በጅብ አስበሏት”
ከልጅ እጅ ጠብቀው፥ ከሚያገኙት ቀንሰው ለወገን ጦር ድጋፍ የቸሩ እናት
ወ/ሮ ውዴ በለጠ ይባላሉ። ነዋሪነታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ነው። ሀገሬ በችግር ውስጥ ሆና እኔ በድሎት አልኖርም በማለት ልጆቻቸው ለቀለብ ብለው ከሚሰጧቸው ጥቂት ገንዘብ እየቆጠቡ ለሰራዊት አባላት በግላቸው ስንቅ አዘጋጅተው አቅርበዋል። ወ/ሮ ውዴ የልጆቻቸውን እጅ ጠብቀው የሚኖሩ እናት ቢሆኑም ለህልውና ዘመቻ የሀገርን ክብርና የወገንን ህልውና ለማስጠበቅ ግንባር ለተሰለፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ይሁንልኝ ሲሉ 3 ኩንታል በሶ አዘጋጅተው ድጋፍ አበርክተዋል። ግለሰቧ “ከዚህ በፊትም ልጆቼ በቻሉት አቅም ግንባር ለዘመቱ ወገኖቻቸው ድጋፍ አድርገዋል” ይላሉ። “አሁን ደግሞ የኔ ተራ ነው፤ ከወር ቀለቤ እየቀነስኩ በሰበሰብኳትና ልጆቼ በሰጡኝ ጥቂት ገንዘብ ይህንን አድርጌያለሁ” አሉ። እኔ በሰላም ወጥቼ እንዲገባ እነሱ ህይወታቸውን … [Read more...] about ከልጅ እጅ ጠብቀው፥ ከሚያገኙት ቀንሰው ለወገን ጦር ድጋፍ የቸሩ እናት