“የሚዲያው” ባለቤት በሼራተን የቪአይፒ ተስተናጋጅ ሆኗል
የ“ሹክሹክታ” (ጎሲፕ ወይም ሐሜት) አምራች በመሆኑ ትልቅ ዋጋ የተሰጠውና በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓመቱን ሽልማት የለገሰው ዘ-ሐበሻ ትላንት “በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ” ሲል ያሰራጨው ዜና ፍጹም ሃሰት መሆኑንን ዩኒቨርሲቲው ባሰራጨው የማስተባበያ ዜና ይፋ አደረገ። የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት የዚሁ “ሚዲያ” ባለቤት ነው የሚባለው ሔኖክ ዓለማየሁ በሸራተን አዲስ በልዩ የዕንግዳ መስተናገጃ /ቪአይፒ/ ሲስተናገድ እንደሰነበተ አስታውቀዋል።
“ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በተነሳ ብጥብጥ ምክንያት ሁለት ተማሪዎች በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል” በማለት ዘ-ሐበሻ የሐሰሰት ዜናውን ሲረጭ በስምንት ሰዓታት ውስጥ 556 ሰዎች ስሜታቸውን የገለጹ፣ 197 አስተያየት የሰጡ ሲሆን 146 ሰዎች ይህንኑ የፈጠራ ዜና አሰራጭተዋል።
ዜናው በመዘበጉ ምክንያት ሊፈጥር የሚችለውን ያልተፈገ ችግር የተረዳው ዩኒቨርሲቲም የሚከተለውን በማውጣት የዜናውን ሐሰተኝነት አረጋግጧል፤
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ረብሻ ተነስቶ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሽከረከረው መረጃ ውሸት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። በዩኒቨርሲቲያችን ምንም የሞተ ተማሪ የሌለ በመሆኑ በውሸት መረጃ እንዳትሸበሩ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
Universiti Haramaya keessatti jeeqqumsii ka’ee barataan akka midhamee fi du’ee marsaaneeti irratti naanna’uu sobbaa fi kan dhugaa irraa faggattedha.
(ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ)
Universiti Haramaya keessatti barataan lubbun isaa darbittee akka hin jiree hubbatanii akka tasgabooftan ergaa keenya dabarsu barbaannaa.
(Universiti Haramayaa)
ስማቸው እንዳይጠቀስ ያሳሰቡ የመንግሥት ባለሥልጣን ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳሉት “ዘ-ሐበሻ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የመገናኛ ዘዴዎችና የፌስቡክ አተራማሾችን የመለየት ሥራ ተጠናቋል። አገር ውስጥ ያሉትም ሆነ ከአገር ውጭ ያሉት በሕግ የሚጠየቁበት አግባብ በቅርቡ ይፋ ይሆናል። በዚህ ጉዳይ ሕዝባችን እፎይ ብሎ የሚተነፍስበት ቀን ሩቅ አይሆንም። ጉዳዩ የሕግ ብቻ ይሆናል። ጠንካራ ቅጣት እንደሚኖር ጥርጥር የለም” ብለዋል።
የሐሰት ዜና፣ ሐሜት፣ ወዘተ በማሰራጨት ከሚገኘው ጥቅም ራሱን እያበለጸገ ያለውን የዘ-ሐበሻ አዘጋጅ ሸራተን ቪአይፒ አሁን ብቻ ሳይሆን ለሁለተኛ ጊዜ ስለመቀመጡ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን እዚያ ማስቀመጥ የፈለጉት አካላት ብቻ መልሱን ሊሰጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ “የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!” ከዚህ ቀደም ባነበበው ሐተታ ላይ ዘ-ሐበሻ በወቅቱ የፈጸመውን ሥነምግባር የጎደለውንና ግጭት ቆስቋሽ መረጃ ከሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ሽልማት ጋር በማያያዝ ዘግቦ ነበር። ዘገባው እንዲህ ይነበባል፤
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገዳዮች መሪ ነው” የሚለውን ጨምሮ በርካታ የነቀፌታና ጥላቻ አዘል ትችት በዶ/ር ዐቢይ ላይ የሰጡት ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው በማለት ዘ-ሃበሻ በፊትለፊት ገጹ መዘገቡና ይህንኑ ተከትሎ የማኅበራዊ ገጾች ዜናውን ማራባታቸው ቀውስ ፈጥሮ ነበር። ዘ-ሐበሻ “ዜናውን” ያሰራጨው ከሳተናው ድረገጽ ላይ በመጥቀስ ነው። ሁለቱም ድረገጾች “እህትማማች” እንደሆኑ እዚህ ላይ ልብ ይሏል።
ባልተጣራ ምንጭ ዶ/ር ደረጀ በሰነዘሩት ትችት ሳቢያ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው የሚለው ዜና “ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በዐቢይ አህመድ ከተቀነባበረባቸው የሞት ድግስ መትረፋቸው እየተሰማ ነው። ትናንት እሁድ ጭንብል የለበሱ ገዳዮች በመኪና ደፍጥጠው እንዲገሏቸው የተጠነሰሰው ሴራ የሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎችን ህይወት እና የመኪና ግጭቶችን በማስተናገድ ተጠናቋል” በሚል ሳምሶን ያይሉ በሚባሉና በሌሎች የማኅበራዊ ገጽ “አርበኞች” ተሰራጭቶ ነበር።
ዘ-ሐበሻ “ምንጮቼ” ያላቸው ክፍሎች እነዚህ ይሁኑ ሌላ በግልጽ ባይታወቅም፣ ዜናው መሰራጨቱን ተከትሎ በዶ/ሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ባልደረቦች ዘንድ ቀላል የማይባል ችግር እንደፈጠረ ለማወቅ ተችሏል።
ይህንን የፈጠራ ዜና ለማሰራጨት የተፈለገበት ልዩ ምክንያት ይፋ ባይሆንም፣ ዜናው አገሪቱ ውስጥ መረጋጋት እንዳይፈጠር ሆን ብለው በጀት መድበው የሚሠሩ አካላት ያደረጉት ለመሆኑ ግን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፤ ጥቂት የማይባሉም ቁጣቸውን ገልጸዋል።
ሃሰተኛ ዜናዎችን እያሳደዱ ከሚያመክኑ ዜጎች መካከል አንዱ የሆነው ኤሊያስ መሠረት የፈጠራው ዜና መሰራጨቱን ተከትሎ ዜናውን እያራገቡ ላሉ፣ በዜናው ለተደናገጡ ወገኖች ምላሽ ይሆን ዘንድ ተጎዱ የተባሉትን ዶ/ር ደረጀ በማነጋገር ትክክለኛውን መረጃ አሰራጭቷል። ይህንን ነበር ያለው፤ “ዶ/ር ደረጄን ቅድም ስለዚህ ዜና ጉዳይ ሳወራቸው (እንዲህ ብለውኛል) “የሚገርምህ ምናለ ቲቪ ላይ ቀርቤ ባላወራሁ ነው ያሰኘኝ። ቤተሰብ እና ጓደኞቼ በጣም ነው የደነገጡት። ይህ ጭካኔ ነው። ሕዝቡ ግን የሃሰት ዜና እነማን እያሰራጩ እንደሆነ በዚሁ ይገንዘብ” ብለውኛል።
ዶ/ር ደረጀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባሳለፉት ትዕዛዝ መሠረት ማስክ ባጠለቁ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በመኪና ግድያ ሊፈጸምባቸው እንደነበር ምንጮች ጠቅሶ የዘገበው ድረገጽ ሳተናው ሲሆን እህት “የሙያ አጋሩ” ዘ-ሐበሻ ደግሞ ዜናውን እንዳለ አውርዶታል። ሆኖም ዜናው የውሸት እንደሆነ ይፋ ከተደረገ በኋላ ዘ-ሐበሻ ይህንን ብሎ ነበር፤ “በሳተናውና በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ በዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ የሚለው ዜና በስህተት የተለጠፈ ስለሆነ አንባቢዎቻችንን ስለተደረገው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ደረጀ ምንም የደረሰባቸው አደጋም ሆነ የአደጋ ሙከራ አለመኖሩን በይቅርታው ሃረግ ውስጥ አላካተተም።
ዜናው የፈጠራ ወይም የሃሰት ሆኖ ሳለ ዘ-ሐበሻ “በስህተት የተለጠፈ” ሲል ስህተቱን በማሳነስና በሌላ ሶስተኛ ወገን እንደተደረገ አድርጎ ማቅረቡ ይቅርታውን ሰባራ እንደሚያደርገው ለሙያው ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ። የተሰራጨውን የሃሰት ዜና ተከትሎ እውነተኛ ቀውስ ቢደርስ፤ ግለሰቡ ጥቃት ደረሰባቸው በሚል የተነሳሳ ኃይል አፀፋ ቢመልስ፤ ወዘተ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው ሚዲያ ማስተባበያውን ሃሰተኛውን ዜና ባሰራጨበት መጠንና ድምጸት ልክ ሊሠራው በተገባ ነበር።
የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ በቅርቡ አትላንታ በተካሄደበት ወቅት የዘ-ሐበሻ አዘጋጅ “ሌት ተቀን እንቅልፉን በመሰዋት መረጃ በመስጠት ተመስግኗል” በማለት ገድለ ሔኖክን የተረከው ክንፉ አሰፋ ነበር። አቶ አበበ ባልቻ ሽልማት ያበረከተለት የዘ-ሐበሻ ባለቤት ከተወደሰበት ሥራው አንዱና ትልቅ ተደርጎ የተወሰደው ከሐሰተኛ ዜና ረድፍ የሚመደበው “ሹክሹክታ” የሚለው ዝግጅቱ ነው። ይህ በየማኅበራዊ ገጾች ላይ የሚሰራጨው መረጃ አልባ ሃሜቶችን መሠረት ያደረገ ዝግጅት ለሽልማት የሚያበቃ መሆኑ የአዘጋጅ ኮሚቴ (ፌዴሬሽኑም ካለበት) የሽልማት መፈርት፣ ሽልማቱ ምንን ለማበረታት እንደሆነና ዓላማው ምን እንደሆነ ሽልማቱን ተከትሎ ሊቀርቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ናቸው። ወይስ በያዝከው የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ቀጥልበት ማለት ይሆን? (በርግጥ የዶ/ር ደረጀ ሃሰተኛ ዜና ከመውጣቱ በፊት ሽልማቱ መሰጠቱ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ይህ የዘ-ሐበሻ ሹክሹክታ ዓምድ በቅርቡ ጋብቻውን የፈጸመ የመብት ተሟጋችን መረጃ ያለባለቤቱ ፈቃድ ከሠርጉ አዘጋጅ በወዳጅነት ስም በመውሰድ ካሰራጨ በኋላ በባለጉዳዩ ተቃውሞ ከዩትዩብ ስለመውረዱን ጎልጉል መረጃ አለው)።
በሸራተን ሆቴል ቪአይፒ የሚኖረው የዘ-ሐበሻው ባለቤት ሔኖክ ዓለማየሁ ለምን ዓላማ እንደዚህ ዓይነት እንክብካቤ እንደሚደረግለት ባይታወቅም ጎልጉል ከሸራተን-አዲስ ባገኘው መረጃ ለሔኖክ ልዩ የመኝታ ክፍል፣ የግል ኢንተርኔት፣ መኪናና ሾፌር እንዲሁም አስፈላጊ ወጪዎች ተመድቦለታል። በሼራተን ውስጥ ከሚገኙት እጅግ ውድ ባሮች በ“ሸራተን ጋዝላይት”ም ሆነ “ኦፊስ ባር” እየፈረመ የሚጠቀም ሲሆን ነዋሪነቱ ሆላንድ የሆነ ወዳጁም አብሮት እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል። ስም መጥቀሱ አስፈላጊ ባለመሆኑ ለጊዜው ትተነዋል።
የኢትዮጵያን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ያለ ተቀናቃኝ የሚፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ግፍ እየፈጸመ ሲመራ የነበረው ጌታቸው አሰፋ እና መቀሌ ከከተሙት ጥቂት የህወሓት አድራጊ ፈጣሪ የበረሃ ወንበዴዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበራቸው የሸራተን ሰዎች ለምን ጉዳይ ዘ-ሐበሻን እንደመረጡና እያደለቡት እንዳሉ ባይታወቅም የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ግምታቸውን ሰጥተዋል።
እንደ እነዚሁ ክፍሎች ከሆነ የሸራተን አውራዎች ከሚጠረጠሩበት በርካታ ጉዳዮች በተጨማሪ ከፍተኛ የርስበርስ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ከሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ እስር በኋላ በዙሪያቸው ባሉ አገልጋዮቻቸው መካከል ሰላም የለም። እናም አንዱ ሌላውን ለመዋጥና መከላከያ ወረዳ ለማበጀት የዘ-ሐበሻ ሹክሹክታ ሳይፈለግ እንዳልቀረ ግምታቸውን ሰጥተዋል። በመሆኑንም የግል ጥቅማቸው እስከተሟላላቸው የአገር ጉዳይ ምንም የማይጨንቃቸው እንደ ሔኖክ ያሉ ስግብግቦች ለእንደነዚህ ዓይነት ቁማርተኞች መጠቀሚያ በመሆን ያገለግላሉ።
በአገራችን የለውጥ እንቅስቃሴ በመንግሥት ደረጃ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በዘመነ የትግራይ ነጻ አውጪ የ27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ ዘመናት እምብዛም የማይታወቀው የሐሰት መረጃና ዜና በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም በፌስቡክና ዩትዩብ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ብዙዎቻችን የምንመሰክረው ጉዳይ ነው። በእነዚህ የሐሰት መረጃዎች አማካኝነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ክቡር የሰው ልጆች ህይወት እንደጠፋ፣ ንብረት እንደ ወደመ፣ ሰላም እንደ ደፈረሰ፣ አገራችን እንደታወከች፣ ወዘተ የሚክድ የለም።
የሃሰት መረጃ ለምን በረከተ? ከአፋኙ ዘመነ ህወሓት ይልቅ አሁን ለምን ሚዲያው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በሃሰት መረጃ ተሞላ? በዕቅድ የሚካሄድ የዲጂታል ጥቃት ውጤት ነው? ወይስ እንደው በዘፈቀደ የሆነ ተግባር ነው? በርካታ ገንዘብ የሚፈስበት ፕሮጀክት? ወይስ ጥቂት ግለሰቦች ከማኅበራዊ ሚዲያ ከሚገኘው ትርፍ ራሳቸውን ለማበልጸግ የሚያደርጉት የግል ፍላጎት ላይ የተተከለ የሳንቲም ለቀማ አባዜ? አገር ለማፍረስ የሚካሄድ የተቀነባበረ ተግባር? ወይስ የመንግሥትን ሸፍጥ ለማጋለጥ የሚደረግ የሚዲያ አርበኝነት? የለውጡን እንቅስቃሴ ማክሸፍ ዓላማቸው አድርገው በተነሱ የሚካሄድ ረቂቅ ሤራ? ወይስ “እውነትን እንዘግባለን” በሚል ፍካሬ ሳያውቁት የሌሎች ዓላማና ግብ ያላቸው ሴረኞች ቀጥተኛ መጠቀሚያና ሰለባ የመሆን ውሳኔ? ወዘተ። ጥያቄው ብዙ ነው። ጠያቂዎቹም በርካታ ናቸው።
ይህ ብቻ አይደለም ሌላም የጥያቄውና የአዙሪቱ መነሻ አለ። የትግራይ ነጻ አውጪ ባላሰበው ሁኔታ አገሪቱን እንዲነዳ ዕድል ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ መሪዎቹ ባደባባይ ህዝብን ሲቀጥፉ፣ ዓይናቸውን ታጥበው ሃሰታቸውና ሸፍጣቸውን በሌላ ሸፍጥ ሲያስተባብሉ፣ አገርን በሚያክልና አገራዊ እሴት ባላቸው ታሪካዊ ንብረትና ማንነት ላይ ሲሻቀጡ በነበረበት የ27 ዓመታት የክሽፈት ዘመን ለምን የሃሰት ዜናን የማስተባበል ተቃራኒ ሤራ ልክ አሁን ባለው ደረጃ አልተስፋፋም? ዛሬ በንፅፅር ሚዲያው ክፍት በሆነበት ዘመን የጠራ መረጃ ለህዝብ ማድረስ እየተቻለ ዓላማ ያላቸው የሃሰተኛ ዜና ዘገባዎች ለምን ጎልተው ወጡ? ማንስ ነው የሚያመርታቸው? በምን ያህል የድርጅትና የስትራቴጂ ነዳፊዎች ዘገባዎቹ ተመርተው ይከፋፈላሉ? ማን ላይ ነው መሠረታዊ የማነጣጠሪያ መውጊያቸው የሚያርፈው? አንዳንድ ቁልፍ ጉዳዮች ሲነሱ እንዴት ተጠልፈው ወደ ሤራው ቋት እንዲገቡ ይደረጋሉ? የሚሉትን ዜጎች በጥሞና የመመርመር ፈቃደኛነቱ ካላቸው ቲያትሩ ዕርቃን የሚሆን የተገለጠ ምሥጢር ነው።
ዓላማቸው አገር ማውደም የሆኑት “ዲጂታል ወያኔዎችም” ሆነ “እኔ ካልበላሁት እደፋዋለሁ” በሚለው ጽንፍ ውስጥ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር ሚዲያ የመሠረቱ የጃዋር ድርጎ ተሰፋሪዎች እንዲሁም የሄኖክ ዓይነቶች ሆደአደሮች የሐሰት መረጃ የሚሰራጩበት ዋንኛ ዓላማቸው “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል” የሚለውን ተግባራዊ ለማድረግ ነው!!
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
gi Haile says
ማፉያ ድርጅት ከባንክ ዘረፋ ጀምሮ ጠቅላይ ምንስትር የሆነበት የሽፍቶች ድርጅት በከሰረና በወደቀ የምራል ውድቀት ውስጥ ከገቡ በኋላ የከሰረና የተበላሸው ኄሊናቸው ሽሾኣልና የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ደንዝዘዋል። በወያኔ የዘረፈተ ሐብት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ የበላይነት የተቆጣጠሩት በወንጀል ነው። አሁንም የወያኔ ሐብታሞች በሰረቁት ሐብት አገራችንን ለመበታተን ቸሚያደርጉት የሐሰትና የፈጠራ ወሬ የ44 አመት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በለሙያነታቸውን ያስመሰክራልና ከዚህ ከወንበዴ ድርጅት ጋር ቃል ኪዳን የገባ ሁሉ የተረገመ ብቻ ነው። በሰው ደም የሰከረ ግንባር ጋር የሚሰሩ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። የሐሰት ወሬ ለወያኔ መሪዎች ሱስ ነው። ደርግን የጣሉት በሐሰት ፕሮፓጋንዳ እንጅ እውነቱ ሌላ ነው። በዶ/ር ኣቢይ ላይ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ዋና ምክንያት የወያኔን የውስጥዋን ገበና የሰራችውን አለም አሸፍ ወንጀልና አፈና ከሚያውቁት አንዱ ስለሆነ ከመጥፋታቸው በፊት የስም መጥፋት ዘመቻ አራማጆችን መመልመል አዲሱዘዴኣቸው ነው። ከማፊያ ድርጅት ምንም መልካም ነገርን መጠበቅ ኣንችልምና እነ ሄኖክ አለማየሁ ኢትዮጵያን ለብር ብሎ ከካደ መጨረሻው ውድቀትና ውርደት ነው። ቸሐሰት ኣባት የወያኔ የጉዲፈቻ ልጅ ነውና ሕግ ትክክል ሊያገባው ይገባል።
Berhan Tamiru says
Please shut up!!! You are a bunch of morons. People are dying in daily & you have the fucking nerve to criticise the Habesha??? Your idiotic blind support for spineless Abiye is completely wrong. Get you stupid fact checked & focus on the real issues rather than running a shameless smearing campaign. Idiots
Efrem says
I feel sorry to hear the frequently spoken press release from u in parallel to the killings and universities students are sheltering with in the Orthodox churches. how u put it as if the treason are not out of the hands of the country peace keepers.
I wish u refrain from playing with the life’s of students from poor Ethiopians mothers.
Boldly speaking why don’t u let theme back hometown.
if u can’t why don’t u resigned Rather than sending curfews again time again.
l will let u tries to put yourselves in to mothers handover curfews
bua-yalew says
ጎልጉል
በጣም ጥሩ ሥራ ነው የውሸት ዜና ፈጣሪዎችንና አሰራጮን ለሕዝብ ማሳወቅ፤ በተለይ ዘሐብሻ የሌሎችን ዜና በመለጠፋን ጭር ካለም ዜና በፍጠር ካልሆነም የከተማ ተባራሪ ወሬና ሃሜትን ዜና ብሎ ያሰራጫል፤ ትክክለኛነቱን ማጣራትም ሆነ ምን ሊያስከትል ይችላል የሚል የሙያ ሃላፊነት ጨርሶም የለም፤ ከማስታወቂያ የሚያገኘ ገንዝብ ብቻ ነው የሚፈልገው፤ ነፍሱን አይማረው ጎዶሎው መለስና ጠቅላላ የውያኔ ስርዓት እንዲህ አይነት ግብረገብ የለላቸ ሆዳም ገንዘብ አምላኪዎች ፈልፍሎ አሳድጎ ለቀቃቸው