የፖለቲካው መዋቅር ውስጥ ያሉትን ሌቦች የመያዙ ተግባር ይጠናከር
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።
ይህ የተገለፀው በቅርቡ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ስራውን በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ የኮሚቴው አባላት ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
በአዲስ አበባም የአርሶ አደር ልጆች ወይም የልማት ተነሽ ሳይሆኑ የሆኑ በማስመሰል በሐሰት ሙስና የሰሩ ግለሰቦችም ተለይተዋል ብለዋል የብሔራዊ ኮሚቴው አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ።
175 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታና የኮንዶሚኒየም ቤት ምዝበራ የፈፀሙ እንዲሁም በፍትህ ዘርፉ ስልጣናቸውን በመጠቀም ከግለሰቦችና ከንግድ ተቋማት ጋር ለግል ጥቅማቸው ሲሰሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም ተለይተዋል ተብሏል።
ኮሚቴው ሶስት ንዑስ ኮሚቴዎችን ማለትም የህግ፣ የመረጃ እና የፋይናንስ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም እቅድ አውጥቶ ስራ መጀመሩንም የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።
በመንግሥት አግልሎት አሰጣጥ፣ በፋይናንስና ግዥ፣ በፍትህ ስርዓቱ እና በመሬት አስተዳደር እንዲሁም በመሰረታዊ ፍጆታ አቅርቦት ዘርፎች ላይ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ይስተዋላል ብለዋል።
የሌባ ትንሽ የለውም ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጀምሮ ህብረተሰቡን የሚያማርሩት ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል። (ንብረቴ ተሆነ – ኢቲቪ)
ይህ ሌባን የማደኑ ተግባር መቀጠል ያለበት ሲሆን ወደ ፖለቲካ ሹመኞች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ሌቦቹ ታድነው መታሰር እንዳለባቸው አስተያየት ይሰጣል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሌቦ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ መሆናቸው ታውቆ በዋስ እንዳይለቀቁ እና በቀላል ቅጣት እንዳይወጡ ተገቢው መፈጸም እንደሚገባ ብዙዎች ይስማማሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Feyissa kenenissa says
Yechin ye politics chewatae nech
Yesewen ayen ke woyane Lai aneseto wedezih lemazor yetederege Kumar new
Enji Le hizib tasebo aydelem . Lebochuma eko yitawekalu kebefitum be loader eyafessu yewesedut Esti beccemento tuba balehabet yehonewen yazut lib kalachehu (ye shimelis en network )
Berelea says
አይመስለኝም ከንቲባ አዳነች አቤቤን ሚኒስቴር ታከለ ኡማና የህወአት ጩሉሌ ሌቦችን ምን ልታደርጋቸው ነው? ጢሞቴዎስ እንደ ትምህርት ቤት ህጻን የደብረጽዮንን አይን ማየት የፈራ እንዴት አድርጎ ነው እነ ጻድቃንን ላይ የእስር ትእዛዝ የሚያወጣ?