- አዲሱ ህወሃት በአሮጌ አቁማዳ
በትግራይ መቀሌ መሽገው የ13 አመት ልጅ እየመለመሉ ስልጠና ሲሰጡ የከረሙትና ትላንት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉት ሁለቱ ሙሰኛና የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ጄኔራሎች በፎቶው የሚታዩት ናቸው!
ብ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ፤ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ሲመጣ “ተደምሪያለሁ” በማለት ጊዜ ገዝቶ፤ ሚስቱንና ሶስት ሴት ልጆቹን አሜሪካ ወስዶ፤ ቤት ገዝቶ፤ አመቻችቶ፤ እንዲሁም ከመጀመሪያ ሚስቱ የወለደው ዳንኤል የተባለውን ልጁ በካናዳ እንዲኖር ያደረገው ተክለብርሃን፤ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ወደ መቀሌ ሸሸ።
ሁለት ትላልቅ ህንፃዎች በመገናኛ ወደ ሃያት በሚወስደው መንገድ ያሉት (ተገትረው የቀሩ) በኦሮሚያ በርካታ መሬቶች የሸጠ፣ ለበርካታ ዘመዶቹ በሃብት ጥግ ያደረሰ ሙሰኛ ነው!
ሁለተኛው ብ/ጀነራል ኃ/ሥላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ) ነው። ከታጋይ ሚስቱ ትቅደም ሶስት ልጅ ወልዶ፤ ልጆቹን አሜሪካ የላከና በሙስና የበለፀገ ሚሊየነር ነው።
ደብረፂዬን ሁለት ልጆቹ አሜሪካ ናቸው። ጌታቸው አሰፋ በለውጡ ሰሞን አሜሪካ ኢንዲያና ጠቅላይ ግዛት ትልቅ ፓላስ ገዝቶ ሚስትና ልጆቹን በተንደላቀቀ ህይወት የሚያኖር ገዳይ ሙሰኛ፣ የስዩም መስፍን ልጅ በሜሪላንድ ወዘተ አብዛኞቹ ልጆቻቸው በተንደላቀቀ ህይወት በውጭ የሚኖሩ ናቸው። ድሃውን የገበሬ ልጅ ሊያስጨርሱ የተነሱት እንግዲህ እነዚህ ናቸው!
አዲሱ ህወሃት በአሮጌ አቁማዳ፤ የመቀሌ ሁለት ቡድን!
በመቀሌ ሁለት የህወሀት ቡድን እንዳለ ማረጋገጥ ተችሏል። በመስከረም “አደረኩት” ካለው የጨረባ ቅርጫ – ምርጫ በኋላ እነደብረፂዬን ከሚመሩት ህወሀት ሌላ ስብሃት የሚመራው እና “ዋና የበላይ ህወሀት” የሚል ስያሜ የተሰጠው ቡድን ይፋ ባልሆነ መንገድ ሲቋቋም፣
- ሊቀመንበር ስዩም መስፍን፣
- ምክትል አባይ ፀሀዬ፣
- ፀሃፊ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ (ሚስቱ ቅዱሳን ነጋ የስብሃት እህት)
ውሳኔ ሰጪ አባላት ስብሃት ነጋ፣ ኮ/ል አወል አብዱራህማን፣ ጌታቸው አሰፋ እንደሆኑ ከቅርብ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።
“የበላይ ዋና” የተባለውና አብዛኛው አባል ሳያውቀው በነ ስብሃት የተዋቀረው ይህ ቡድን በአገሪቱ የሚፈፀሙ እልቂቶችን በመምራት፣ ጦርነት በማወጅ ወዘተ ከጀርባ የሴራው መሪና ቀያሽ ነው!
የዚህ ቡድን አባል የሆነው ኮ/ል አወል ማንነት መጋለጥ አለበት! ብዙዎች ደደቢት ክለብ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያውቁታል! ግን ከጀርባ በሙስና ሲበልፅግ የነበረ የነ ስብሃት መሰሪ አላማ አስፈፃሚ ነው!
ኮ/ል አወል በገርጂና ቦሌ እጅግ ዘመናዊ ሁለት ቪላዎች አሉት። በእሱ ስም የተገነባው 90 ሺህ ሲከራይ፣ በልጁ ሬድዋን አወል ስም የተገነባው ቪላ በወር 4 ሺህ ዶላር ይከራያል።
የኮ/ል አወል ልጅ ሬድዋን በሽሬ ትልቅ ፋብሪካ አለው። “ሻንሃይ” (ሻንጋይ ለማለት ነው) የማዳበሪያ ፋብሪካ በመቶ ሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ የተገነባ ነው። ሬድዋን አንድም ስራ ሰርቶ አያውቅም። ትምህርት ጨርሶ ሚሊየነር የሆነ ነው።
ኮ/ል አወል ከዚህች አገር በዘረፈው ሀብት ሁለት ቪላ ገንብቶ እያከራዩ፣ ኪራዩንም በወኪል እየወሰደ ባንፃሩ (እርሱና ግብረአበሮቹ) በዚህች አገር ላይ የጥፋት አዋጅ አውጀዋል!
ኮ/ል አወል ልጆቻቸውን በዘረፈው ገንዘብ ሚሊየነር ካደረጉት አንዱ ሲሆን የትግራይ ድሃ ልጅ ለማስጨረስ ከነስብሃት ጋር ከፊት መስመር ተሰልፏል!
ምንጭ፤ አርአያ ተስፋማሪያም ፌስቡክ ገጽ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply