ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አምስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
ስሙ ለዘለዓለም – ይኖራል ሲጠራ
ነገር ግን ታሪኩን – ያረገውን በጎ
አንባቢው አለበት – መረዳት ፈልጎ
እኛ ለማስታወስ – ይሄንን አድርገን
ለማቅረብ ችለናል – መላኩ በያንን
እኚህ ስመ ጥሩ – ኢትዮጵያዊ ዶክቶር
ሙሉ እድሜአቸውን – ደክመዋል ለሀገር።
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
እናት ሀገራችን – ብዙዎች ነበሯት
የታሪክ ማህደር – ፋይል ሳገላብጥ
እኚህን ታላቅ ስው – አየኋቸው ከውስጥ
ላስታውስ ነው እንጂ – መቼም አታጧቸው
በሉ ተናገሩ – እኚህ ሰው ማናቸው?
senu says
zeray deses ?
Taddese Mammo says
DR.Melaku Beyan : He was organizing pro Ethiopian forces in the USA representing Ethiopia during Ethio-Italian war as Haile Selassie special representative
Dereje Mengesha says
ነጋድራስ ናቸው ገብረህይወት ባይከዳኝ
በነጋ በጠባ ማናቸው እያልከኝ
ፈተና እያመጣህ በቃ አትጨቅጭቀኝ
Zenaneh Temesgen says
እኔጃ ነው መልሴ እንዴት ላስታውሳቸው
የታሪክ መድብል ውስጥ የለም አልበማቸው
Mengesha Asmare says
የአገሬ ሰዎች በበጎ ስራቸዉ ሀገር ያወቃቸዉ
እረ ብዙ ናቸዉ
ሁሉንም ባንድ ጊዜ ቆጥረን ባንዘልቃቸዉ
ቀስ በቀስ እያልነ እስኪ እንዘክራቸዉ
የሀገሬ ታሪክ ትልቁ መፀሀፍ ከከታተባቸዉ
ገ/ህይወት ባይከዳኝ ያነን ስመ ጥሩዉ
ይመስላል ፎቷቸዉ
Bombu says
እንደው በግርድፉ ፎቶውን ሲያሰሉት
የቆየ ይመሥላል ዘመን ያለፈበት
ደግሞ ሲያስተውሉ ግለስቡን ዘልቆ
አለባበሱንም ካዩ ተጠንቅቆ
ወጣት ከመሆኑም ዘና ከማለቱ
ኮፍያው ከራሱ ከረባት ባንገቱ
ሁሉንም አሥማምቶ የተነሳው ፎቶ
ዘመነኛነቱን ያሳያል አጉልቶ
በውጭ አገር ኖረው ያውቃሉ ለማለት
ነበር ሙከራዬ ይሕ ሁሉ መዋተት
ከዚህ በተረፈ የምስማማው እኔ
የመገምት አቅም ባይኖረኝም ወኔ
ቢሆኑ ደስ ይላል በያን ወመላኩ
እንደተጠቀሰው ከላይ በመድረኩ
Bombu says
አወይ የኔ ነገር አወይ የኔ ሥራ
ግለሰብ ለይቼ ስሙን ሳላጣራ
ካቀያየርኩዋቸው አንዱን ወደ ሌላ
ማሥተካከሉ ላይ እንዲፈጠር መላ
ወለላዬ ወይም የጎልጉል አዘጋጅ
ማንንም ሳልጠይቅ ሳላመጣ አማላጅ
ይስተካከልልኝ ጥያቄው ከመልሱ
እንዲሁም ይታገድ ይቆይልኝ ሒሱ
Editor says
ወዳጃችን Bombu ምንም አያስቡ
በውል ተስተውሏ መልሱና ሃሳቡ
የመጀመሪያውን መልስ ተገቢው ቦታ ላይ አትመነዋል፡፡ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ ሁለተኛ በማስተካከያነት የላኩትን ውብ ግጥም ላለማጥፋት ብለን ከ“ስህተቱ” ጋር እዚሁ ትተነዋል፡፡
አርታኢ
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ
Tsegaye Kassa says
አላዉቀውም እንጂ ባውቀውማ ኖሮ
እነግርህ ነበረ ከቅድም ዠምሮ
መገመቱንማ ልገምትላቹ
የግምት የግምት ፈስም ዳለቻ ነው አትብሉኝ ባካቹ
እኝህ ትልቅ አባት ታሪክ ያስቀመጡ
ዛሬ ለትዝታ በፌስቡክ የመጡ
የዋዛ አደለም የፀግሽ ግምቱ
ገ/ሂወት ባይከዳኝ የጥንት የጠዋቱ
henos says
gebrehiwot bykedagne nachew ”yehizib ena ye mengist astedader” yemilewun metshaf yetsafut