እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩

(ወለላዬ)

ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን who is this personእናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሃያ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡

መልስ

በጌምድርና – ሰላሌን በመግዛት

ጠቅላይ አዛዥ ሆነው – በጣሊያን ጦርነት

በተንቤን ግንባር – ላይ ሌሎች የመሩ

ልዑል (ራስ) ካሣ ኃይሉ – እኚህ ሰው ነበሩ


ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡

ጥያቄwho is he 21

ብዙዎች ነበሩን – እጅግ ጀግና ሰዎች

የህዝብ እንደራሴ – የሀገር አኩሪዎች

ጊዜው ተደራርቦ – ዘመኑ ቢረዝምም

የሰሩትን ሥራ – መርሳት አይቻልም

እኝህ የሚታዩት – በዋና አዝማችነት

የታወቁ ናቸው – በጣሊያን ጦርነት

ምስክር ሁኑልኝ – እናንተም እንደኔው

የት ነው የዘመቱት – እኚህ ሰው ማናቸው?

Comments

  1. Ras Birru Wolde Gabriel ..

Speak Your Mind

*