እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ

(ወለላዬ)

ከአዘጋጆቹ፤

ከጥቂት ወራት በፊት በወዳጃችን ወለላዬ ለቀረበው የበርካታ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩ ባለሥልጣናትን ፎቶ ለያዘው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተባበራችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን::

ከተለያዩ ምንጮ ያሰባሰቡትን ምላሽ ወለላዬ አጠር ካለች ግጥም ጋር በቁጥራቸው ቅደም ተከተል አቅርበውታል፡፡ ከዘመኑ መብዛትና መረጃ መዛባት ምክንያት በምላሹ ላይ ስማቸው ወይም ማዕረጋቸው የተዛባ ቢኖር ማስተካከያ ለሚሰጡ ሁሉ አሁንም በቅድሚያ ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡

መልስ

በዝርዝር ማስቀመጥ – በቁጥሩ በስሙ

ለመግጠም የሚያስችል – ነበረኝ አቅሙ

ነገር ግን ለአንባቢ – እዚህጋ ሲቀመጥ

እንደዚህ ሲሆን ነው – የሚጥመው ይበልጥ

በማለት አስቤ – የሁሉም ዝርዝር

ከስር አስፍሬያለሁ – በስማቸው አንፃር

officials

 1. መርዕድ  መንገሻ (ሜ/ጄኔራል) የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩ
 2. አክሊሉ ኃብተወልድ (ፀሐፊ ት እዛዝ) ጠቅላይ  ሚኒስትር
 3. ይልማ ደሬሣ (አቶ) ገንዘብ ሚኒስትር
 4. አበበ ረታ ( አቶ ) የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
 5. ከበደ ተሰማ (ደጃዝማች) የግቢ ሚኒስትር
 6. ታደሰ ያዕቆብ  (አቶ) የመንግስት ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር
 7. አማኑኤል አብረሃም (አቶ)  የመገናኛ ሚኒስትር
 8. ክፍሌ እርገቱ (ደጃዝማች) የሀገር ግዛት ሚኒስትር
 9. ከተማ ይፍሩ (አቶ) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
 10. ግርማቸው ተ/ሐዋርያት (ደጃዝማች) የእርሻ ሚኒስትር
 11. አስፍሐ ወ/ሚካኤል (ቢትወደድ) የፍርድ ሚኒስትር
 12. አሰፋ ለማ (ሻለቃ) የማዕድን ሚኒስትር
 13. ምናሴ ኃይሌ (ዶ/ር) ሚኒስትር (በንጉሠ ነገሥት ልዩ ጽ/ ቤት)
 14. ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ (ዶ/ር) የሥራ ሚኒስትር
 15. አብዱረህማን ሼህ (አቶ) ሚኒስትር (በጠቅላይ  ሚኒስትር ጽ/ቤት)
 16. ሳሊት ሄኒት (አቶ) የፖስታ ሚኒስትር
 17. ሥዩም ሐረጎት  (አቶ) የማስታወቂያ ሚኒስትር
 18. አብዱልህማን ሙሜ ( _ ) ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
 19. በለጠ ገ/ጻዲቅ (አቶ) የመሬት ይዞታ ሚኒስትር
 20. ጌታሁን ተሰማ (አቶ) የሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ሚኒስትር
 21. አካለ ወርቅ ሀ/ወልድ  (አቶ) የትምህርት ሚኒስትር
 22. ማሞ ታደሰ (አቶ) የፕላን ሚኒስትር

Speak Your Mind

*