የቴድሮስ ቅሌት!!

የኮ/ሎ ጎሹን ብቃት አስናፍቋል

ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት እየተወዳደረ ያለው የህወሃቱ ዕጩ ቴድሮስ አድሃኖም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አቅቶት በተደጋጋሚ ግልጹን ጥያቄ እንዲብራራለት ሲጠይቅ መዋሉ ብዙዎችን ያነጋገረና ያሳፈረ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ውርደቱ የከነከናቸው ትንታጉን አንደበተ ርቱዕ ኮ/ሎ ጎሹ ናፍቀዋል፡፡

በ2017 የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሚያገለግል ለመምረጥ ለ194 ዓባል አገራት በቀረበው ጥሪ መሠረት ህወሃት/ኢህአዴግ ከሚገዛት ኢትዮጵያ፣ ከጣሊያን፣ ከፈረንሣይ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከፓኪስታንና ከሃንጋሪ ስድስት ዕጩዎች አገራቱ አቅርበዋል፡፡

በተያዘው ዕቅድ መሠረት ዕጩዎቹ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ የቃል መግለጫ ካቀረቡ በኋላ ከአባል አገራት ጥያቄዎች ቀርበውላቸውል፡፡ ቴድሮስ አድሃኖም ከአልጄሪያ፣ ከጀርመን፣ ከአውስትራሊያ፣ ከህንድ የቀረቡለትን ጥያቄዎች ጥቂቶቹን በቀጥታ ከመመለስ በስተቀር ለአብዛኛዎቹ ተገቢ ምላሽ ሳይሰጥ አልፏል – በተለይ ከህንድና ከጀርመን ተወካዮች የቀረቡትን ጥያቄዎች!

tedros2በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደነበር የሚያሳብቅበት ቴድሮስ በሁለተኛው የጥያቄ ዙር ከፍተኛ ችግር ገጥሞታል፡፡ ኤርትራ የተወለደውና ለድርጅቱ ባስገባው የማመልከቻ ቅጽ ላይ እንግሊዝኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋዬ አቀላጥፌ እናገራለሁ በማለት የተናገረው ቴድሮስ ከብራዚል ተወካይ የተሰነዘረለትን ቀጥተኛ ጥያቄ ለመመለስ አንዴ ይብራራልኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይደገምልኝ ግን ደግሞ ይብራራልን ራሱ ግራ ተጋብቶ በርካታዎችን ግራ ሲያጋባ ቆይቷል፡፡

ጠያቂው ያቀረቡት ጥያቄ ከምታድግ አገር (ከደቡብ) የመጣህ ሆነህ ድርጅቱን እንዴት እንደምትመራ ያቀረብከው ማብራሪያ ደግሞ የምዕራቡን ዓለም (የሰሜኑን) አጀንዳ የሚያንጸባርቅና የሚደግፍ ነው ይህንን እንዴት ታስታርቀዋለህ ነው፡፡ ጠያቂው በግልጽ እንግሊዝኛ ነው የጠየቁት፤ ጥያቄውን ዕጩ ተወዳዳሪ ያልሆነ ማንም ሊረዳው የሚችል ነበር፡፡ ቴድሮስ አልገባኝም ይደገምልን አለ፡፡ ጠያቂው ባጭሩ ጥያቄያቸውን ደገሙ፡፡ ቴድሮስ አሁንም “ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በማያያዝ ነው የጠየከኝ” በማለት ጠያቂውን መልሰው ይጠይቃል፤ ብራዚላዊው ጠያቂ በጠየቁት ቀላል ጥያቄ የቴድሮስ መንተባተብ ግራ የገባው በሚመስል ሁኔታ ፈገግ ብለው “እኔ የሁለትዮሽ ንግግር (ዳያሎግ) ለማድረግ አይደለም …” በሚሉበት ወቅት ሰብሳቢው ጣልቃ በመግባት ለሦስተኛ ጊዜ ጥያቄውን ያስረዳሉ፡፡

በህወሃቱ ዕጩ በርካታ ሰዎች ሃዘናቸውንና እፍረታቸውን እንዲሁም ንዴታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአገር ውርደት እንደሆነ በመቁጠርም ከየዲግሪው ወፍጮ ቤት ዲግሪ እየገዙ “በችሎታ/ሜሪት” ነው አገር የምናስተዳድረው በሚሉ በህወሃት ሹመኞችና በቴድሮስ ላይ ውርጅብኝ አውርደዋል፤ ምስሎችንም ለቅቀዋል፡፡ ከተሰጡት በርካታ መካከል ጥቂቱ፤tedros

 • “ለማንኛውም ትምህርት እድሜ አይወስነውም አሁንም ቋንቋ መማር ይችላሉ… ምነው አባዱላ እንኳን ፈገግ ብሎ “ፍቅር፤ ፍቅር” እያለ እንግሊዘኛውን እያጧጧፈው አይደል እንዴ!!”
 • “እርር ድብን ያደርጋል ወይ ብሔር ብለናል አወቅናችሁ ሰው የለም ውስጣችሁ”
 • “I don’t understand what you said?
  Can you clarify that?
  Can you say it in short sentence?
  Can you say it in Tigrigna”
 • “I dont understand what you say sir? Can you clarify it or Would please say it in Tigrigna? Wayi Atah Tigiregna Tizarebalo? boaaaa!!…Keserina!!! Ayi zendro!!!”
 • “He failed to understand and answer crucial question. They thought he is a normal candidate who is educated and capable. However he started to argue instead and said something irrelevant to the question.”tedros1
 • “ከ5 አመት በፊት ለUNAIDS. Executive Director። አንድ ኢትዬጵያዊት … ዶ/ር ደብረወርቅ የምትባል…ትወዳደር ነበር። ሁሉም ሰው እርሷ ትመረጣለች ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን አዜብ መስፍን ስለማትወዳት በመለስ በኩል ይች አመልካችን መመረጥ የኢትዮጵያ መንግስት እንደማይደግፍ ደብዳቤ ተፅፎ አመልካቿ እንድትወድቅ ተደርጓል። ይህች ሰው አማራ ነበረችና ወያኔወች አይወዷትም። ካስታወሳችሁ በEBS ከ6 ወራት በፊት ቀርባ ነበር። ቴድሮስን ወያኔ ደገፈው ወጩንም ሸፈነለት። ይሁን ደህና። እመኑኝ የትምህርት ዝግጅቱም ሆነ ያቀረበው ፅሁፍና ለጥያቄወች የሰጠው ምላሽ እጅግ ደካማ ነውና እንደኔ ግምገማ ቴድሮስ አይመረጥም። ታያላቹ።”
 • “እንግዲህ እዩልኝ… ወዲ አድሃኖምን የሄዱት ከ:-
  1. ልማታዊ መንግስት/developmental state/
  2. ልማታዊ ኢኮኖሚ /developmental economy/
  3. ሰውን እያደራጁ የልማት ሰራዊት/ developmental army/
  4. ከምንም በላይ እንግሊዝኛን እንደ native speaker ነኝ ያለ ሰው እንዴት ከታች ከተሳታፊዎች የቀረበለትን ጥያቄ አልገባኝም ብሎ ሰው እስኪስቅበት ድረስ እየደጋገመ ይደገምልኝ ይላል? How can we translate your views in terms of a development candidate?”
 • Know your limit. Otherwise, be ready to face such embarrassments.
  ‘ካሪዝማ’ ምናምን አለህ ብለው ፎግረውት እኮ ነው መገኘት ያልነበረበት ቦታ የተገኘው።
 • አሳቃቂ ነው። እኔ ግርም ያለኝ ገገማነቱ። ዝም ብሎ ስለ ሆነ ነገር ፈጥሮ ያልተጠየቀውን አይቀባጥር (እንደ መሌ)። … 10ሬ ድገሙ ከሚል። ለምሳሌ ስለ እጅ መታጠብ፣ ስለ አተት … አገር በቀል በሽታዎች… የሟቹን Legacy ገደል ከተተው።😜😜
 • አገር ቤትማ ቢሆን ጥያቄውን ገና ሳይጠይቁት መመለስ ይጀምር ነበር። መልሱም ጥያቄውም ቀድሞ ስለሚሰጥ። እዚ ግን እናቴ ጥያቄ መረዳት በራሱ መከራ ሆነ መመለሱማ ቅንጦት ነው። ወይ ግሪንዊች!!!!!😜😜tedros6
 • Love is never die. አይልም ነበር እንደ አባ ዱላ?! ተሸወደ
 • እህ ዶክተር ኢንጅነር ሳሙኤል ዘሚካኤልም እስኪነቃበት ድረስ ተደንቆ እና ተጨብጭቦለት ነበር!
 • ወይኔ ይሄም ደንግጦ መሞቱ ነው!
 • Journalist: “Dr ቴድሮስ I understand you are the breadwinner in your family”?
  Dr ቴድሮስ “sorry the question is not clear, may I ask you to clarify?”
  Journalist: “are you a breadwinner of your family?”
  Dr ቴድሮስ: u mean linking it with the sustainable development goal?
  *እዝች ጋ ሳቅ ከተሰብሳቢው*
  Dr ቴድሮስ: “I’m hearing that allegation for the first time, I have heard it before, It’s the work of ነፍጠኛ those who want to tarnish my name… I want to tell you that, I’ve never been in any competition to win bread. Ask those people who say I’m a breadwinner where they saw me win that bread? I don’t need to be a bread winner to feed my family, I can buy it with my own money. “If there is love and trust between us never die” አለ አባዱላ ገመዳ “ጨንቆት እኮ ነው” that have been said Those claiming I am a breadwinner must be very careful otherwise I will sue them…
 • በጣም የሚገርመዉ ጥያቄው የሚጠበቅና ግልጽ መሆኑ ነው።
 • How can a person who is confirmed to be inefficient to lead a Ministry by his government, will lead a huge international organization?!!!!
 • I accept that English isn’t his mother tongue, I also accept that once in a while you can ask clarification to better position yourself in responding to questions. But keep asking clarification now and then for questions so strategic for this global position, is acceptably missed in action. እውነት ለመናገር ትንሽ ተሸማቅቈያለሁ!
 • … What a HUMILIATION!!! This is beyond SHAME!!!!! Robel on Olympic now this fool and idiot what’s next……tedros-and-robel
 • I’ve come to a conclusion that this presentation was prepared by someone else. There are rumors that he hired a US based Firm to help him get elected for this WHO position. His mumbling is clear evidence that he has no knowledge of his own ‘Presentation’.
 • እኔ የሚገርመኝ የወያኔ ደጋፊዎች ክርክር ነው። ይሄ ሰው ከስሙ በፊት የዶክተር ማእረግ ለጥፎ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኒስቴር ማእረግ የተቀመጠ አፍሪካን ወክሎ ለአለም ጤና ድርጅት እጩ ሆኖ ቢመረጥ ምን እቅድ እንዳለው ፅፎ ባቀረበው ፅሁፍ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቆ እራሱ ፅፌዋለሁ ላለው ነገር መልስ መስጠት ባለመቻሉ መሽማቀቅ ሲገባቸው ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። ያቀረበውን ፕላን ወይ ሰው ነው ፅፎ የሰጠው ወይ ከሆነ ቦታ ነው የገለበጠው።
 • Do you mean about sustainይነብል ዴበlovመንት?
 • የኢቢሲ የምሽት ዜና “አንዳንድ የሻቢያና የግንቦት 7 ተላላኪዎች ቴድሮስ አድሃኖምን በ WHO መድረክ ላይ ከባድ ጥያቄ መጠየቃቸውን ተከትሎ ኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ዛሬ አስታወቀ።!!!! ታደሰ ሚዛን ዝርዝር አለውውው…..”

ሌሎችም እጅግ በርካታ አስተያየቶችና ለጆሮ የሚቀፉ ዘለፋዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰጥተዋል፡፡

ይህ የቴድሮስ ብቃት ማነስ የዛሬ 25ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉትን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ አስናፍቋል – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት

goshu“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” እጅግ መሳጭ የሆነውን ሙሉ ንግግራቸውን እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

በጎሹ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረው ቴድሮስ በዚህ ዓቅም ባነሰው አቀራረቡ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያንንም አሰድቧል፤ አዋርዷል፤ አንገት አስደፍቷል፡፡

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት የዕጩዎቹን ገለጻ ካዳመጠ በኋላ በመጪው ጥር ወር ላይ ሥራ አስፈጻሚው በሚያደርገው ስብሰባ አሁን ካሉት 6 ዕጩዎች ውስጥ እስከ 5 የሚደርሱ ዕጩዎችን ይወስዳል፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ እጩ ቃለ መጠይቅ ካደረገ በኋላ ሦስት ያስቀራል፡፡ አጠቃላይ ጉባዔው በግንቦት ወር በሚሰበሰብበት ወቅት አባል አገራት በሦስቱ ዕጩዎች ላይ ድምጽ ይሰጣሉ፡፡ ከድምጽ ሰጪዎቹ አገራት መካከል 46 ያህሉ አፍሪካውያን ናቸው፡፡ ለጤና ድርጅቱ ከአፍሪካ እስካሁን መሪ ተመርጦ ስለማያውቅ የአፍሪካ ዕጩ ሆኖ የቀረበው ቴድሮስ በድምጽ ብልጫ ያሸንፋል የሚል ግምት ካሁኑ እየተሰጠ ነው፡፡ ስለዚህ የቴድሮስ ዕጩነት እና ከህወሃት ጋር ያለውን የወንጀል ተግባር በማያያዝ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ወገኖች ከአሁን በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ከምንጊዜውም በበለጠ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጉዳዩን የሚከታተሉ የሚሰጡት የምክር ሃሳብ ነው፡፡

የቴድሮስን አጭር ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ ሙሉው የቃል ገለጻው እዚህ ላይ ይገኛል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. >>>ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት በ2017 የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሚያገለግል ሰው የሆነ ሰው(ሰው መሳይ ዋሾ ሳይሆን ማለት ነው።) ለመምረጥ ለ194 ዓባል አገራት በቀረበው ጥሪ መሠረት ከጣሊያን፣ ከፈረንሣይ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከፓኪስታንና ከሃንጋሪ ስድስት ዕጩዎች አገራቱ አቅርበዋል፡፡
  ** ህወሃት/ኢህአዴግ ከሚገዛት ኢትዮጵያ፣ የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ቴድሮስ አድሃኖም ከብራዚል ተወካይ የተሰነዘረለትን ቀጥተኛ ጥያቄ ለመመለስ አንዴ ይብራራልኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይደገምልኝ ግን ደግሞ ይብራራልኝ ሲል ራሱ ግራ ተጋብቶ በርካታዎችን ግራ ሲያጋባ ቆይቷል፡፡ ጠያቂው ባጭሩ ጥያቄያቸውን ደገሙ፡፡ ቴድሮስ አሁንም “ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በማያያዝ ነው የጠየከኝ” በማለት ጠያቂውን መልሰው ይጠይቃል፤ ብራዚላዊው ጠያቂ በጠየቁት ቀላል ጥያቄ የቴድሮስ መንተባተብ ግራ የገባው በሚመስል ሁኔታ ፈገግ ብለው “እኔ የሁለትዮሽ ንግግር (ዳያሎግ) ለማድረግ አይደለም …” በሚሉበት ወቅት ሰብሳቢው ጣልቃ በመግባት ለሦስተኛ ጊዜ ጥያቄውን ያስረዳሉ፡፡

  1) ጠያቂው ያቀረቡት ጥያቄ ከምታድግ አገር (ከደቡብ) የመጣህ ሆነህ ድርጅቱን እንዴት እንደምትመራ ያቀረብከው ማብራሪያ ደግሞ የምዕራቡን ዓለም (የሰሜኑን) አጀንዳ የሚያንጸባርቅና የሚደግፍ ነው ይህንን እንዴት ታስታርቀዋለህ ነው፡፡
  *********************!
  »የኢህአዴግ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ለስዩም መስፍን መኝታ ቤት ሆና 10ዓመት አገልግላለች። ለህወአት የማይደፈርና የማይገሰስ ልዩ ንብረት ተብሎ 1983 አዲሲቷ ኢትዮጵያ ላይ ፀድቋል። የአልጀርስ ስምምነት ባድሜ ለኤርትራ ተስጥቶ ኢትዮጵያ አሸነፈች ያሉት ስዩም መስፍን የቋንቋ ዕጥረትና የሻቢያ ክልል የትግራይም ነው በሚል የሰጥቶ ማጭብጨብ በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተው የክፉ ቀን ወዳጅ የክፉ ቀን መግቢያም ስለሆነ ነው።

  » በእግራቸው የተተኩትና የዓለም ጤናን ዕድገት ለማሻሻል እወክላለሁ ያሉት የፌስ ቡኩ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር…ከአንዳርጋችው ፅጌ ቱፋ የእሥር ቤት ዲቨሎፕመንት ራዕይ ያልታተመ መጽሐፍ ረቂቅን በቃላቸው ሸምድደው ገብተው የጤናውን ጉዳይ “በዘመቻ መልክ በማሳመን እንዲቀበሉ ወደታች ማስረጽ” ማለታቸውን ተከትሎ ባላደገና ባልተማረ በሕዝባችሁ ላይ የጫናችሁትን እንዴት በዓለም ሕዝብ ላይ እጭናለሁ ትለናለህ አብራራ??
  አልሰሜን ጠይቅ በለው!
  ** ነጠላ ሰረዝ ሳይቀር ከፈረንጅ እየገለበጡ ለራሳችው የሚያነቡላችው 25 ዓመት ትውልድ እንዳጀዝቡ ክልላዊ ቤተ ሙከራ አድርገውን ነው።
  >የጅምላ አስተዳደር…የኢትዮ ሚዲያ ብዝሃነትና ሕዳሴ!… የተረጋጋ ኢኮኖሚ ደብል ድጂት….ተከታታይ በመቶና… በዚህ ደረጃ በዚያ ደረጃ… አብዮታዊ ልማታዊ….ዴሞክራሲያዊ…ፈጣን ብሔርተኝነት.. ነጻ ሚዲያ ….ሽብርተኞች…የድሮ ሥርዓት…አክራሪ..ማሳለጫ መንገድ! ወ.ዘ.ተ
  አሁን አላስፈለገም። አንድ ሰው ጥያቄው ግልጽ አደለም ማለቱ ባልከፋ እራሱ የተናገረውን አስረዳ ሲባል ካቃተው እንደ ህወአት/ኢህአዴግ ፓርላማ ሁሉ በጭብጫቦ ይሸፈን መስሏቸዋል። ተጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀልድና ተረት ጨርሰው አሜሪካን አቋርጠው የቻይና ተረት ሲጀምሩ ፓርላማው ሲዝናና ሲገልፍጥ ቀልዱ ሲቀር በድንኳን ልማታዊና ታማኝ ሌባ አቧድነው “አንድ ሕዝብ አንድ ለቅሶ!” አስቀወጡት።
  ***ይቺ በአንድ ሠፈር ልጆች የተገነባች ልማታዊ ብሔርተኝነት “በማስርጽ” ተበክሏል በዚሁ ሰሞን አንድ የኢህአዴግ የሕግ ባለሙያ ነኝ ባይና የአርብቶ አደር ዴኤታ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ሲያወያዩ “ሕዝቡ ለምን ኮከብ ያልውን ባንዲራ ያቃጥላል! ያዋርዳል! ትውልዱ እንደድሮው የባንዲራ ፍቅር የለውም!…ህገመንግስቱን 16ሚሊየን ሕዝብ ተወያይቶ አጽድቆታል.. ተቃዋሚ ፓረቲዎች..ትምህርት ቤቶች..መሥሪያ ቤቶች እና ሚዲያው..የግድ በጋራም በተናጠልም በሕዝቡ ‘ማስረጽ’ ግዴታቸው ነው፡” ሲሉ ደመደሙት የሀገር ፍቅር በግድ!?
  +++ ዶ…ቴዎድሮስ ማስረጽና ማስገደድ የጫካ ማኒፈስቶ ነው። ኢህአዴግ የሚወለዱ ጭቅላ ህጻናትና የእናቶች በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ ቁጥር ቀነሰ ሲል ወጣት፡ጎልማሳ፡ አዛውንትን ግድያ ከፍ እያደረገ መሆኑን ታሪክ ምስክር ነው።
  ++ + የትግራይን ህዝብ የዕርዳታ እህል ሸጦ መሳሪያ በመግዛት፡ ለልማት፤ ለሕጻናት ተመጣጣኝ ምግብ፤ ልብስ ዘይትና፤ የዱቄት ወተት፤ በመቸርቸር የታወቀ ወሮ በላ ቡድን ሲሆን የንግድ ሞኖፖል ‘የጥረት ኢምፓየር’ የጀመርኩት “የስንዴ ጆንያ ሸጬ” ነው ሲል የተመፃደቀና የዋሸ የዓለም ጤና ደርጅት ቢሰጠው መድኅኒተና ምግብ ለመቆጠብ ማምከንና መግደልን ከልምድ ወደ ዓለም ድርጅት እንደሚያሰርፅ ምንም ጥርጥር የለም።
  የውሻን ጥርስ በምን ይፈሩታል ? “እኛን ያየ ይቀጣ!” በቸር ይግጠመን

 2. በኤርትራ ኣነጋገር ”ዝበልዕሉ ጻሕሊ ዝሰብሩ!” ይላሊ። ለምትበላው ወጥ የሚሰራበት እንደመስበር ማለት ነው። ብዝዎቹ የወያኔ ታጋይ በለስ እየሸጡ በኤርትራ የተማሩ ናቸው። እና ሁሉ ግዜ ነፍሳቸው ከሰው ኣዘቅዝቀው ስለሚያዩት፡ ሃይል ከተሰማቸው፡ ለአስተማረው፡ ለመገበው፡ ያቀፈፍ፡ ብጥሩ ተንከባክቦ ለተኘው ሰውን ለማጥቃት፡ ለመሸወደ፡ ለማታለል፡ ብሎም ለመግደል ይናፍቃሉ። ይፈልጋሉ። ብየተኘው ልብ እንሚቀራረቡ ማውቅ ቀላል ነው። ወያኔውች የማታለል ፈገግታ ልማዳቸው ነው። ከሰው ጋር ፊት ልርፊት መደራደር ፍጹም ልማዳቸው ኣይደለም። ብስውር የጠነሰሱት ብውይይት በሰው ላይ ማመጽ፡ ሰው ከሰው ማዋጋት፡ ማጥላላት ነው የሚወዱት። ሌላ ባህርይ የላቸውም።
  10 ልባቸው!
  1. በውይይት፡ የሰው ልብ መስለብና፡ ተቀናቃኝ ድርጅት ማፍረስ፡ የሚወክልህ ድርጅት ብቻ ሰው መሰብሰብ፡ ሰው የማግለል ልብ
  2. ብፈገግታ እንደ ጓዶች፡ የፍቀር ፍሬንድ ሆኖ በማቅረብ፡ ያንተ ሃሳብ፡ አዝማምያ፡ ማወቅና መልቀም የማታለል ልብ
  3. ብስውር በተንኮል የማሰር፡ የመግደል፡ ወደገደል የመወርወር ልብ
  4. የመዝረፍ፡ በምትወደው ውስጣዊ ስሜት በመግባት፡ በመለማመጥ፡ ጓደኛህን ገድልህ በገደልገው ሰው ላይ መኖር ልብ
  5. አንድ ግዜ ከሰው በላይ ስሜት ከተሰማው፡ የሰው ህፍረት በማስወገድ፡ እሰው ላይ አማጽ ማካየድ ልብ
  6. ስልጣን ለማግኘት በሰው ህይወት ላይ መሯሯጥ ልብ
  7. ስልጣን ከተገኘ የወገንነት፡ ቃል ኪዳን መመስረት ልብ
  8. ሁሉ ነገር የፈለከው ለማድረግ ልመና፡ የመማጻደቅ ልብ
  9. በቡዙሃን ህዝብ ንግድ ማካየድ፡ መሬት፡ ላይሰንስ፡ የልጃገረድ ለውጭ ድፕሎማት መሸጥ፡ ህጻናት ለሞጉዚት መሸጥ፡ ሰው እንደፍላሻ መሸት ዋጋ የተገኘ ሁሉ መሸጥ ልብ
  10. ሽብር እንደ ቢዝነስ ዶላር ለመግኘት ከምዕራቡ ኦለም በተላላኪ፡ ቅጥረኛ፡ በመሆን የአከባቢው ሰላም፡ ፍቅር፡ አንድነት ማፍረስ፡ ብቻው የመኖር ማየት በህልም መኖር ልብ

Speak Your Mind

*