“እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ?

የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል።

የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል።

በመሰዳደብ፣ ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል።

ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል።

የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦

“ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።”

“አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች ያየነው ነገር የማይጠበቅ ነው። ይህ በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም”

“ሰውነት የሚለካው በስራ ነው እንጂ በስድብ አይደለም። የአብይን ስራ ማሳነስ በእጅ መዳፍ የፀሃይን ብርሃን መከላከል እንደማለት ነው።”

“ሽማግሌ ሆኖ ልትፈርስ የነበረችን ሀገር ያዳነና ሰላምን ያወረደው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ነው። ይህን ደግሞ ዓለም ሁሉ መስክሮለታል። እኛ እንደ ቄሮ ማንም ሰው እንዳሻው የሚጫወትብን መሆን አይገባንም።”

“እኛን እየሰደበ እና የአንድ አባት ልጆችን ለማባላት የሚመጣብንን ሰው አንፈልግም። የሚያጋጨንን ሰው በፍፁም አንቀበልም”

“እኛ ከአባጅፋር  የተማርነው አቃፊነትንና በአንድነትና በወንድማማችነት በጋራ መኖር ነው። እኛ ረገጣና ጭቆናን ነው የምንቃወመው”

“ስድብና ጥላቻ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የለውም። ህብረተሰቡ አብሮነቱን የሚያጠናክር እሴቶችን ሊጠብቅ ይገባዋል”

ዋልታ ያጠናከረው ቪዲዮ ከዚህ በታች ይገኛል፤

ከዚህ ሌላ ሐሙስ በጅማ ስታዲየም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል። በርካታ ቁጥር ያለው የጅማ እና አካባቢው ነዋሪ ከጥዋት ጀምሮ ወደ ስታዲየም ሲያመራ እንደነበር የጅማ ከተማ ቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

ምን አይነት መልዕክት ነው እየተላለፈ የሚገኘው ብለን የጅማ ቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ጠይቀናል፦

 • ዶ/ር አብይ አህመድ የሰራውን በጎ ስራ በማጣጣል የሚመጣ ለውጥ የለም፤ ሀሳብ ያላቸው ለህዝቡ ሀሳብ ያቅርቡ።
 • ስድብ፣ እና ጥላቻ ባህላችን አይደለም፤ የሀገር መሪዎችን በአደባባይ መሳደብና ማንቋሸሽ ከባህላችን ያፈነገጠ ነው።
 • ሀገር ማስተዳደር የሚገልጉ ሰዎች ሀሳባቸውን ሽጠው በምርጫ ይመረጡ፤ ከዛ ውጪ ስድብ እና ማንቋሸሽ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ተገቢነት የለውም።
 • እኛም ዶክተር አብይ አህመድ ነን!
 • የተለያዩ ሀሰተኛ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የኦሮሞን ህዝብ ለመከፋፈል የሚሰራው ስራ ሊቆም ይገባል።
 • ዶ/ር አብይ የሰላም እና የብልፅግና አባት ነው!
 • እኛ የአባጅፋር ልጆች አቃፊዎች ነን!
 • ስድብ እና ጥላቻ ተቀባይነት የለውም!
 • ጅማ መሬትም ሰውም አለ!
 • ጊዜው የዶክተር አብይ ነው!
 • ከዶክተር አብይ ጋር ወደብልፅግና እንሻገራለን!

ሠልፎቹን መንግሥት አበል ከፍሎ ነው ያስተባበረው?

የማህበራዊ ሚዲያዎች ርዕስ የነበረው ጉዳይ ትላንት በጅማና አጋሮ የተደረጉት ሰልፎች መንግስት አበል ሰጥቶ ያስተባበረው ነው እንጂ ሰዎች ፈልገው ያደረጉት አይደለም የሚል ነበር።

ለዚህ ጉዳይ ቢቢሲ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ላይ የሠልፉ አስተባባሪ እንዲሁም ተሳታፊ የጅማ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ድማሙ ንጋቱ፦ “አበል መክፈል ይቅርና ቲሸርቶቹንና መፈክሮችን ለማሳተም እንኳ መንግሥት ምንም ዓይነት ገንዘብ አላወጣም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ምንጭ፤ የቲክቫህ ጅማ ቤተሰቦች

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Speak Your Mind

*