የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!

ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር!

ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ሳያስበው አስፈነጠረው እንጂ የመለስና ዋናዎቹ የህወሓት መሥራቾች  ዕቅድ ይህንኑ ለማሳካት እንደሆነ ሰሞኑን በተከታታይ በምናትመው የአቶ ገብረመድኅን ጽሁፍ በግልጽ የተቀመጠ ሐቅ ነው

የወቅቱ የፍጅት ዓላማ ደግሞ ኦሮሞን ከሶማሊ ወገኖቹ ጋር በማጋጨት የአገዛዝ ዘመኑን ማራዘም፤ ሁለቱን ጎሣዎች በማይረሳ ቂምና ጥላቻ ውስጥ ማስገባት፤ ይህንንም እስካሁን በሌሎቹ ጎሣዎች መካከል ከፈጠረው ጥላቻና ቁርሾ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያን ኅልውና አጥፍቶ የትግራይን የበላይነት ማስፈን ነው። ለዚህ ደግሞ የሚደግፉት ከሁሉም ጎሣዎች የተውጣጡ ጥቅም ያሰከራቸው ወሮበላ ጎረምሶች መኖራቸው የሚካድ አይደለም።

አሁንም ከተቀናጀ ኅብረት፤ አሁንም ትኩረት ሁሉ ህወሓትንና ማንነቱን ተረድቶ ከመዋጋት ያነሰ አስተሳሰብ እስከተያዘ ድረስ ውጤቱ ንጹሐንን ማስፈጀት ብቻ ነው የሚሆነው። የሐረርጌ ሙስሊም ኦሮሞና ሙስሊም የኢትዮጵያ ሶማሊ ሊፋጁበት የሚችሉበት ምንም ምክንያት የላቸውም። (ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)

የሰሞኑን የህወሓት ግፍ በተመከለከተ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የዘገበውን ከዚህ በታች አስፍረናል።

በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች ወሰኖች ባሉ ወረዳዎች ውስጥ እየተካሄደ ካለው የጥቃት እርምጃዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከሰማሌ ክልል የተፈናቀሉ ከአርባ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ምሥራቅ ሃረርጌ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጭናቅሰን ውስጥ ዛሬ (አርብ) በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚሁ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ቀውስ ጋር ተያይዞ ጎረቤት ሶማሌላንድ ውስጥ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያጠፋ ጥቃት እየተፈፀመባቸው መሆኑና ከፍተኛ ሥጋት ላይ እንደሚገኙ እየገለፁ ናቸው።

ሃርጌሣ ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገድለው አንደኛው ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የሶማሊላንድ የፀጥታ ሚኒስትር ዴኤታ አስታውቀዋል።

ሶማሊያዊያኑ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ ጥሪ ያስተላለፉት ሚኒስትር ዴኤታው ሞሐመድ ሙሣ ዴሬ ለኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ጥበቃ እንዲያደርጉ ኃይሎቻቸውን ማዘዛቸውን አመልክተዋል።

በሌላ በኩል በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ላይ ከተፈፀመው ጥቃቶችና እየታዩ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዙ ሁከት አዘል ጥቃቶች አወዳይ ከተማ ውስጥ ቁጥሩ የበዛ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎም የሰፋ መፈናቀል ከጅጅጋ እና ሌሎችም የሶማሌ ክልል ከተሞች መከተሉ ተነግሯል።

ማክሰኞ ዕለት መስከረም 2/2010 ዓ.ም. አወዳይ ከተማ ውስጥ ሁከት የቀላቀለ ሰልፍ ያደረጉ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት ሃምሣ ሰው መገደሉን የሶማሌ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢድሪስ ኢስማኤል ለቪኦኤ የገለፁ ሲሆን የኦሮሚያ ክልል አቻቸው አቶ አዲሱ አረጋ ግን አድራጎቱ መፈፀሙን አረጋግጠው የተገደለው ሰው ቁጥር ግን 18 መሆኑን ከመካከላቸውም 12ቱ የሶማሌ ተወላጆች ስድስቱ የኦሮሞ ጃርሶ ጎሣ አባላት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በተፈፀመው ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እንደሚያዝን ቃል አቀባዩ ጠቁመው ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ በጥቃቱ ላይ ተሣትፈዋል የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ መሆንን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ይህንኑ የአወዳይ ጥቃት ተከትሎ ከሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂጂጋ ከ21 ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሎ ጭናቅሰን፣ ባቢሌና ሐረር ከተሞች ውስጥ የተጠለሉ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮችና የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ አመልክተዋል፡፡

ስለዚህ የመፈናቀል ጉዳይ ምላሽ የሰጡት የሶማሌ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ኢድሪስ ኢስማኤል ሶማሌ ክልል ውስጥ የሌላ የማንም ብሄር ብሄረሰብ አባል የሆነ ነዋሪ አንድም አለመነካቱንና ሰዎቹ እየወጡ ያሉት በፈቃዳቸው ነው ቢሉም ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ግን የምንፈርመው ተገድደን እንጂ መውጣት ፈልገን አይደለም ብለዋል።

እንዲያውም የልዩ ፖሊስ አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ ትዕዛዝ እንደሰጧቸውና መጠጊያ ፍለጋ ሸሽተው በገቡባቸው የጦር ካምፖች ውስጥ ሁሉ ሳይቀር የደበደቧቸው መሆኑን፤ የተገደሉ ሁለት ሰዎችን በሸራ ጠቅልለው ሲወስዷቸው ማየታቸውን አንድ ተፈናቃይ ተናግረዋል።

አቶ ኢድሪስ በሰጡት ተጨማሪ መረጃ በአስራ አንድ የሶማሌ ወረዳዎች አካባቢዎች ውስጥ በተሠነዘሩ ጥቃቶች እስካሁን የሁለት መቶ አስራ ሦስት ሰው ህይወት መጥፋቱንና አርባ አንድ ሰው መቁሰሉን ገልጸዋል።

ጥቃቶቹን በኦሮሚያ ወረዳዎች ላይ እያደረሰ ያለው የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ነው መባሉንም አቶ ኢድሪስ አስተባብለው የኦሮሚያን ከፍተኛ አመራር አባላት የዘር ፍጅት በመምራት ወንጅለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ ይህንን ክሥ የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት አቋም ነው ብለው እንደማያምኑ ጠቁመው “የራሳቸውን ጥፋት ለመሸፋፈን የሚሉት፣ ኃላፊነት የጎደለውና ከአቶ ኢድሪስ የአቅም ብቃት ማነስ የመነጨ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

Comments

 1. መለስ ከመነሻው ገና ከጅምሩ
  ህገ መንግስት ነድፎ ነበር ላገራችንና ላገሩ
  ግን ቆየት ብሎ ሰንብቶ
  በዚያው ባቋቋመው ፓርላማ ሰግቶ
  ሌላውን ትጥቅ አስፈትቶ
  እሱ ታጥቆ ታጅቦ ዝቶ
  እየመረጠ አስሮ አንገላቶ
  ማስፈራራትን ተያያዘው
  የፓርላማ አባላቱም ለጉድ አለው
  ግን እኮ አልቆየም ፈጣሪ ከረበተው
  ማን ተካው? ማነው ስሙ?
  የመንግስቱ አባት ነው ደሙ??
  የታጠቀው ሰራዊታችን
  የህገ መንግስቱ አለኝታችን
  የምንኮራበት ዋስትናችን
  እንጂ መች እንደ መንግስቱ
  ሰራዊት ዘራፍ ባይ በየታቦቱ
  የሻብያ የወያኔ ራቱ
  አላማየለሽ ባለኮተቱ!
  ለህዝብ የቆመ ከመሰረቱ
  ኧረ ወዲያ! ታዲያ እንደ መንግስቱ??
  የህገ መንግስታችን አለኝታ!
  የማንጠራጠር ላንዳፍታ!
  ለሁሉም ብሄር እፎይታ!
  ታሪክ ሰሪ ባንዳፍታ!
  የህዝባችን አለኝታ!!

 2. ውድ ጎልጉል፣
  የጋዜጠኛነት ሙያ አክብራችሁ ርዕሠ አንቀጽ ስለምትጽፉና አስተያየቶችን ስለምታሰተናግዱ በቅድሚያ ላመስግናችሁ። ከላይ የሚታየው ጠመንጃ ያነገቡ ሕጻናት ፎቶ፣ ህወሓት ተተኪውን በነፍሰ ገዳይነት እያሠለጠነ ለመሆኑ መረጃ ነው። የረጅም ጊዜ እቅድ ስለያዘ የአገር ውስጡን ሚድያ ተቆጣጥሮታል፤ አሜሪካኖችን በሽብርተኞች ምክንያት አግባብቶ በገዛ ሕዝቡ ላይ የስለላ መረብ ዘርግተውለታል። አሁን ደግሞ የአልጀዚራ አዲስ አበባ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ኤርትራዊ መሐመድ ጠሃ ተሹሟል፤ እዚህ ጠቁም http://awate.com/tewekel-manages-the-new-al-jazeera-office-in-addis-ababa/ [ስብሃት ነጋ ይታይሃል?]። መሐመድ ጠሃ ቀደም ሲል የቱርክ ዜና አገልግሎት አናዶሉ ኃላፊ ነበር [ከላይ ፎቶውን ተመልከት]። የህወሓት አባላት በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተሠግስገዋል። ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም ጤና ድርጅት፣ ሙሉ ቀጸላ፣ መሐሪ ታደሰ፣ ሐዲስ ታደሰ፣ ሙሉጌታ ገ/ሕይወት፣ ወዘተ ወዘተ። ሥራዬ ብለህ ብትከታተል የተዘረጋውን መረብ ስፋት ማየት ትችላለህ። የሚያሳዝነው ዶ/ር ብርሃኑ በሽብር ፈጣሪነቱ ዓለም የፈረጀውን ኢሳይያስን [ያውም የተመሰከረለት የኢትዮጵያ ጠላት] መጠጋቱ ነው። ትልቅ ሥራ ያለው በሚድያ ሆኖ ሳለ የጦር አመራሩን ኢሳይያስ ይዞለት ነገ ሥልጣን እይዛለሁ የማለቱ ጅልነት ያሳዝናል። ትልቁ ጉዳይ አሜሪካኖችን እንግሊዞችን አውሮጳን በምድራችን ህወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና ምዝበራ ማሳመን ሲሆን፣ በእነርሱ ድጋፍ የቆመን መንግሥት ያለእነርሱ ድጋፍ እዋጋለሁ ማለት ቂልነት ነው።

 3. ወያኔ ያልገባበት ቀዳዳ የለም። በአሜሪካ ሃገር ውስጥ ደም ያፈሰሱና ያፋሰሱ ያለምንም ፍርሃት እንደሚኖሩ የታወቀ ነው። በኬኒያ/በየመን/ በሱዳን/በግብጽና በሌሎችም የአፍሪቃ ሃገሮች ወያኔ በተላላኪዎቹ በኩል ጉቦ በመስጠትና በማባበል ስደተኞችን ያተራምሳል፤ ይገድላል፤ ሲሳካለትም አፍኖ ሃገርቤት ይወስዳል። ከተዘረፈው የሃገር አንጡራ ሃብት ለወያኔ ደጋፊዎች የነዳጅ ማደያ፤ ቤት፤ የምግብ ቤት፤ የመኖሪያ ቤት እየተገዛ እንደሚታደላቸው ድብቅና ሾልከው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
  በሃገር ቤት በወታደራዊው፤ በኢኮኖሚው መስክ ላዕላይና ታህታይ መዋቅሩን ወጥረው የያዙት የዚሁ መሰሪ አባላት ብቻ ናቸው። የአማራ፤ የኦሮሞ የደቡብ ክልል ተወካይና ተጠሪ የሚባሉት ተለጣፊ ድርጅቶች ሁሉ የሚበላ ተመልካች ናቸው። ለሃገርም ለወገናቸውም የማይጠቅሙ የወያኔ ጀሌዎች። ወያኔ ለሃገር አንድነትና ብርታት አስቦ አያውቅም። ለትግራይ እንጂ! ህዝባችን አክ እንትፍ ብሎ የተፋቸው እነዚህ ወስላቶች በጸረ ሙስናና በጸረ ሽብርተኝነት ስም የሚያጉሯቸው ሁሉ ለሃገራቸው አንድነት የሚሰሩ፤ የዘር ፓለቲካ አሻፈረኝ ያሉና የወያኔን የዘረፋ ሚስጢር ያወጣሉ ተብለው የሚገመቱትን ነው። ሽብርተኛውና ዘራፊው ወያኔ ነው። የገበሬ ማሳና የሳር ጎጆ እያቃጠለ ረሃብ ሃገራችን ገባ በማለት የተራድኦ ድርጅቶችን የሚማጠን ጠኔ ልማዱ የሆነ ድርጅት ነው። ወያኔ አሁን በኦሮሞና በሶማሊያ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ ለኮሰው እሳት በአርሲና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ሃገራችሁ አይደለም አማራ ውጡ በማለት ከህጻን እስከ ሽማግሌ በቆንጪራ እየተገዳደሉ በገደል የተወረወሩትን ወገኖቻችን ትዝ ያስብላል። ወያኔ ፋሺሽታዊ ነው። ወያኔ የሰው ሞት አይገደውም። የሚያስበውና የሚተነፍሰው በዘሩ ዙሪያ በመሆኑ ለሌላው ወገናችን ሰላምን ተመኝቶ አያውቅም።
  በአንጻሩ ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ድርጅቶች (ግንቦት 7 ጨምሮ) በሻብያ ከለላ ሥር ሆነው ሃገርን ማዳን አይችሉም። ሻቢያ ሃገራችን ዛሬ ላለችበት አረንቋ ዋናው ተጠያቂ ነውና። ሻቢያና ወያኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ትላንት በሃገር ውስጥ በሚጽፋቸው ከፋፋይ መጻጽፍት ይታወቅ የነበረው የሻብያና የወያኔ የስለላ መረብ አገናኝ መኮነን ደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ ዛሬ በአስመራ ዋና ስራው ሻቢያንና ወያኔ በሚስጢር አሰራር ማጣመር ነው። ለዛ ነበር የግንቦት 7 ታጋዮች ገና ወንዝ ሳይሻገሩ የተገደሉትና የተማረኩት። ለዛ ነው አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በወያኔ ሊጠለፍ የበቃው። ሻቢያ ለኢትዮጵያ አንድነትና ህብረት ገዶት አያውቅም። ነጻ ወጣን፤ ድል አረግን እያለ በየአመቱ ከበሮ የሚመታው ሻቢያ የከበሮው ቃናና ግጥም በ 25 ዓመታት አልተቀየረም። የደንቆሮ ዘፈን መልሶ መልሶ እንዲሉ ያንኑ ወንድምና እህቱን የገደለበትን ጀግንነት እንደ ጀብድ ቆጥሮ የሃገሪቱን ባንዲራ በየጊዜው አካኪ ዘራፍ እያለ በሚረጋግጥበት ምድር ሻቢያን ታምኖ ማንም ድርጅት ወያኔን መታገልና ሃገራችንን ማዳን አይችልም። ከላይ አስተያየት ሰጪው እንዳሉት በፎቶና በመረጃ የተደገፈ የወያኔን ወንጀል በዝርዝር በማስቀመጥ የዓለም ህዝብ እንዲያውቀው ማድረጉ ጠበንጃ አንግቶ ጋራና ተራራን ከመውጣትና ከመውረድ የተሻለ ውጤት ያስገኛል እላለሁ። ከመካከላችን ተሰግስገው ለወያኔና ለሻቢያ ወሬ አቀባዮች የሆኑትን ለይቶ በምንኖርበት ከተማ ባለስልጣናት ማስታወቅ ተገቢ ነው። በበረሃ እያሉም ሆነ አሁን በህዝባችን ላይ ወንጀል ሰርተው የተደበቁን ሁሉ በመረጃ ክስ ልንመሰርትባቸው ይገባል። ህግ ባለበት ሃገር ወያኔና ተላላኪዎቹ ማፈር አለባቸው። በተረፈ በዘርና በጎሳ በተሰመረች ሃገር አንድ የአንድን አንገት ቢቀላ እግዚኦ አያሰኝም። ወያኔ ህዝባችንን ያመቻቸው ለእልቂት ነውና! በዚህ ግጥም ልሰናበት። የግጥሙ ምንጭ አላውቀውም። የራሴ ግን አይደለም፡
  በጊዜ የምንገባው ….. ማምሸቱን የተውነው፤
  ሌባ ወም ሰይጣን .. አይደል የፈራነው፤
  ማጅራት መቺዎች… ፅልመት ተገን አርገው
  ስላሉ ገዢዎች …. እነርሱን ፈርተን ነው።

Speak Your Mind

*