በአዲስ አበባ፣ አውሮፓና አሜሪካ ለ“ዘመቻ ዓቢይ” የስውር ምልመላ ተጀምሯል! የ“ዘመቻ ዓቢይ” - አዝማቾችን ዓቢይ ያውቋቸዋል?

  • ኃይሌ ገብረሥላሴ መልማይ መሆኑ ታወቀ

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዳላስ ሊያካሂድ ያሰበው ሰላሳ አምስተኛ የስፖርት ፌስቲቫል ከወዲሁ እጅግ ጥንቃቄ በሚያሻው ጉዳይ ተወጥሯል። የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች እንዳሉት በአገር ውስጥ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የሕዝብ ግንኙነት የሚሠሩ ክፍሎች በምሥጢር እየተመለመሉ ነው። ኃይሌ ገብረሥላሴ አገር ውስጥ ሆኖ ይህንኑ የምልመላ ሥራ እየሠራ ነው። አነጋጋሪ የሆነው ይህንን ዘመቻ የሚያከናውኑት ክፍሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ እውቅና ይኑራቸው አይኑራቸው አለመታወቁ ነው።

ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ በፖሊሲ ጉዳዮች፣ ሕዝብ ባነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች፣ አፋኝ ህጎችን ከማንሳት አኳያ፣ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ከመፍታትና የአስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ ቀጣዩ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆን ምርጫ ቦርድን ከማፍረስ ጀምሮ ተግባራዊ ውሳኔ ያላሳለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ዳላስ በሚካሄደው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ፈቃድ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው በምሥጢር  የሕዝብ ግንኙነት ሥራ የሚሠሩ ሰዎች እንዲመለመሉ የተደረገው።

እንደ ጎልጉል መረጃ ሰዎች ከሆነ ለህወሓት/ኢህአዴግ በአገር ውስጥ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የውስወሳና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ እንዲሠሩ የታጩትን የሚያነጋግረው ኃይሌ ግብረሥላሴ ነው። “ዳያስፖራውንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማቀራረብ ነው ዓላማው” በሚል በግል ሰዎችን የሚመለምለው ኃይሌ፣ የማግባባት ሥራውን በስልክ ሲሠራ በተጠቀሱት ቦታዎች የሚዲያ ሥራ የሚሠሩ፣ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ የሚያከናውኑና የማግባባት ሥራ የሚሠሩ ሰዎች እየተመለመሉ መሆኑንን አረጋግጧል።

ቀደም ብሎም ቢሆን ጎልጉል በአሜሪካ በምሥጢር ሰዎችን የመመልመልና የማደራጀት ሥራ በኤምባሲው እየተሠራ መሆኑ መረጃ ደርሶት ነበር። ነገሮችን በጥበብ መያዙና የጉዳዩን አካሄድ መከታተል አስፈላጊ በመሆኑ በወቅቱ ይፋ አላደረገም። ይሁን እንጂ ይህ የውስጥ ለውስጥ አሠራር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከተናገሯቸውና አራምደዋለሁ ከሚሉት ጉዳይ ጋር ፍጹም የሚጻረር ሆኖ በመገኘቱ ዜናውን ለማተም ተገድደነናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በርሳቸው ስም የተጀመረውን የምሥጢር ምልመላ የሚያውቁት ስለመሆኑ መረጃ የለም። በተመሳሳይ ይህ ድርጊት ከእርሳቸው ዕውቅና ውጪ በስማቸው እየተከናወነ ላለመሆኑም የጎልጉል ምንጮች ማረጋገጥ አልቻሉም።

ቅቡል ንግግሮችን በማቅረብ፣ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረግ፣ የሴቶችን ሚና በማጉላት፣ በጎረቤት አገራትና በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት ሲማቅቁ የነበሩ ዜጎችን በማስፈታት፣ በሰው በላ ጽንፈኞች ተሰይፈው በረሃ የተጣሉትን ወገኖች አስከሬን እሰበስባለሁ፣ ወዘተ በማለታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቀባይነትን ያገኙት ጠ/ሚ/ሩ በጁላይ ስድስት የኢትዮጵያ ቀን ላይ እንዲገኙ ያቀረቡት ጥያቄ መልስ ሳይታወቅ በምሥጢር ዳያስፖራውን ለመከፋፈል እየተሠራ ያለው ሥራ ከፍተኛ ቅራኔ እንደሚያስነሳባቸው ይጠበቃል።

ከጀርባውም ይሁን ውስጡ ምን እየተሠራ እንደሆነ ያልተረዳው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለውሳኔ እንዳይጣደፍ ሲሉ የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች ጠቁመዋል። እንደ ተባባሪዎቹ ከሆነ ፌዴሬሽኑ ሰከን ብሎ ነገሮችን መመርመር ካልቻል በሰላሳ አምስተኛ ዓመቱ የመቀበሪያውን ጉድጓድ ይቆፍራል።

የህወሓት አንደበትና መልዕክት አስተላላፊ የሆነው ዳንኤል ብርሃኔ ማብራሪያ ሳይሰጥ ፌዴሬሽኑ “ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመጋበዝ ወሰነም አልወሰነም ጉዳዩ የሰሜን አሜሪካውን የተቃውሞ ካምፕ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቦታዎች እንደሚተረትረው ይጠበቃል” በማለት በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

ድንገት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ በተስፈነጠረው መለስ ትዕዛዝ በሌብነት ተጠርጥሮ በሳዑዲ እስር ቤት የከረመው አላሙዲና የእሱ አስፈጻሚ በሆነው አብነት ገብረመስቀል ምልምሎች አማካይነት ዶላር በትነው ሊንዱት፣ ሊያፈርሱት፣ ሊያከስሙት፣ ሊሰነጥቁት ሁሉ አይነት ሙከራ አድርገውበት በሕዝብ ትግል የተረፈውን ፌዴሬሽን መጠበቅ የዚህ ቦርድና አመራር ኃላፊነት እንደሆነም የመረጃው ባለቤቶች አሳስበዋል።

ለህወሓት ስልታዊ አካሄዶች ግንባር በመሆን እያገለገለ ያለው ኃይሌ ገብረሥላሴ በምሥጢር የሚመለምላቸው ሰዎች አድሮ ስለሚታወቁ ከወዲሁ ጥንቃቄ ቢያደርጉ፣ በንግግራቸው የሕዝብን ቀልብ የሳቡት ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህ በሳቸው ስም የተጀመረው ዘመቻ እንደማይመጥናቸው፣ በእሳቸው አባባል ካነገሳቸው ሕዝብ ጋር የከፋ ጸብ ውስጥ እንደሚከታቸው በመረዳት ይህንን የድብብቆሽ አሠራር እንዲያስቆሙ የጎልጉል የመረጃ ሰዎች አሳስበዋል።

“አስቡት” ይላል የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያነጋገረው አስተያየት ሰጪ “አስቡት የአማራን ህዝብ ያዋረደ፣ የሸጠና ለማያባራ መከራ የዳረገው ካሳ ተከለ ብርሃን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ተቀምጦ ንግግር ሲያደርግ … ነፍሰ በሎች በዲስኩር ብቻ አታለውን ፖለቲካዊ ድል በራሳችን ግብዣ ሲወስዱብን” በማለት ፌዴሬሽኑ ራሱን ከታሪካዊ ስህተት፣ ሊፋቅ ከማይችል ውርደት ሊጠብቅ እንደሚገባ ያሳስባል።

በቀጣዩ ምርጫ በግል ከሚወዳደሩት ምልምሎች መካከል አንዱ የሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ያወቀ መስሎት እዛም እዚህም ጥልቅ ማለቱ፣ እጅግ ለሚተላው የህወሓት ጎሰኛ ቡድን ተላላኪ መሆኑ አድሮ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ከወዲሁ እንዲረዳ በተደጋጋሚ ሲነገረው መቆየቱ አይዘነጋም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

  1. በቀለ ኃይሉ says:

    ይኼ ኃይሌ የሚሉት ምን አለ አርፎ ቢቀመጥ? በጣም ተንቀዠቀዠ:: ፖለቲካና ሩጫ አንድ ይመስለዋል ልበል? ያ ርጉም ወያኔ መለስ ባንድ ወቅት ኃይሌ የኢትዮጵያ ፕሬዚዴንት መሆን ይፈልጋል ሲሉት: “ኃይሌ ፕሬዚዳንት መሆን የሚችለው ሰው ሁሉ በእግሩ ማሰብ ሲጀምር ነው” ብሎ አላግጦበታል:: እንደው የምትቀርቡት እባካችሁ ምከሩት!! አፉን በከፈተ ቁጥር የሚወጣው የሚያቅለሸልሽ ነው:: መጥኔ ለሚስቱ!! ይህን ችላ መኖርዋ

  2. I love. You guys.

  3. ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ

  4. “ጠርጠር ገንፎም ውስጥ አየጠፋም ስንጥር” እንደተባለው ሁሉ ሃይሌ ከያዘው አጋንንት እንዲገላገል ወደ ጊሼን ማርያም ሄዶ ፀበል በሚጠመቅ ደግ ነበር። ሌላዋ ልታይ ልታይ ያበዛች ደግሞ ይህች ማን ናት….? አዎ ኣስቴር በዳኔ የሚሏት ሠገጤ ነች። እንዲያው እጅግም ስልት ይቀዳል አፎት እንደሚባለው በሰይፉ ሾው ላይ ቀርባ ሳታፈር ሰይፉ ሳይጠይቃት ከእርሱ ቀዳማ D/ር አብይን የስነ ጽሁፍ ጓደኛዬ ነበር እስከማለት ተቀዥቅዣ ነበር። በኋላ ሰይፉ ፊት ሲነሳት ደግሞ አይ እንደ ቀልድ ነው ያሉኩት ለማላትም ዳድቷታል። ስልጣን ላይ ለወጣ ሁሉ ያዉም የአፍሪካ ቀማኛና ዲክታቶሮችን፤ ጓደየኛ ነበር፡ ጓደኛዬ ነበረች ለማለት እሽቅድድሙን በእነ አስቴር በዳኔ በኩል ሲፈራገጡበት ማየት እነ አስቴር በዳኔ ትምሬእያለሁኡ እያአለ ትመጻደቃለች እንጅ ምን ያህል የበታችነት ሰሜት ላይ እንዳወደቁ ያመላክትታል። ወንበር ወይም ዙፋን ላይ መዉጣትብርቅ ነው እንዴ..? ትኋንም እኮ አልጋን ያተራምሳል…ጎበዝ ? ኡኡኡ ቴ ቴ ቴ ምነው ሸዋ! አስቴር በዳኔ እረ እንረጋጋ።!! በተረፈ የአፍሪካ ወንበር ወይ ስልጣን እንደ ትኋኑ በሰው ደም የሚጨማለቅ የመሆኑ ምስጢር ካለሆነ በቀር፣ ሀብት ለማግኘት ብቻ ነው እንዳይባል ከንጉስ አብይ መሀመድ በላይ የሃይሌ ገብረ ሥላሤ ሃበት የትዬ ለሌ ነው። በተለይ ከዶ.ር አብይ ከሃይሌ ገብረሥላሴ አንፃር ያጣ የነጣ ደሃ ነው ማለት ይቻአላል። የሰው ደም ለማፈሠስ እንዲህ መንቀዥቀዥ ምን ይሉታል አጋንንት ካልሰፈረባቸው በቀር ? መጠኔ ለእነ አስቴእር በዳኔ

  5. በቀለ ሃይሉ ድንቅ ጠርጠረሃል “ጠርጠር ገንፎም ውስጥ አለ ስንጥር” እንደሚባለው ከንጉስ አብይ አህመድ ንግሥና በኋላ ብዙ ቀዥቃዥዎችን እያዬን ነው ። ያች ማነው የሚሏት ….አስቴር በዳኔ ምናምን የርሷም መቀዥቀዥ ቅጥ አጣ ። ምንድር ነው ይሄን ያህል መቀዥቀዥና ማደግደግ – ያውማ ለአፍሪቃ ዘራፊዎችና ቀማኞች። ደግሞም እኮ በሰው ደም ነው ጋኔላቸውን የሚያጥቡ። ታዲያ ለአፍሪካ ዲክታተሮችን በራሳቸው ፈቃድ ስይጠየቁ ሊያስተዋውቁ ጫማ ሲጨርሱ የሚታዩት የእነ አስቴር በዳኔ ዓይነት ብኩኖች አያሳዝኗችሁም። አሁን በቀደም እዕለ ሸህ ሙሃመድ አላሚዱ ቀልቡን የሚሠፍርለት (ቶክ ሾው አቅራቢ ነኝ ባዩ) ሰይፉ ፋንታሁን ቶክ ሾው ላይ ይህችው አስቴር በዳኔ የተባለቸው ሰገጤ ቀርባ፤ ንጉስ አብይ አህመድን ንጉስ ከመሆኑ በፊት በሥነ ፅሁፍ ዙሪያ እንተዋወቅ እንደነበር ሰዎች እንዲያውቁልኝ ብዬ ነው ብላ በለበጣ በሰይፉ ፕሮግራም ላይ ስትለፋድድ ላያት ሰው ላኢላ ኢላላህ ሙሐመድ ሩሱሩላህ የሚያሰኝ አጋንንት እንደሠፈረባት የሚያሳይ ነው።አስቴር በዳኔ ተምሬያለሁ ትበል እንጅ ትምህርቷ ግን የበታችነት ሰሜቷን ሊያርቀው አልቻለም አጃኢብ ነው ይብላኝ ለወለደሽ እንጅ ያገባስ ይፈታል እንዲሉ። አሁን ማን ይሙት who cares about it ዶ/ር አብይን አወቀችው አላወቀቸው ? ስለራሷ ያላትን ገመት ያሳይ ካለሆነ በቀር። እንዲያው ለነገሩ ስልጣን ለወጣና ሃበት ላለው ሁሉ ማደግደ ለአስቴር በዳኔ አይነቱ ብርቅ ነው እንዴ…? ለማደግደግ ደግሞ የሚያስፈልገው ንጉስ ነኝ ብሎ ዘፋን ወይም ስልጣን ላይ መውጣት ከሆነ ትኋንም እኮ ዙፋን ላይ ወጥቶ ያታራምሳል ። ሀቁ ግን ትኋኑም ሆነ የአፍሪካ ዲክታተሮች ምሳቸው ያው አንድ አይነት የሰው ደም ነው። አፍሪካ ውስጥ ዙፋን ላይ መዉጣት ወይም ንጉስ መሆን ምንድን ነው የሚያስፈነድቀው? ላተወሰነ የሥልጣን ዘመን የራሳቸውን ዜጋ እያሰቃዩ ቀጥቅጦ መግዛት ነው እንዴ ጮቤ የሚያስረግጠው ? ደግሞስ የአፍሪካን ዲክታተሮችን እንዲህ ብዬ ደፍሬ ጠየኩት፤ እንዲህም ብዬ ደፍሬ በመናግሬ እኔ ከተናገርኩት ቃላት ወሰደው እንዲጠቀሙ አደርግሁ ብሎ መፏለለ የሚያሳየው፤ የጠያቂየውን ደፋርነት ሳይሆን በሰው ደም የሚጨማለቁ የጨካኝ ዲክታተሮችን ግልጽ ባህሪ አበጅጃችሁ ቀጥሉበት ብሎ እንደማወደስና ፊሻካ እንደመንፋት ነው። የባርነት mentality ሰብዕናና ስነ ልቡና ያላቸው ጩልሌዎችም የሚገለጹበትም የባህሪ ገንዘባቼው አድርባይነት ነው ። ሃይሌ እንኳ እዉነት ለመናገር የሚረዳው አጥቶ ነው እንጅ ጌጤ ዋሜ ላይ እንደዚያ ከሚደነፋ ራሱ ሃይሌ ገብረሥላሴን እጁን ይዞ ወደ ግሽን ማርያም በመውሰድ ፀበል ቢያስጠምቁት የያዘው መገኛ ይፈወስለት ነበር። ሃይሌ እኮ ታሟል ለራሱ አልታውቀውም እንጅ ። ግን ደግሞ ኃይሌን ተከትለው ጨረቃቸዉን ሊጥሉ ያቆበቆቡ ሰው መሳይ በሸንጎዎችም በተጠንቀቅ ላይ ቆመው እየጠበቁ ነው እነ አስቴር በዳኔ ለሚመለከት ሰው ሃ ሃ ሃ … እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣል አሉ ። God Bless Ethiopia

  6. I have a respect for the new Prime Minster Dr. Abiy. Dr. Abiy is still a very controversial leader from his background to his flowery speech not yet supported with his deed. Controversial as he is, he is also divisive. He has many supporters filled with emotion while he also has opponents who are cautious. Personally, I believe the request for attending ESFFNA is not sincere, it is to create division. The way out for the Federation is to stick with its core principle of no politicians. Let us remember the time with Birtukan Mideksa. Do the same, this is a sport gathering, entertainment not a place of political reflection. If Dr. Abiy wants a real participation with the occasion, he can do it from his office with official speech or letter to all attendee.

  7. Everywhere I read about Dr abiy’s Presence in N. America Ethiopian Annual football torament event has become more and more and more controversial. For traditionalist Ethiopians it is disrespectful to deny a big personality like PM. Academicians, postulating that nothing happens out of the ordinary, so that it is advategeous to have the PM. Supporter or those who do not support try to rationalize their side of case no matter what. The sucpicion and fear of politicians is understandable. There is a group that positioned itself to exploit the the whole event. Does Dr. Abiy know all of this? I believe, by this time he is well aware the honesty and innocence of the Ethiopian people. One of the integrity of a leader not to mishandle, misuse such profound honest and innocence. I hope he can help in this regard by taking firm decisions.

Speak Your Mind

*