ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ

ላለፉት በርካታ ዓመታት በየአደባባዩ “በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም” ሲል የነበረው ህወሓት/ኢህአዴግ ዛሬ በኃይለማርያም አማካኝነት “እስረኞችን እፈታለሁ፥ ማዕከላዊን እዘጋለሁ” ብሏል።

ባለፉት ዓመታት በግፍ የታሰሩት በሙሉ የተከሰሱት በአሸባሪነት መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ይህ መግለጫ በራሱ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲዋሽ እንደነበር የሚያሳይ ነው ወይም ይቺ ጊዜ መግዣ የህወሓት ጨዋታ ነች።

ለሁሉም በመቆየት የሚታይ ነው።

የእኛ አቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰር የለበትም፥ በግፍ የታሰሩት ሁሉም የፖለቲካ እና የኅሊና እሥረኞች ህወሓት/ኢህአዴግ ይቅርታ እየጠየቀ ካሣ ከፍሎ በነጻ ይልቀቃቸው ነው።

ጎልጉል!

Comments

 1. “ሰበር ዜና፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡
  ___________________________________________!
  ፖለቲከኛ እስረኞች የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም
  ———————————————————–!
  “በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ ወንጀል በመፈፀም ድርጊት ተጠርጥረው በአቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ህግና ህገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እንዲፈቱ ይደረጋል::”-ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ
  *************************!
  *ማዕከላዊ እስር ቤት ይዘጋል ተብሏል..
  __ እርግጠኛ ነኝ ማሰር ቆሟል አላሉም። ይልቁንም ከፍተኛ ቁጥር ዕሥረኛ የሚይዝ፡ ደርጃውን የጠበቀ ዘመናዊ እሥር ቤት፡ በከፍተኛ ወጪ እንደተገነባ ተነግሯል። ዓለም በቃኝ እሥር ቤት ተዘግቶ፡ ኢትዮጵያ በቃችን የሁሉም የቁም እሥር ቤት ሲከፈት እንዲህ ጮቤ ያስረግጣል?

  * ድርድርም ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል…
  ___ አንድ መንግስትና ብዙ ፓርቲ ሰፈርተኞች ቢደረድሩ ጥቅሙና ተጠቃሚው ማነው? የፓርቲ ብዛት ያለጥራት የልዩ ጥቅማጥቅመኛ ማበርከት ተሞሳሟሽና ኪራይ ሰብሳቢ ወሮበላ፡አድርባይ መፈለፈያ እንጂ፡ ለማኅበረሰቡ የሰላም፡ የእኩል ተጠቃሚነት፡ የትምህርትና ጤና፡ የተቋማት ግንባታ ላልፉት ፳፯ ምንም አልታየም፡ የመድብለ ፓርቲ፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፡ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት(ብዝሃነት) ማጣፈጫ የዜናና ለፎቶ ለማስረጃነት ጥሩ መናጆ ሆነው ከውስጥም ከውጭም እያጭበረበሩ ፡ትውልድ ሲያጥበረብሩ…ሀገርና የሕዝብ ንብረት በመበዝበር ተቃዋሚ/ተቋቋሚ ሆነው የሀገር ሀብት አብረው ሲመዝብሩ፡ ወጣቱን አላግባብ ጭዳ ሲገብሩ ኖረዋል ይኖራሉም።

  * ክሳቸው በመካሄድ ላይ ያሉ የፖለቲካ እስረኞችም ክሳቸው ይቋረጣል ተብሏል…
  ___ ሀወሓት/ኢህአዴግ ከአጋርና ተደርዳሪ ፓርቲዎቹ ይልቅ ዲያስፐሩን በደንብ ያደምጣል፡ሁሉም እሥረኛ ይፈታ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው ሲያፏጩ ነበር አሁን ችግራቸው ተፈታ አርፈው ይቀመጣሉ? አጀንዳ ቀይረው ይቀወጣሉ?
  እነሱን ብሆን ቅድሚያ የሕዝብ መፈታት አስቀድም ነበር። ለነገሩ ዲያስፐሮቹ ህወሓት/ኢህአዴግ አሰልጥኖ የለቀቃቸው ግብረኅይሎች ስለሆኑ እርስ በርስ ይረዳዳሉ፡ተቃዋሚ ትብዬዎች ግን ትግል ላይ ሳይሆኑ በጎን ልፊያ ተጠምደዋል/ተጣምደዋልም ለምሳሌ፡… አዲስ አበባ አይስፋፋ ሲሉት እሺ፡ ልዩ ጥቅም ይከበር ሲሉት እሺ፡ እሥረኛ ይፈታ ሲሉት እሺ፡ ለነገሩ..ሌባ! ሌባ!…መንግስት የለም ወይ! ሲሉት በሞቀታ ተነሳስቶ ይሆናል።አሁን ያልሰማው ቅላጼ ግን ሰው ከክልል እስረኛነት እያፈተለከ፡ ኢትዮጵያ ኬኛ! ቢመችሽም ባይመችሽም ወያኔ አንለቅሽም! ይናዳል ይናዳል ገደሉ ይህ ነው የኢትዮጵያዊ ገድሉ!ብለዋል፡ ነን ሰቤ?
  ጋዜጠኞች የፖለቲካ እሥራኛ ናቸውን? በሀገሪቱ የነበረው ሰልፍ የፖለቲካ ነው የብሔር ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ትዕይንት? የሚፈቱት ፈረንጅ ያወቃቸው ናቸው?የሀገሪቱ ሕግ አላግባብ ታስረው ነበር አላቸው? ከሆነስ ካሳያገኛሉን?

  *አገዛዙ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን አምኗል…

  __የፖለቲካ እሥረኞች እነማን ናቸው?
  *ፖለቲካ ማለት አቋም/መርህ/ርዕዮት ከሆነ ሰዎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው/አመለካከታቸው ልዩነት ብቻ ለምን ታሰሩ? የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የሰሞኑ ማላገጫ የሚለው “ላጠፋነውና ላሰርነው ይቅርታ ለምናስረውና ለምናጠፋው ታገሱን ጭራሽም ተባብሩን” ነው፡ ታዲህ ይህ ማንን ለማስደሰት ነው? ሜ/ጄ አባዱላ ‘የተናቀው ህዝቡና ፓርቲው’ ጥያቄ የተመለሰውና ‘ወጣ ገባ’ የሆነው ለዚች ነው? እንግዲህ ኦነግ፡ ኦብነግ፡ ግንቦት ፯፡ መስከረም ፪፡ ታስረው የተፈቱ ያፈነገጡና የተባረሩ ግንቦት ፳፯ ፓርላማ ሊገቡ ነው?፡ ኢሳትና ኦሮሞ ሚዲያ ከአሸባሪነት ነጻ ሆኑ ማለት ነው? መቼም እየጻፈ ፖለቲካ የሚተች እስክሪብቶ ማምረቻን በመዝጋት ፀሐፊን መግታት ይቻላል ማለት ድድብና እንጂ ብልሃት አደለም።
  __ የፖለቲካ ምሕዳር ማስፋት ሲባልም እያሰሩ መፍታት አሮጌውን እሥር ቤት ማዕከል አድርጎ ሲዖል በመገንባት ሳይሆን የተተቹበትን ስሕተት ማመንና ማስተካከል፡ ጭራሽም መካሪ አታሳጣኝ ሲሉ ሚዲያና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በሕግና ሥርዓት መጥኖ (ከብዛት ጥራት) እንዲደራጁ መፍቀድና ማገዝ የግድ ነው።
  __የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸው ሚዲያ፡ የተሟላ ጽ/ቤት ተገቢውን የሕግ ከለላ፡ ተመፅዋች (አሳውቀውና አስፈቅደው) በሙሉ የዜግነት ነጻነት፡ እንዲኖራቸው ማድረግ ግን የበለጠ ለገዢው/አውራው/ ነጻ አውጭው ፓርቲ፡ ተቋማቱና ደጋፊ/ተደጋፊ አባላቱ ዋስትና ነው።ለሀገር ሠላምና ደህንነት እሥረኛ ቅነሳ፡ ከአላግባብ የሕዝብ ንብረት ብክነትና ውድመት ያድናል ።አራት ነጥብ።

 2. Exactly! These prisoners & families need compensated! Imagine the damag that has taken place within the families. How many have died in the prisons? How many have lost their their income, directly or indirectly? How many have migrated, or died on the desert and sea shores?

Speak Your Mind

*