የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ

 • ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል

በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል።

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት ብቻ በሥልጣን መንበር ላይ ሲንገታገት ቆቷል። ሕዝብ ፊቱን ካዞረበት ቢቆይም በተለይ ትውልድ ካመጸበት ወዲህ ግን የአገዛዙ ኃይል እንደ ሹራብ ክር መጎልጎል ጀምሯል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራና በኦሮሞ ቦታዎች የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ህወሓት በኢህአዴግ ሥም እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራቸው ብአዴንና ኦህዴድ “ሕዝባቸውን” መምራት የተሳናቸው መሆኑን ያስመሰከረ ሆኗል። የእነዚህ ሁለት ድርጅቶች የበታች አመራሮች መክዳት በስለላና በጥርነፋ ሁሉንም “ልክ አስገባለሁ” እያለ የሚፎክረውን ህወሓት ከራሱ የውስጥ ችግር ጋር ተዳምሮ የማይለቅ ራስ ምታት ሆኖበታል። እንደ አንዳንዶች አገላለጽ ሁለቱን ድርጅቶች አራቱም ጎማው ወልቆ መንገድ ዳር ከቆመ መኪና ጋር ያመሳስሏቸዋል።

የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተጀመረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሁኔታውን በዘገበበት ወቅት ስለ ኦህዴድ መክዳት ይህንን ብሎ ነበር፤ “ሳምንታት ያስቆጠረውና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በማድረግ የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ ልዩ እየሆነ መሄዱ ኦህዴድ ኢህአዴግን የመክዳቱ ማስረጃ ነው ሲሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ለጎልጉል መረጃ የሚያቀብሉ አመራር አስታውቀዋል።

“በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ፤ ስለላ፤ ሕዝባዊ አደረጃጀት፤ ቁጥጥር፤ … መዋቅሮችን ሁሉ አልፎ ይህንን ያህል ሕዝብ ያለአንዳች ከልካይ መውጣቱ አገዛዙ ሕዝቡን ለመጠርነፍ የተጠቀመበት አሠራር መልሶ ራሱን እየጠረነፈው እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ታማኝ ተብሎ የተቀመጠው ካድሬም ሆነ የጥርነፋው መዋቅር ሕዝቡን ሊያስቆም አለመቻሉ የኦህዴድ እምቢተኛነትና ለአገዛዙ ድጋፍና እገዛ ከማድረግ ይልቅ ከሕዝቡ ጋር ለመቆሙ እንደ ዓይነተኛ ማስረጃ ይጠቀሳል”።

የዛሬ ዓመት በጎንደር ከተማ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ በማካሄድ “በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም፤ በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው” ባሉበት ወቅት “ስልታዊ ጥርነፋውን አልፎ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ መቻሉ ብአዴን ህወሃት የሚዘውረውን ኢህአዴግ ለመክዳቱ ፍንጭ ሰጥቷል” በማለት ጎልጉል ዘግቦ ነበር

ይህንን መሰሉ ግልጽ መከዳት ያሳሰበው ህወሓት በቅርቡ በደኅንነት ክፍሉ በኩል የቀረበለትን የመረጃ ትንተና አዳምጧል። እንደ መረጃው ከሆነ በአገሪቷ ላይ ሲካሄድ የቆየው ሕዝባዊ ንቅናቄ ኢህአዴግን ክፉኛ ጎድቶታል። የድርጅቶቹ በሕዝቡ ላይ ያላቸው የበላይነት ካከተመ ሰነባብቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ ሁኔታው በዚህ መልኩ መቀጠሉ በህወሓት አዛዥነት የሚተገበረው የኦህዴድና የብአዴን የጥርነፋም ሆነ የስለላ መረብ መርገቡ የሚያሳይ ሆኗል። በመሆኑም በቅርብ ጊዜ ውስጥ በመላ ኦሮሚያና በከፊል አማራ ክልል የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ እንደሚችል የደኅንነት ክፍሉ ዘገባ ትንበያ ሰጥቷል።

የጋምቤላ ደን በህወሓት ከመውደሙ በፊት

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዘገባው አማራጭ የሚላቸውን “የመፍትሔ” ሃሳቦችን ጠቁሟል። አንዱ፤ ያለውን ኃይል ሁሉ ተጠቅሞ ሕዝባዊ ንቅናቄውን መቀልበስ፤ ሕዝቡን የሚያነሳሱ የፕሮፓጋንዳ መስመሮችን ሁሉ መዝጋት፤ ሌላው በምዕራባውያን አገራት ገለልተኛ ዕገዛ ኢህአዴግን ከተቃዋሚው ጋር ጠረጴዛ ላይ በማቅረብ ወደ ድርድር መምጣት፤ ይህ ካልሆነ ግን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር የሆነው ህወሓት የትግራይን መጻዒ ዕድል በተመለከተ የራሱን አቋም እንዲወስድ ምክር ተለግሶታል።

ምዕራባውያን ፊታቸውን በሕወሓት ላይ ከማዞራቸው አንጻር ሁለቱ አማራጮች ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆኑ ለመገመት የሚከብድ ቢሆንም ሦስተኛን በተመለከተ ግን አሁን አገሪቱ ውስጥ እየተከሰተ ያለው እምቢተኝነት ትግራይን አገር ለማድረግ እየተሠራ ካለው ሥራ በመፍጠኑ ሁኔታዎችን ያወሳሰበ ይመስላል። ሆኖም ከመለስ ዜናዊ “እንኳን ከናንተ ተወለድኩኝ! እንኳንም የሌላ አልሆንኩኝ..” ንግግር ጀምሮ መለስ ትግራይን ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አውጥቶ እንደ ነበር አዜብ መስፍን

ጋምቤላ በህወሓት ከወደመ በኋላ Photo: Ajiem Ogalla

“ምሥጢሩን” እስከተናገረችው ድረስ ትግራይን አገር ስለማድረግ በአስረጂነት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህም አልፎ ሕዝባዊ ንቅናቄው በተነሳበት ወቅት የትግራይ ወጣቶችን ለ“ትግራይን አድን” የውትድርና ስልጠና ከመጥራት ጀምሮ የዛሬ አምስት ዓመት በትግራይ በክልተአውላዕሎ ወረዳ ውስጥ የምትገኘው አብርሃ ወ-አጽብሃ የገጠር ቀበሌ “የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን በማቀጣጠል” በዓለምአቀፍ ደረጃ መሸለም፤ ከአግዓዚያን የትግራይ ድንበር እስከ አስመራ ነው ርዕዮት እስከ ‘‘(ትግራይ) በተፈጥሮ ሃብት አጠባበቅ ባካናወነችው ድንቅ ስራ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእጩነት ከቀረቡ ስድስት (እጩዎች) መካከል በአንደኝነት በመመረጥ የወርቅ ተሻለሚ” መሆን የትግራይን በሉዓላዊ አገርነት የመመሥረት ምልክቶች ሆነው በአስተያየት ሰጪዎች ይቀርባሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. ርዕሱና ሀተታው የማይገናኝ ፅሑፍ ማቅረባችሁ ለአንባቢ ያላችሁን ግምት ያሳያል። ከዚህ በመቀጠል ስለትግራይ በአለም ዓቀፍ ደረጃ መሽለም ስትገልፁ የኢትዮጵያ የግዛት አካል ሳትሆን ራሷን ሉዓላዊት አገር አድርጋ የቀረቀች አስመስላችሁ ስትገልጽ ትንሽ ሀፍረት አይሰማችሁም? እንደአገላለፃችሁ 2ኛ&3ኛ የወጡት የብራዚል እና የቻይና ግዛቶች ሉዓላዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን አለበት ማለት ነው። የአብርሃ ወአፅብሃ ቀበሌ በሰራው የተፈጥሮ ስራ በዓለም አደባባይ እውቅና ሲሰጠው ከሚገባው በላይ ደስ ሊለንና የተራቆተውን የሀገራችን ስነ ምህዳር ለማደስ አርዓያነቱን ተጠቅመን ለተግባራዊነቱ መነሳሳት ሲገባን መዋሸቱ ለምን አስፈለገ?ምንስ ጥቅም ይሰጣል ከማባላት ውጭ?የድረገጹ ዓላማ በርትዕ ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ የዜና ምንጭ መሆን ቢችል ሀገራዊ ጥቅም ሊሰጥ ይችላል አለያ ግን ለራሳችሁም አይጠቅም።

  • Mulatu

   ከአስተያየትህ ጽሁፉ የተፈለገውን ዓላማ ያሳካ ለመሆኑ ራስህ ማስረጃ ስለ ሰጠኸን ከልብ እናመሰግናለን። ለአንባቢዎቻችንም ምን ያህል አክብሮት እንዳለን ያሳየ ዜና መሆኑን አንተን ከመሰለ አንባቢ ምስክርነት ማግኘታችን በራሱ ታላቅ ድል ነው። “ርትዕ” “አገራዊ ጥቅም” … ምናምን ያልከውን ከ26 ዓመታት በኋላ አሁን ስንጠየቅ ለመመለስ ሞከርንና መልሱ ጠፋብን።

   በውነት ያንተው

   የጎልጉል አርታኢ

  • ወያኔ ሃገር ማፍረስ የጀመረው ገና በበረሃ እያለ ነው። ለወያኔ ህብረት፤ ውህደትና አንድነት ጭራሽ የማይዋጥለት እውነት ነው። ዛሬ በዘርና በጎሳ የከለላትን ሃገር ለራሱ እንዳመቸ ሲፈነጥዝባት ዘመናት ተቆጥሮአል። የሚገርመው ግን ጊዜው ሲመሽ እንኳን ጨለማን ከብርሃን መለየት አለመቻላቸው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ከተፋው ቆይቷል። ያው በታጠቀው መሳሪያ እያስፈራራና እያፈነ ዛሬም እንደትላንቱ እኖራለሁ ብሎ ማሰቡ ግን ሞኝነት ነው። በባህርዳር በወያኔ አነጣጣሪ ተኳሾች ወደ ሥራ ስትሄድ ከሞተችው ሴት ቦርሳ የተገኘ ጽሁፍ እንዲህ ይላል።
   ፈጣሪ ጥሩ ነው ዘመን ያሻግራል
   ለእኔም ቀን ወቶልኝ አልፎልኝ በኑሮ
   እናቴን አባቴን እንካችሁ የምለው
   ጊዜው መቼ ይሆን ጥቂቱ ተርቦ
   ብዙው ጠግቦ እሚያድረው?
   ራሷ በጥይት ተቦድሶ፤ ቡናማ ቦርሳዋ አጠገብዋ ሰው ሆን ብሎ እንዳስቀመጠው እስከሬኗን የሚይይ ዓይን ያለው ፍጡር ይመስላል። ፎቶው በብዙ ድህረ ገጾች ላይ ሰውን ያላቀሰ ነው። ወያኔ ዲሞክራሲን አያውቃትም። ዛሬ በሃገር ውስጥ መጽሃፍ ጽፈው ላሳታሚ ከሰጡ በህዋላ አሳታሚውን በማስፈራራት ህትምት እንዲቆም ያደርጋሉ፤ ከባንክ ገንዘብ ይዘርፋሉ። በጥቁር ገቢያ የዶላር ለዋጮች በሙሉ የወያኔ የድብቅ ሰራተኞች ናቸው። በንግድ ዓለም የተቃረናቸውን ከውድድር ያስወጣሉ፤ ያፍናሉ፤ ይገድላሉ። በዚህ ዓመት ብቻ የአሜሪካ መንግስት ስድስት ጊዜ ዜጎቿ በኢትዮጵያ በሚዘዋወሩበት ሥፍራ ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያረጉ ይመክራል። እንደ ፈሳሽ ውሃ በፈለገው ጊዜ ወያኔ የሚቆልፈው የኢንተርኔት አገልግሎት ሰው ለሰው እንዳይረዳዳ ሆን ተብሎ የሚደረግ አፍራሽ የወያኔ ሴራ ነው።
   እንደ አቶ ሙላቱ አይነቱ ወስላታ የጠራ እይታ በማጣት የሚተነፍሱበት ሳንባና የሚያስቡበት ጭንቅላት የተገጠመላቸው በወያኔ የዘር ፓለቲካ ነው። የትግራይ ክልል መልማት ምንንም ቢሆን ደስ ያሰኛል። ይሁን እንጂ የሌላው የሃገራችን ክፍል እየተመነጠረና እሳት እየተለቀቀበት ትግራይ ብቻ አረንጓዴ ሆነች እስይ በሉ ማለት ተጨፈኑና ላሞኛችሁ እንደማለት ነው። የፓለቲካ ወስላቶች የዛሬን እንጂ የነገን አያዮም። እኔን እንጂ እኛን ማለት አይወዱም። ከሌላው የሃገሪቱ ክፍል እየተዘረፈ ትግራይን አለማን በአለም እውቅና አገኘን ማለት ፓለቲካዊ ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም። ስርቆት የሚከበርበት፤ የተማሩና ለሃገሪቱ የሚያስቡ ወገኖቻችን በካቴና ተተፍረው ወህኒ የወረዱበት የወያኔዋ ከቁራሽ ተራፊ ኢትዮጵያ የእብዶች ስብስብ የሚያተራምሷት እድለ ቢስ ሃገር ናት። ያው አንተም ውሻ በበላበት ይጮሃል ነውና ለወያኔ ለማደር የድርሻህን የትርምስ ፓለቲካ ትነዛለህ።
   ታላቋ ትግራይ የወያኔ ህልም እንጂ እውነትነት አይኖረውም። ህልማቸው በአለም መንግሥታት ተቀባይነት የምይኖረው፤ ቀሪውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ነው። እርስ በርስ የሚያስተላልቅ ህልም ነው። ኢትዮጵያ ፈርሳ ትግራይ አትኖርም። ለዘመናት የአማራን ህብረተሰብ እንደ ቀንደኛ ጠላትነት የፈረጀው ወያኔ አሁንም በጎንደር ቅማንት ለራሱ ይሁን እያለ የሚያድበሰብሰው የአማራን ህዝብ ለመከፋፈል እንጂ ሌላ እይታ የለውም። በኤቢሲ የታየውም ካርታ ትክክለኛ ወያኔ የነደፈውን ሴራ ያሳያል እንጂ ማስተባበያ አያስፈልገውም። ወያኔ እኮ ደንቆሮ ነው። አባይን ትግራይ ውስጥ ነው ብሎ መጽሃፍ እንዲጻፍ ያደረገ ጭፍን ድርጅት። እንደሚታወቀው የአባይም ወደ ትግራይ በካርታ ላይ መጠቃለል በስህተት ነው ተብሎ ነው የታለፈው።
   ዘፋኞች የሙዚቃ ድግሳቸውን ለማቅረብ የማይፈቀድበት፤ የመሰብሰብና የመናገር ነጻነት የተነፈገበት፤ በሙስና ስም ሲበሉ ያዮትን እንጂ የበሉትን የማያስር፤ በዘር ችርቻሮ የከበረው የጠባብ ብሄርተኛው ቁንጮ ወያኔ የሮም አወዳደቅ ሲወድቅ ይታየኛል። ዛሬ በፀረ-ሽብር በሙስና እያመካኘ በሃገሪቱ እስር ቤቶች ያገታቸው የወያኔን ድብቅና ይፋ ሴራ የተጋፈጡትን ነው። ሃገር ማለት ለወያኔ ትግራይ ብቻ ነው። የለማው፤ የተሻለ ቀለም መሸመቻ የትምህርት ተቋማት የቆሙለት ለትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ሌላው ፍርፋሪ ለቃሚ ነው። በወያኔው አለቃ ሞት የተነሳ ወያኔ የባለ ብዙ አለቆችና የአዕላፍ ነጭ ለባሾች ስብስብ በመሆኑ መልህቅ እንደለላት መርከብ አቅጣጫ አልባ ነው የሚጓዙት። ጠ/ሚ የይስሙላ፤ ምክትል ጠ/ሚ በጥፊ በወያኔ የሚመታ (በዶ/ር ደብረጽዮን)፤ ጠበንጃ አንጋቹ በወታደርነት ስም የሚዘርፍና ህዝባችንን በሜዳ የሚረሽን የጨካኞች ስብስብ ነው። ወያኔ የጎንደርን ቆላማ ክፍል ለሱዳንና ለራሱ እየሸራረፈ የሚወስደውም የአማራን ህዝብ ለማበርክከ ነው። ሱዳንን አቆላምጦ ካልያዘ በዚያ በኩል የሚገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወያኔን በቀላሉ እንደሚያጠፉት ያውቃል። ምንም ይሁን ምንም ወያኔ ለፈጸመው ሃገር አፍራሽ ሥራው ዋጋ እንደሚያገኝ አምናለሁ። ጊዜው እየቀረበ ነው። ጀሮ ያለው ይስማ!!

   • Messay Dejene Beshah says:

    To the vast majority of Ethiopians the fate of Tigre/Tigrai is already sealed. In all honesty, no conscious Ethiopian would wish to see Tigres as anything but a neigbour.

    Having a common heritage or history does not necessarily lead to a harmonious unity.
    TPLF and its Tigre masses have acted as nothing but a brutal occupation force bent on completely destroying Ethiopia as we know it.

    From fighting alongside Eritreans to ceding vast tracts of land to the Sudan as well as annexing Afar, Benshangul, Gondar, and Wollo, to brazen genocides, they have done it all with impunity.

    Well, the writing is in the wall. Whatever it takes, the Tigre atrocities will be avenged before our borders are redrawn with our blood. Every Nazi German who was alive, was tracked down ruthlessly, thanks to the tireless Israeli intelligence services. Primitive, witless and ostentatious Tigres cannot be likened to the meticulous Germans.

    Criminal Tigres will be herded like lambs from wherever they are and brought to justice. America is not a safe heaven for terrorists and mmoney launderers which Tigres are. The thousands of bottle stores and shopping malls Tigres have opened in Denver, Dallas, Chicago and elsewhere will not shelter them from the American justice system when the day of reckoning beckons.

 2. There won’t be right and wrong if there was no law and/or conscience based culture!
  With the same token, there is no criminal, no terrorist, no liar, no looter, no killer, no racist and no dictator if appraised by Western states and intelligences.
  If ordained or instituted by USA/CIA/UK/etc,
  An absolute criminal is absolutely lawful;
  An absolute terrorist is absolutely wise;
  An absolute liar is absolutely genuine;
  An absolute looter is absolutely righteous;
  An absolute killer is absolutely blameless;
  An absolute racist is absolutely liberal;
  An absolute oligarch is absolutely democrat;
  An absolute dictator is absolutely democrat.

  TPLF is procured, installed, hired and sustained by USA/CIA/MOSAD/UK. Enemy of TPLF is enemy of UK too. Genuine democrat, genuine humanitarian, genuine human, etc. is absolute enemy of UK, USA and their partners. That because such entities object deceit and sadism.

  But, Ethiopians need to hold on humanity!
  Sadist and narcissists shall be shattered like the other times by Ethiopians!
  And humanity will be liberated and cherish in our course again.

 3. ሃ/ማርያም: ሃ/ማርያም!!
  ያገራችን መሪ ድባብ! ተማም!
  ኣንደበተ ርቱእ ለምለም!!
  ቢናገሩት ዓይከፌ ዝናም

  አገር በቀል መጤ ዓይደል
  ያገር ልጅ ጠንበለል
  ዘመድ ለዘመድ ኣፋላጊ
  ሃገር ወዳድ ጠላት ዓስጊ
  ያገር ልጅ ያገር ኩራት
  ሃገራችንን ወደፊት የምናያት
  እንኳን ኣደረሰሽ እንበላት!!!
  ለመጀመሪያ ጊዜ እንበላት!!
  ያንድት የኩልነት ይሁንላት!!
  ባንተ ጊዜ እንኳን ለዚህ በቃሽ እንበላት!!!
  ሃ/ማርያም!! ታደግህላት!!
  ከመበጣጠስ ዓዳንካት!!
  ሁላችንም እንኳን ለዚህ ዓበቃሽ በሏት!!!

  ጠ/ሚ: ሃ/ማርያም በሱዳን ያደረጉት ጉብኝት እጅግ የምደነቅ ስራ ነው!!! ትልቅ የስራ ውጤት ነው!! መሪያችን እናመግኖታለን!!!

 4. I feel pity for “PM” Hailemariam!

Speak Your Mind

*