• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከOMN እንዲነጠል ደጋፊዎች አሳሰቡ፤ መዋጮ ሊያቆሙ ነው

July 13, 2020 05:44 pm by Editor Leave a Comment

“ቴክኖሎጂ የአማራ አክቲቪስቶችን ማንነት አጋለጠ”

በዋናነት ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በሚል የተገንጣይ ወንበዴ ስም በሚጠራው ቡድን፣ አፍቃሪ ትህነግ በሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ደጋፊዎቹና የትህነግን የሥውር ንግድ በሚያከናውኑ ኃይሎች የሚደጎመው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ (TMH) አሁን በሕግ ጥላ ሥር በሆነው ጃዋር መሀመድ ከሚመራው ኦኤምኤን ሚዲያ እንዲለይ ተጠየቀ። ይህ ካልሆነ ድጋፍ ማድረግ ይቆማል።

ይህ የተሰማው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ የተሰኘውና ጃዋር መሀመድ በሂደት የግሉ ንብረት ያደረገው ሚዲያ የሚያሰራጫቸውን ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ዘገባዎች የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ቃለ በቃል እየተረጎመ በማቅረብ መቀስቀሱ አደጋ እንደሚያስከትል ከታወቀ በኋላ ነው።

የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በቅንጅት በተፈጸመ ጥቃት በኦሮሚያ ከፍተኛ ጉዳት መደረሱና ይህ “የግደለው” ዘመቻ አሁን ድረስ ከአገር ውጪ እየተላለፈ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ ዘርና እምነትን መሰረት አድርጓል የተባለው የጥቃት ዘመቻ ለበርካታ ንጹሃን በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል፣ ለንብረት መውደም፣ ለዝርፊያ እንዲሁም ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በዚህም የOMN እና ተመሳሳይ አደረጃጀት ያላቸው ሚዲያዎች ባሰራጩትና እያሰራጩት ባለው የጥፋት ቅስቀሳ መሠረት መንግሥት በይፋ ግብረኃይል አቋቁሞ የዘር ማጥፋት አዋጅ የሚያውጁና የሚያሰራጩ ለሕግ እንዲቀረቡ እየሠራ መሆኑን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።

የአሜሪካ የጎልጉል ዘጋቢ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ እንዳለው ከOMN ጋር ፍቅር በመመሥረት ተናብበው የዘር ማጥፋት አዋጅ እያወጀ ያለው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ መንግሥት ወደ ሕግ እንዲቀርቡለት ጥያቄ ካቀረበባቸው ሚዲያዎች አንዱ መሆኑ ደጋፊዎቹን አስደንግጧል።

መንግሥት ከተቻለ ተላልፈው እንዲሰጡት ካልሆነ ባሉበት አገር በሕግ እንዲጠየቁለት የጀመረው እንቅስቃሴ እየከረረና ትብብር የተጠየቁት አገራት ትብብር ለማድረግ መስማማታቸው ያሰጋቸው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ አጋሮችና ድርጎ ሰፋሪዎች ሚዲያው ከOMN ራሱን እንዲለይ መጠየቃቸውን ዘጋቢያችን አረጋግጧል።

ሚዲያውን በቋሚነት ገንዘብ በማዋጣት ድጋፍ የሚያደርጉ አፍቃሪ ትህነጎች ጥያቄያቸውን አክብሮ ሚዲያው ራሱን ከOMN ካልለየ ለደህንነታቸው ሲሉ መዋጮ ለማቆም እንደሚገደዱ ግልጽ አድርገዋል። እስካሁን በስማቸው በግልጽ ሲረዱ የነበሩት እነዚህ ክፍሎች የሚዲያው በዘር ማጥፋት አዋጅ ክስ ከተመሠረተበት ከተጠያቂነት ስለማያመልጡ ተቋሙ ስማቸውን በስውር እንዲይዝላቸውም ያሳሰቡ አሉ። የሕግ አዋቂዎች እንደሚሉት ግን ትብብር የተጠየቁት አገራት ከተስማሙ በማናቸውም መልኩ ክፍያ የፈጸሙ ሁሉ ስማቸውን ሊደብቁ ወይም መረጃው ሊሸሸግላቸው እንደማይችል ያስረዳሉ። በተለይ ከሴፕቴምበር 11ዱ በአሜሪካ ከደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት በኋላ በሽብር ለሚከሰሱ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የሚደረግ ማንኛውም መዋጮ በማን፣ መቼ፣ የት፣ ስንት ብር፣ ወዘተ የሚሉትን መረጃዎች ማግኘት እንደቀለለ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ OMN በቀጥታ ስርጭቱ ሕዝብ እንዲነሳ፣ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ሲያስተላልፍ የትግራይ ሚዲያ ሃውስም በተመሳሳይ ድርጊት የOMNን ስርጭት ተቀብሎ በማሰራጨት አመጹ ላይ ነዳጅ በማርከፍከፍ ወዲያውኑ መወንጀሉ፣ ይህንኑ ተከትሎ ከድምጸ ወያኔ፣ ከትግራይ ቲቪና ከወዳጁ OMN ጋር እንዲዘጋ መደረጉ አይዘነጋም።

በሌላ ዜና ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኢንተርኔት መዘጋት አንድ ከፍተኛ ምሥጢር ይፋ አድርጓል። “ቴክኖሎጂ የአማራ አክቲቪስቶች ነን የሚሉት አገር ቤት የሚገኙና ስማቸውን ቀይረው የሚንቀሳቀሱ የዲጂታል ወያኔ ተከፋዮች መሆናቸውን አረጋገጠ” ሲሉ አስተያት ሰጪዎች ገለጹ።

አገሪቱን ለማተራመስ በቅንጅት የተወጠነውን ሤራ ለማክሸፍ መንግሥት ኢንተርኔት መዝጋቱን ተከትሎ በአማራ ስም የሚነዙ ቅስቀሳዎች በመክሰማቸው ነው አስተያየቱ የተሰጠው። በዚሁ መሠረት በአማራ ስም በተከፈቱ የማኅበራዊ ገጽ (በተለይ የፌስቡክ) አካውንቶች የሚረጨው ቅሰቀሳ የዲጂታል ወያኔ ተግባር እንደሆነና ምንጩም አገር ቤት በመሆን መንግሥት ማረጋገጥና ምንጩን ለማድረቅ ሊሰራ እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎቹ አመልክተዋል። ራሳቸውን አክቲቪስት እያሉ የሚጠሩትም ለአማራ መብት የቆሙ ሃቀኞች ሳይሆኑ ትህነግ ያሰማራቻቸውና ለዓላማዋ የምትጠቀምባቸው ዲጂታል ወያኔዎች መሆናቸውን የኢንተርኔቱ መዘጋት አጋልጧል ተብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ እነዚሁ ማኅበራዊውን ሚዲያ የሚከታተሉ ወገኖች “አቶ ጌታቸው ረዳ ከፖለቲከኛነት ወደ አክቲቪስትነት አደገ” ሲሉ ተሳልቀዋል። ጌታቸው ረዳ ሰሞኑንን አፍሪካ ውስጥ ሱዳን ወይም ግብጽ ሆኖ ጥላቻን በሚሰብኩ ቅልብ ሚዲያዎች እየቀረበ በተደጋጋሚ ሲወተውት ማየታቸው አስገርሟቸው ነው ይህን ያሉት።

“አክቲቪስት ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በፌስቡክ ቀርቦ “እንዴት ነው አላችሁ፤ እስቲ ገባ ገባ በሉ፤ ድምጼ ይሰማል?” ሲል ይሰማል በማለት ሽሙጥ ተናግረዋል። ከትግራይ ከወጣ በኋላ ለመመለስ ያልቻለው ወይም ያልፈለገው የትህነግ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ፤ መቀሌ የመሸገው የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ህንፍሽፍሽ (ክፍፍል) ውስጥ በመግባቱ የእርሱ መጨረሻው ከማኅበራዊ ሚዲያ አክቲቪስትነት አያልፍም ተብሎ ይገመታል።

በተለይ ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከOMN ጋር ባለው ቁርኝት የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ከገባ ወይም በሕግ ተጠያቂ ከሆነ እንደነ ጌታቸው ረዳ ዓይነት ትህነጎች ካገር ቢወጡ እንኳን የጥገኝነት ወረቀት ለማግኘት ፖለቲካ የሚሠሩበት ሚዲያ የማይኖራቸው ይሆናል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን። 

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: omn, oromia media network, tigray media house, tmh

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule