የምርጫና ነጻነት ቁልቁለት

ያኔና ዛሬ

* ከ45 ዓመት በፊት የፓርላማ ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች

ሰማንያ አራት ዓመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ የመጀመርያው ሕዝብ በቀጥታ የተሳተፈበትና እንደራሴዎቹን የመረጠበት ምርጫ የተካሄደው በ1948 ዓ.ም. ነበር፡፡

በቀዳሚው ምርጫ ካሸነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዷ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ናቸው፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ወ/ሮ ስንዱ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት ዓመት አገልግለዋል፡፡

ከወ/ሮ ስንዱ በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሴቶች እስከ 1965 ዓ.ም. ድረስ በተካሄዱት አምስት ምርጫዎች ተፎካክረዋል፡፡ በ1961 ዓ.ም. በተካሄደው አራተኛው የሕዝበ እንደራሴዎች ጠቅላላ ምርጫ ከመላው ኢትዮጵያ ከተመረጡት 250 እንደራሴዎች መካከል አሸናፊ የነበሩት አራት ሴቶች ሲሆኑ፣ ከተወዳደሩት መካከል 24ቱ ሴቶች ነበሩ፡፡

female mps

ከ45 ዓመት በፊት አሸናፊ የነበሩት እንስቶች ወ/ሮ የሺመቤት ወንድማገኘሁ (ደብረ ብርሃን)፣ ወ/ሮ ምንትዋብ ካሣ (ጎንደር)፣ ወ/ሮ ራቢያ አብድርቃድር (ሊሙ) እና ወ/ሮ ምፅላል ገብረ ሕይወት (ተምቤን) ናቸው፡፡ (ሔኖክ መደብር – ሪፖርተር)

Comments

  1. Bizuayehu Gelanew says:

    Endet tiru neger eyagenen aydelem meselachehu

Leave a Reply to Bizuayehu Gelanew Cancel reply

*