ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል

አሜሪካ ቅደመ ሁኔታ አስቀምጣለች

አሜሪካ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግን ከመውቀስ አልፋ እያስጠነቀቀች ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ የጉዞ ማዕቀቡ እንዲነሳለት እየወተወተ ስለመሆኑ በተለያዩ መገናኛዎች ተደምጧል። የጎልጉል መረጃ አቀባይ የዲፕሎማሲ ምንጮች እንዳሉት አሜሪካ ለኢህአዴግ ጥያቄ መልሷ “ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም” የሚል ሆኗል። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ የአራት ቀን የስራ ቆይታ ባደረገበት ወቅት “በግልጽ ተወያይተናል” የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ እንደሚባለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ለቪኦኤ አማርኛው ክፍል ብቻ መግለጫ የሰጡት ቶም ማሊኖዊስኪ “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት” እንደሆነ መናገራቸው የተደረሰና የተቆረጠ ስምምነት አለመኖሩን ነው።

ረዳት ሚኒስትሩ እንዳሉት “በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ ሥርዓቱን ለዝነተ ዓለም ለማፅናት በሚደረግ ትግል ወይንም ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን አይገባም” ማለታቸውንና “ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል” ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን በማሳያነት የሚጠቅሱ ክፍሎች ተቃዋሚው ጎራና ኢህአዴግ ተያይዘው ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲገቡ አሜሪካ አሁን ላይ የደረሰችበት እምነት ነው። ለዚህም ይመስላል ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠችው።

በውይይቱ ወቅት ለአሜሪካው የልዑካን ቡድን ህወሃት/ኢህአዴግ የጉዞ ማዕቀቡ እንዲነሳለት “በወዳጅነታችን ይሁንባችሁ” ዓይነት ውትወታ ማቅረቡን የጠቆሙት ዲፕሎማት ምንጮች “አሜሪካ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ነገር አላማረኝም” በሚል ለጊዜው ውሳኔዋን ለመቀልበስ ቃል እንደማትገባ ማስታወቋን አመልክተዋል።

የጉዞ ማዕቀቡ ነባር ኢንቨስተሮችን ያስበረገገ፣ አዲስ የሚመጡትን የገታ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ “የአገሪቱን ገጽታ ያበላሸ” እንደሆነ ለቶም ማሊኖውስኪ ቡድን ተገልጾለታል። እንደ መረጃ ሰዎቹ አገላለጽ አሁን ከቻይና፣ ከአረብ አገራትና ከአፍሪካ ባለሃብቶች ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነት እንደሚደረግ የሚጠቁሙ የዜና ዘገባዎችን ኢህአዴግ በስፋት የሚያሰራጨው ይኽው “ጠፋ” የተባለውን መልካም ገጽታ ለመመለስ ነው፤ የግልገል ጊቤ ሦስት ምረቃና ከዚያ ጋር አብሮ የተነገረው ፕሮፓጋንዳ የዚሁ ዘመቻ አካል አድርገው ይጠቅሱታል። ጥረቱ ቢደረግም የሚፈለገውን ለውጥ ባለማምጣቱ፣ ገንዘባቸውን እየያዙ የሚወጡ ባለሃብቶች በመበራከታቸው፣ አንዱ የምንዛሬ ምንጭ የሆነውን የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (ኤፍ.ዲ.አይ) እየጎዳው በመሆኑ፣ የቱሪዝም ፍሰቱ በመስተጓጎሉ አሜሪካ ማዕቀቡን እንድታነሳ መወትወት ግድ ሆኗል። ምክንያቱም የአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ አሜሪካውያንን ብቻ ሳይሆን መላውን አውሮጳና የሩቅ ምስራቅ አገራት በቀጥታ የሚተገብሩትና ለአገራቸው ሕዝብ እንደማስረጃ የሚያቀርቡት በመሆኑ ጭምር ነው፡፡

“ሰዎቹ” ይላሉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አሜሪካኖቹ ማለታቸው ነው “ሰዎቹ ተንኮል ሲያስቡ የት ጋር ሄደው ቆጣሪውን እንደሚነኩት ያውቃሉ” ሲሉ የአሜሪካኖቹን አካሄድ የተጠና እንደሆነ ያስረዳሉ። ቶም ማሊኖውስኪ “(የኢህአዴግ ሰዎች) ቃላቸውን ይጠብቃሉ ብለን እናምናለን” ማለታቸው፣ “ቁልፍ የፖለቲካ መሪዎችን መፍታትና ሚዲያውን ነጻ መልቀቀ ግድ ነው” ሲሉ በተለመደው “የነጮቹ ቋንቋ” መናገራቸው ቅድመ ሁኔታ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ ተናግረዋል። አያየዘውም አሜሪካ አሁን እየተኬደበት ያለው የችግር አፈታት ሂደት “አኩራፊዎችን ከማብዛት የዘለለ ውጤት እያመጣም የሚል አቋም አላት” ሲሉ ቶም ማሊኖውስኪ መናገራቸውን ያስታውሳሉ። እናም ኢህአዴግ ከገባበት ውስጣዊና ውጫዊ አጣብቂኝ ይወጣ ዘንድ የተነገረውን ማድረግ ግድ ነው።

“እንደ ወዳጅ መክረናል … ምክንያቱም … ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ቢፈጠር ሙሉ ምስራቅ አፍሪቃ ምን ሊከተል እንደሚችል ስለምናውቅ … “ በማለት አገሪቱን እሳት ላይ ተቀምጦ እንደሚንተከተክ ማሰሮ የመሰሉትና ማስሮው እንዳይገነፍል ብቸኛው አማራጭ ክዳኑን መክፈት እንደሆነ ያመለክቱት ቶም ማሊኖውስኪ፣ “ተስፋ አለን ይሰሙናል፣ መልካም ነገር እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት ኢኮኖሚው በድርብ አኻዝ እያደገ ነው፤ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል፤ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት የምትመች አገር ናት፤ ኤምባሲዎቻችን የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚም ነው የሚሠሩት፤ ወዘተ በማለት ህወሃት/ኢህአዴግ የውጭ ባለሃብቶችን ለማማለል የተጠቀመበት ሥልት አገሪቱ ውስጥ ከፈነዳው ነውጥ አኳያ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፡፡ በርካታ የንግድ ተቋማት፣ የእርሻ ቦታዎች፣ … ከወደሙ በኋላ ተመሳሳይ ኢንቨስትመንት ለማድረግ የሚመጡ ባለሃብቶች የመኖራቸው ጉዳይ አስተማማኝ አልሆነም፡፡ በነሐሴ ወር ከገንዘብ ሚኒስቴር በተሰጠው ዘገባ መሠረት የአገሪቱ ዕዳ 20.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡

በአሻባሪነት ስም የሚደረገው ማስፈራሪያ ጊዜው ያለፈበት ይመስላል፡፡ የህወሃትና የአልሸባብ ግንኙነት እንዳለ ሆኖ አሸባሪነትን ለመዋጋት በሚል አርባ ምንጭ የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ (ድሮን ቤዝ) ማቋቋም ደርሳ የነበረችው አሜሪካ ፕሮጀክቷን ያጠናቀቀች ይመስላል፡፡ “ሶማሊያ ውስጥ … በኮንዶም አንዋጋም!” እያለ የሚያምታታ መለስ የሌለው ህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮውን ብቻ ሳይሆን ከበረሃ ጀምሮ ሲያግዙት የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎችም” እያጣ ነው፡፡

የቶም ማሊኖውስኪ ንግግር አሜሪካ ለኢህአዴግ ጀርባዋን እየሰጠች ያለ ቢያስመስልም ንግግሩ ከኦባማ ሌጋሲ ጋር እንዲጠቀስ የተነገረም ሊሆን ይችላል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ “ዴሞክራሲያዊ” በማለት በሕዝብ የተሳለቁት ኦባማ በሥልጣን ዘመናቸው አንዳች ሳይፈጽሙ ቆይተው አሁን በስተመጨረሻው ይህንን ብለን ነበር ለማለት ለታሪካቸውና ለአስተዳደራቸው አስበው የፈጸሙትም ይሆናል፡፡ ሆኖም እንደ ማሊኖውስኪ ንግግር ኳሱ ያለው በአሜሪካ ዘንድ ሳይሆን በራሱ በህወሃት/ኢህአዴግ እጅ ነው፡፡ አሜሪካ ከጸጥታና ደኅንነት በስተቀር ከኢትዮጵያ ጋር ይህ ነው የሚባል የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት የሌላት ከመሆኑ አንጻር ጀርባዋን መስጠቷ በኢህአዴግ ላይ ጉዳቱን ያከርረዋል፡፡

ከአፍሪካ ጋር የተለካ አዲስ ሽርክና እንጀምራለን የሚል አቋም ለመውሰድ እየተዘጋጀ ያለው መጪው የትራምፕ አስተዳደር ለህወሃት/ኢህአዴግ የሚመች አይሆንም የሚለው ግምት ሰፋ ያለ ነው፡፡ የውትወታ (ሎቢ) ቢሮዎችን እዘጋለሁ እያሉ የሚዝቱት ትራምፕ ካቢኔያቸውን በወትዋቾች ድጋፍ እያቋቋሙ ያሉ ቢሆኑም የተናገሩትን የሚፈጽሙ ከሆነ በውትወታ በርካታ ተግባራትን በመፈጸም ለሚታወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ ብዙ በሮችን ሊያዘጋበት ይችላል፡፡ ከኦባማ ሥልጣን መልቀቅ ጋር በርካታ “ነጭ ወያኔዎችን” ለሚያጣው፤ በዚህ ከተቀጠለ “ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል” ለተባለለትና በግፍ ያሰራቸውን “የተሃድሶ ሠልጣኞች” እያለ የመፍታት ጭንቀት ውስጥ ለገባው ህወሃት/ኢህአዴግ “መጪው ጊዜ” ከውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጪም “ብሩህ” አይመስልም፡፡ (ፎቶ: በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. The people of Ethiopia, particularly the youth have suffering a lot with politically made outfit. Unemployment, living cost, arbitrary arrest, torture, banishment and intimidation, and all sorts of political vices have become rampant. I believe, no amount of rehabilitation would sooth the already broken heart of the citizens.
  The ball is on the field of the ruling party. I absolutely agree with that. The Ethiopian people always give peace and peaceful resolutions chance. We all wish, the ruling party take the initiative and the first step to accommodate every stake holders and work for sustainable peace.
  I do not believe like some do, that there is hate or enormity between societies. There is only sour and irreparably damaged relationship between the ruling party and citizens. The government should know, it won’t rule and govern like it used to. It is advisable to take smart dicision, so that everybody would be well and good.
  I believe, if there is good will there is always a way. Politics is an art — good and evil inherently imbedded. Humans, particularly politicians are calculating rational — capable of choosing the best possible solutions or way.
  A lot of damage have been done. Every citizen Is affected. Hereafter, peace is unimaginable, until some form of solution is achieved. Everything is a time bomb, that can explode anytime at any corner of the country. Maintaining power, peace and development is unthinkable.
  I am pretty sure, some honest individuals and groups within the ruling party would come out strong to pave the way to peaceful solutions where the Ethiopian people and the ruling party leadership, both winners.
  The ordinary citizens and party members have nothing to fear. They have been toiling to survive, with the new political set up, they will keep toiling. This time, I hope, with more freedom and rights.
  I wish, our Creator be with us.

 2. አንደ ወዳጄ እንዲህ አለኝ። ወያኔዎች አጋንንቶች ናቸው። ቀድሞ ሰይጣን አምላክ የለም ይለን ነበር። አሁን ደግሞ በወያኔ በኩል ወደ ሃገሪቱ የገባው ሰይጣን እኔም አምላክም የለም የሚል ነው በማለት ቀልድ በተቀላቀለው አባባሉ ፈገግ አረገኝ። ፓለቲከኞች እንደ ሃገራችን ቀበሮዎች ናቸው። በቀቢጸ ተስፋ በሥልጣን ላይ እንኖራለን ብለው የሚያምኑ። ቀበሮዋ የበሬ ቆለጥ ለምግቧ ይወድቅልኛል በማለት ቀኑን ሙሉ በሬውን ስትከተል ዋለች ይባላል። ትርፉዋ ልፋት ብቻ ነው። ጊዜ እንደ አሮጌ የመስፈሪያ ቁና አርቆ የወረወራቸው የፓለቲካ መዝባሪዎች ዛሬ ታሪካቸውን እሳት በልቶት መሳቂያ የሆኑ ስንቶች ናቸው? ወያኔ ግን የሚያስበውም የሚተነፍሰውም ያው ጫካ ውስጥ በተቃመሰው የአልባኒያ የፓለቲካ ዘይቤና በዘር በሽታ በመሆኑ ለመዳን የሚያስችለው አንዳችም መድሃኒት በዓለም ላይ የለም። የሚከተሉትን መረጃዎች እንመልከት።
  1. በነጮች የዘመን መስፈሪያ 1984-85 ላይ አእላይ የትግራይ ተወላጆች በወያኔና በደርግ የሰፈራ አጣቢቅኝ ውስጥ ይገባሉ። ወያኔም ነጮችንና አረቦችን አሳምኖ ቁጥራቸው የበዛ የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጆችን በሱዳን መሬት ያሰፍራል። በዚያም ስፍራ የስለላ መረቡን ስለዘረጋ አንድ ከአንዱ በድንኳኑ ውስጥ መነጋገርን ይከለክላል። በዚህ መካከል ትንሽ መዳሃኒት ያላት ፋርማሲ በሰፈራው ጣቢያ ውስት ትቋቋማለች። በቀን ከ 10 በላይ የሆነ ሰው ይሞታል፡ ረሃቡ፤ ስቃዮ በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በመደብደብ፤ እንጨት ለቀማ ሄደው እባብ የነደፋቸው፤ ወንድ የደፈራቸው፤ በግርግሩ የተሳሳተ መድሃኒት ተሰጧቸው የሞቱትን መቁጠር ያሽቸግራል። በዚህ መካከል አንድ ማለዳ ላይ ፋርማሲው (የመዳሂኒት ካዝናው) በሩ ተሰብሮ በውስጡ የነበሩት መድሃኒቶች ሁሉ መዘረፋቸው ይታወቃል። ከእንግሊዝ፤ ከአሜሪካ ከካናዳ ከጃፓን እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችም እጅግ ይናደዳሉ። በዚህ መካከል ገዳሪፍ ላይ የሆነ ጥቆማ ይመጣና ሲመረመር ዝርፊያው የተካሄደው በወያኔ እንደሆነ ይደረስበታል። ለዚህም ነው የትግራይ ህዝብ እጅና እግሩ የታሰረ ህዝብ ነው የምለው። ዛሬም ሆነ ትላንት ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ገዶት አያውቅም። የትግራይ ህዝብ በስሙ የሚነገድበት ህዝብ ነው!
  2. ስሙን ልጠቅሰው የማልፈልገው የሜዳ ታጋይ (የወያኔ አመራር) አለመግባባት ይፈጠርና ከሜዳ ይሰወራል። በጊዜው መጋባት ተፈቅዶ ስለነበር ሚስት ነበረው። በጊዜውም ነፍሰጡር ነበረች። ታጋየዋን ወያኔ የጠፋውን ለመበቀል መርዝ አብልቶ ይገድላታል። አዎን በድርጅት ሚስጥር ጥበቃ ስም በዙዎች አፋቸው ተለጎሞ ስንት ነገር ደብቀው ወደመቃበር የወረዱ፤ ዛሬም በዘራቸው ተሰልፈው ከእውነት በመራቅ የሚያላዝኑ እንዳሉ ህዝባችን ያውቃል።
  3. አዲስ አበባ – ወያኔና ሻቢያ ወዳጅነታቸው ከመጋሉ የተነሳ – ሞት የወሰዳቸው አቶ መለስ በሻብያ ታጣቂዎች ነበር የሚጠበቁት – ሳይታሰብ በአስመራ የብር እጥረት ይፈጠራል። በዚህ ወቅት ሻብያ ናቅፋ የተባለውን የራሱን ገንዘብ ገቢያ ላይ አላቀረበም ነበር። አቶ መለስም በአስቸኳይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከዋናው የኢትዮጵያ ባንክ ወጥቶ በአውሮጵላን ወደ አስመራ እንዲሄድ መመሪያ ይሰጣሉ። የጊዜው የባንክ ሃላፊ አይደረግም ይላሉ። ሰውየው ሰላም ባለበት ሃገር የሚኖሩ መስሎአቸው ቤታቸው ሲሄዱ የወያኔ የግድያ ስኳድ እቤታቸው ውስጥ ይጠብቃቸው ነበር በገመድ ሰቅለው ይገሏቸዋል። ሞቶ ተገኘም ተብሎ ዜናው ይናፈሳል። በሟች ስፍራ የወያኔ ሰው ይተካል። ገንዘቡም አስመራ ይላካል።
  4. ደራሲና የሻቢያው ሰላይ ተስፋዬ ገ/አብ እንዲህ ይለናል – ሰው እንኳን ነገን ተስፋ አድርጎ መኖር እንዲችል ወያኔ በህዝባችን ላይ የሚያደርገውንና ያደረገውን ሁሉንም መናገር ህሊናየ አይፈቅድልኝም። ከራሱ ቋንቋ ለመዋስ “ይሰቀጥጣል” በማለት ነው ሃሳቡን አሽጎ ያስቀመጠው። ባጠቃላይ ወያኔ አረመኔ ለመሆኑ የራሱ የድርጅት ሰዎች የሚሉትን መረዳት በቂ ነው። አሁን አሜሪካ ወያኔን እጅ እጅ አለኝ ማለቷ ለህዝባችን አስባ አይደለም። ለጥቁር ህዝብ ነጩ ህዝብ ገዶት አያውቅም። ይሁን እንጂ የአገልግሎት ዘመናቸው እየተመናመነ መምጣቱ ያሳስባቸዋል። ጠንከር ያለና ክፉኛ ወያኔን የሚፋለመው ድርጀት ቢኖር በስውር መርዳታቸውም አይቀሬ ነው። አሜሪካ ከአሸነፈው ወገን መሰለፉዋ ለራሱዋ ጥቅም እንጂ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነትና ብልጽግና አይደለም። ያው በፓናማ፤ በግብጽና በሌሎችም ሃገሮች እናየነው ወያኔም ሲወድቅ የሮም አወዳደቅ ነው የሚወድቀው። የሚጠጋበት ምንም ስፍራ አይኖርም። የዛሬዋ ቻይናም እጅና እግር አስራ ነው ለፍርድ የምታቀርባቸው። የሚገርመኝ ግን ይህ ነው። ከአለፈ ታሪክ አለመማራችን። የወያኔ አለቃ ምነው ወደብ አልባ ቀረን ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ይሂድ የግመል ማጠጫ ይሆናል ብለውን ነበር። እውነቱ ግን ግመሎች ጨዋማውን የቀይ ባህር ውሃ አይጠጡትም። ደግሞስ አሁን የአረብ አሰብ የአረብ የጦር ሰፈር ስትሆን ምን ይሉን ነበር? ይህን ሰው ነው አርቆ አሳቢና ታላቅ መሪ የሚለው ወያኔ። የጠባብ ብሄርተኛ መሪ፤ ለራስ አዳሪ፤ ዘረኛ፤ የአማራ ህዝቦች ጠላት አዎን አቶ መለስ ናቸው። ሌላው ግን ለመኖር የሚሰበክ ለጽድቅ የማያበቃ የህልም አለም ነው።

Speak Your Mind

*