የባለቅኔው ዝምታ

(አበራ ለማ)

የታዋቂው ባለቅኔና የሥነ ጽሑፍ ሰው የጋሼ ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) አስከሬን ኖቬምበር 30፤2014 በእስቶክሆልም ከተማ በብዙ መቶዎች በሚቆጠሩ ያገር ልጆች፣ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ጓደኞቹ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት በአቡነ ኤልያስ የሚመራ ፍትሃት የተደረለት ሲሆን፣ ቤተሰቦቹና ተጋባዥ እንግዶች የመሸኛ ንግግርና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥሞችን (Lament) ለለቀስተኞች አቅርበዋል፡፡

በዕለቱ የተገኙት ደራሲ አበራ ለማ ከተጋባዥ ተናጋሪዎችና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥም አቅራቢዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን “የባለቅኔው ዝምታ” በተሰኝ ግጥም ስንብታቸውን አሰምተዋል፡፡

ይህንኑ በማስመልከት አበራ ለማ የላኩልንን ግጥም እንዲሁም ፎቶ አቅርበናል፡፡

የባለቅኔው ዝምታ

መጣልሽ እምዬ፣ ገሞራው ልጅሽ

ቅኔ ባኩፋዳ፣ ስንቁን ይዞልሽ፤

መጣልሽ ከርታቴ፣ አገር ላገር ማስኖ

በሰንዱቅ ሳጥኑ፣ ጨምቶ ተከድኖ፤

(ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Speak Your Mind

*