“እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”

ታዬ ደንደኣ

እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው። የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረግክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረግክ። ራስህ የሰራኸውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች።

ለበርካታ ዓመታት በድራማ ከኦሮሞው ላይ ገንዘብ ሰበሰብህ። አሁን ግን ያን ጊዜ አልፏል፤ ድራማ አዘጋጅቶ የኦሮሞን ድጋፍ መጠየቅ ቀርቷል። ህዝቡ ያንተን አጀንዳ አውቋል። ሀበሻና ሚኒሊክ የአንተ ገበያ ናቸው። የኦሮሞ ድጋፍ ሲቀዘቅዝ ጠዋት ተነስተህ ሀበሻ እና ሚኒሊክ ብለህ ስድብ በመልቀቅ ገንዘብ ትሰበስባለህ። በዚህ መልክ የራስን ብሄር ታልባለህ። በቅርቡ በአሜሪካ የሠራኸው ሚስጥር አሁን ወጣ። ስድብና ተቃውሞ እንደምትወድ ተናግረህ ነበር። ለምን የሰላም መንገድ ትተህ ሀበሻ ባለበት ቦታ አድርሱኝ አልክ? የእነሱ ተቃውሞ ነው ገንዘብ የሚያስገኝልህ።

ዛሬም የተማርከውን ነው ያደረግከው። የሰንደቅ አላማ ዘመቻ አስመስለህ ግጭት ፈጠርህ። የተፈጠረውን ግጭት ልትጠቀምበት ፈለግህ። ዕቅድህ ለፓርቲህ ድጋፍ ማሰባሰብ ነው። ለዚህም ዱርዬ በማሰባሰብ የራስህን ፅ/ቤት በድንጋይ አስመታህ። አሁን ይቺን አጀንዳ ይዘህ ወደ ገበያ ትወጣለህ። ሀበሻ ጠልቶናል! የኛን እንቅስቃሴ ፈርቷል! አይናቸው ቀልቷል! ለዛ ነው ፅ/ቤታችንን የመቱት በማለት በOMN ትተነትናለህ ወይም ታስተነትናለህ። ይህ አሁን አይሆንም። ድርጊቱ በህግ እና በስርዓት ብቻ ይመራ። ከዚህ ውጪ ከጥያቄ አታመልጥም። ዘንድሮም እሾህ የተከለውን ሰው መውጋት አያቆምም!!

***

(ትርጉም፤ FastMereja)

Speak Your Mind

*