የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ

ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ የነበረው ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣኑ ተነስቷል።

አንደበቱ በቅጡ ያልተገራና ፍጹም የህወሓትን ዓላማ በአደባባይ በማስፈጸም የሚታወቀው ዘርዓይ፤ ከዚህ እንደፈለገ ከሚነዳው መ/ቤት መልቀቁ በሚዲያው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ ታላቅ አዎንታዊ እርምጃ ተወስዷል።

አንዳንድ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በላይ በቀለ፣ መሠረት አታላይ፣ ዮናስ ዲባባ፣ አስካለ በላይ፣ ካሳሁን ፈይሳ፣ እና ሌሎችም የሙያው ሰዎች በዚሁ የህወሓት ተጋዳላይ ትዕዛዝ ከሥራቸው እንዲለቁ መገደዳቸው ይታወቃል።

ዘርዓይ በሥልጣን በቆየባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የነበሩ ሲሆን በክልላዊ ነጻነት የሚንቀሳቀሱትን የአማራ ሚዲያና የኦሮሚያ ብሮድካስትን በመዝለፍ የሚታወቅ መሆኑን የዞን ፱ ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ ትዊት አድርጓል። የጋዜጠኛነት ወይም የጋዜጣ ማተም ፈቃድ ለማውጣት ቢሮው የሚሄዱ ሁሉ ከፍተኛ የሆነ የማንነት ምርመራ እንደሚካሄድባቸውና ፈቃድ እንደሚከለከሉ አጥናፍ ጨምሮ ጠቅሷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በተጻፈ ደብዳቤ ዘርዓይ አስገዶም ከቦታው ተነስቶ በምትኩ የደኢህዴኑ ሰሎሞን ተስፋዬ ተሹሟል። አዲሱ ተሿሚ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግሏል።

የሥርዓቱ ተሿሚ እንደመሆኑ ሰሎሞንም ብዙ ለውጥ ላያመጣ ይችላል ቢባልም የዘርዓይ መነሳት ግን ድርጅቱን በተወሰነ ነጻነት እንዲሠራ የሚያስችለውና በክልል የሚዲያ ሥራዎች ላይ የዘርዓይን በህወሓት የተቃኘ ተጽዕኖ እንዲነሳ የሚያደርግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም በተጨማሪ በዘርዓይ ዘመን ለጋዜጠኝነትና የጋዜጣ ኅትመት ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የሚደረገውን ከማንነት ጋር የተያያዘ አፈናና ክልከላ በማስቆም ለግሉ ፕሬስ አንጻራዊ ነጻነት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘርዓይ አስገዶም፤ ሃጫሉ ሁንዴሣ ቄሮ አራት ኪሎ ግባ በማለት በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበውን ዜማ አጥብቆ የተቃወመና “ጸረ ሕዝብ ነው” በማለት የኮነነ ነበር። ዘፈኑ በቀጥታ ስርጭት በኦሮሞያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) በመተላለፉ ኦቢኤንን በመኮነን የዛቻ ንግግር በማድረግ ለትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ጭፍን ወገነተኛነቱን በግልጽ የመሰከረ ነበር። የአማራ ሚዲያንም የቴዲ አፍሮ ዘፈን ላይ የሚታየው ኮከብ አልባው ሠንደቅ ዓላማ በስብሰባዎች ላይ ሲታይ ምንም ሳይሉ በማስተላለፋቸው ዘርዓይ ወቀሳ ማቅረቡ ይታወሳል።

በእነዚህና በሌሎች በርካታ በሚዲያው ላይ በሠራቸው የአፈና ተግባራት ዘርዓይ አስገዶም በአንዳንዶች ዘንድ የሚዲያው “እንቦጭ” ተብሎ ይጠራል። (ፎቶ፤ ዘርዓይ አስገዶም፤ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. Dawit Tesfaye says:

  Thanks God.
  የቆየ ከሚስቱ ይወልዳል፡፡ እስከ ግንቦት 30 ምን ተጨማሪ እንሰማ ይሆን?

 2. Mulugeta Andargie says:

  ተነቀለ? ቂቂቂ!!! ጨበርባሪ ወሬኛ ሁላ! መስሎሻል

 3. እስቲ ምን እንደምትሆኑ እናያለን! ጨበርባሪዎች! ወልቂጤዎች!

 4. ሙሉጌታ ሐጎስ ይገባናል ። አፍቅሮ ተጋሩ ምደር እንደጠበበቻችሁ።
  ግን ግን እነ ዘርዓይ አስገዶምን ተጋሩ ብቻ እንጅ የሚወዳው፣ መላው ኢትጵያዊያን ከተከዜ ወዲህ ያለው መላው ኤርትራዊ ከመረብ ወዲያ ያለው በሙሉ ነቀዝ ብሎ የእህል ጎተራዉን ሁሉ ይመርጋል እንጅ እህሉን የሚፈጀዉን አንበጣ ማን ዝም ብሎ ያያል..? አንበጣን በዲዲቲ ካላጠፉት እህል መፈጀቱን መች ያቆማል እና ሙሉጌታ ሐጐስ ?

 5. ውድ ጎልጉል፣
  የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ። ግሩም ርእስ ነው!
  ሌላኛው የወደድኩላችሁ፣ “ነፍጠኛ”ን ለወያኔ መጠቀማችሁ ነው።
  በርቱ

Leave a Reply to Yonas Cancel reply

*