ተሰማ ናደው

ለዛሬ የማስታውሳቸው በዚህ ምስል ላይ የሚታዩት የአደዋ ጀግና የአጤ ምንሊክ ታማኝ የጦር አዝማች አቤቶ ልጅ እያሱ ባውሮጳ አቆጣጠር1913 ዘውድ ሲጭኑ እንደራሴ ወይም የቅርብ አማካሪ በመሆን ያገለገሉት ራስ ተሰማ ናደው ናቸው ።

በተጨማሪ ራስ ተሰማ እቴጌ ጣይቱ ከምንሊክ ቤተ መንግስት ለቀው እንጦጦ ጋራ ላይ ካለው ዕልፍኝ ውስጥ ከቅጥር ግቢው እናዳይወጡ ታግደው እንዲቀመጡ ካዘዙት መኳንንቶች አንዱ ናቸው። ይህ ድርጊት በእቴጌ ጣይቱ ላይ የተፈጸመው እቴጌ ብልህ ስለነበሩ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ተባብረው ልጅ እያሱን ከጥልጣን ያወርዳሉ በሚል ፍራቻ ነበር።

ራስ ተሰማ በ1916 ዓም ላይ በራስ ተፈሪ እና ልጅ እያሱ መካከል በተደረገው የሰገሌው የዘውድ ሽኩቻ ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል። (ምንጭ: Eduardo Byrono ፌስቡክ ገጽ)

Speak Your Mind

*