ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!

 • ለተስፋዬ ዕድል መስጠት ሬዲዮ RTLM መሆን ነው

የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ፣ ከፍ ከፍ ሲል “የዘር ወባው” የሚነሳበት ተስፋዬ ገ/አብ አሜሪካ ገብቶ የሚያናግረው ሚዲያ በማጣቱ “በሚዲያ ረሃብ” እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በክፉም ይሁን በመልካም ከሚዲያ መገለል የማይወደው ተስፋዬ “ሻዕቢያን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ጽፌአለሁና አናግሩኝ” እያለ በዳያስፖራ ያሉትን ሚዲያ እየለመነ፣ በራቸውን እያንኳኳ መሆኑ ተነግሯል – በተለይ የተንቀሳቃሽ ምስልና (TV and YouTube) የሬዲዮን፡፡ ዛጎል እንደዘገበው ከሆነ እስካሁን ዕድሉን የሰጠው የለም፡፡

ተስፋዬ ከዚህ በፊት እየጻፈ የሚያወጣቸው መጣጥፎች እንደዱሮው ተነባቢነት ካጡ ሰነባብተዋል፡፡ የኦሮሞም ጽንፈኞችም እንደፈለጉ ሲጠቀሙበትና እሱም በተራው ሲጠቀምባቸው ቆይቶ አሁን ከእርሱ “የተሻሉ” አግኝተው ትተውታል፡፡ በርካታ እርሱን የሚተኩ በዘረኝነት የተከተቡ የኦሮሞ ጽንፈኞች (ያውም እንደ ተስፋዬ “ሰልባጅ” ሳይሆኑ ኦሪጂናል ዘረኞች ስለተገኙ)፤ ሚዲያውንም እስከሚበቃቸው ስለተቆጣጠሩትና እርሱ የሚመጻደቅበትን ኦሮሚኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ያደረጉ በመሆናቸው ተስፋዬ “አሮጌ ስልቻ” ሆኗል፡፡ ከዚህም አልፎ ከአማርኛ ጋር ጨምረው ተስፋዬ ሲናገርም ሆነ ሲነገር የሚነስረውን እንግሊዝኛ አቀላጥፈው የሚያንበለብሉ በመሆናቸው ባሁኑ ጊዜ የተስፋዬ ዋጋ የተመጠጠ ሸንኮራ ወይም ፊልተሩ የቀረ የተጨሰ ሲጋራ ሆኗል፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን ዘመን ተገልብጦ አሁን የሚዲያ ባለቤት ሲሆኑ “ዝምታቸውን” አስጩኾ “የጡት ጉማጅ” ሃውልት ባለቤት ያደረጋቸውን “ወዳጅ” መዘንጋታቸው ነው፡፡

ተስፋዬ ግን ሞራል የሌለው በመሆኑ የትም ቢጠራ፣ የትም ተናገር ቢባል፣ … ያደርገዋል፡፡ ዓላማው የውይይት አጀንዳ መሆን ነው፡፡ በተለይ ሰሞኑን በድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊነት አዲስ ቀለም አበጅቶ የአበባው ሕብረቀለማዊነት መታየት ስለጀመረ ይህንን ማፍረስ የተስፋዬ ተቀዳሚ ዓላማ እንደሚሆን የበፊት ታሪኩን መመልከት ብቻ በቂ ይሆናል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለተስፋዬ ዕድል ሰጥቶ ቃለምልልስ የሚያደርግለትን ሚዲያ የሩዋንዳውን ፍጅት እንዲቀጣጠል ካደረገው ሬዲዮ RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) ለይቶ እንደማያይ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለማስቀመጥ ይወዳል፡፡

በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይ) በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚዲያውን ኃይል በመጠቀም RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) በተሰኘው የሬዲዮ ማሰራጫ አማካኝነት የተነዛው የዘር ጥላቻ ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህንን ተግባር ሲፈጽሙና ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱ ያደረገውና ቱትሲዎችን “በረሮ” (“cockroaches”)  እያለ በመጥራት “እንዲገደሉ” በሬዲዮው አማካኝነት “ትዕዛዝ” ሲሰጥ የነበረው ፌሊሲዬን ካቡጋ (Félicien Kabuga) ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ካቡጋ እና የሬዲዮ ጣቢያው ልፈፋ ለ51ሺህ ሰዎች መገደል ቀጥተኛ ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ከተጨፈጨፉት ሰዎች ውስጥ 10በመቶ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው! መጽሐፎቹና መጣጥፎቹም RTLM ሬዲዮ ናቸው፡፡ ተስፋዬ በሚዲያ ረሃብ ጠውልጎ መሞት አለበት፡፡ ይልቅ የጻፋቸው መጽሐፎችና ያወጣቸው መጣጥፎች ለዜጎች መጨራረስ ምክንያት እንደሆኑ የራሱን ማስረጃዎች በመጥቀስ ለፍርድ የሚቀርብበት ሁኔታ ቢመቻች ነው ለአገርና ሕዝብ የሚበጀው፡፡ አሜሪካ ለዚህ ዓይነት ሕጋዊ አሠራር የተመቻቸች አገር ናት፤ በቅንጅት መንቀሳቀስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ምናልባትም ወደ አሜሪካ መምጣቱ ሳያውቀው በአንገቱ ላይ ገመዱን እያጠበቀ እንዳይሆን! የመናገር ነጻነት ማለት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን ማለት አይደለም!

ዛጎል ያወጣው ዜና እንዲህ ይነበባል፡፡

ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ – ተስፋዬም ተነሳ

ተስፋዬ ሲያትል ግብቶ የሚዲያ ረሃብተኛ ሆነ!!

የጋዜጠኛ ማስታወሻ የሚለውንና “የግል የሚለውን ማስታወሻ” ገጣጥሞ ለንባብ ካበቃ በኋላ ዲያስፖራው አንግሶት ነበር። በፓልቶክ፣ በሬዲዮ፣ በ“ቲቪ/ዩቲብ” … በተለያዩ ሚዲያ አክተር ሆኖ ሙገሳ ጠግቧል። “የቡርቃ ዝምታ” በሚለው የፍጅት አቀጣጣይ መጽሃፉ ጥርስ የነከሱበት ከጅምሩ ቢቃወሙትም የሚሰማቸው አልነበረም። በኢትዮጵያኖች ሚዲያ፣ ኢትዮጵያ ላይ መርዝ እየረጨ ሲጨበጭብለት ያበዱ፣ የተቃጥሉና የተሟገቱ ብዙ ብለው እንደነበርና የሃሳብ መለያየት እስከሚከሰት ድረስ ግጭት ተነስቶም ነበር።

በደጋፊዎቹና ከልብ በሚጠሉት መካከል ያለውን ፍትጊያ “ኦሮሞን” በመንተራስና ግንቦት ሰባትን በ“መደገፍ” ያለፈው ተስፋዬ ገብረአብ (ገብረ እባብ አንዳንዶች እንደሚጠሩት)፣ በስደት ከሚኖርበት ኔዘርላንድስ የወጣበት መረጃ ሊስተባበል በማይችል መልኩ ከሚዲያና እንዳሻው ከሚዘንጥበት ማህበራዊ ገጾች ገፍትሮ እንደወረወረው በጊዜው ብዙ ተብሎበታል። የአሁኑ አመጣጡ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ መሆኑ አነጋግሪ ሆኗል።

በተለይም ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር የሚያደርጋቸውን የጽሁፍ ምልልሶች ኮፒ በማደረግ የኔዘርላንዱ ነዋሪ ይፋ ካደረገው በኋላ፣ ካለፈው የቡርቃ ዝምታ መጽሃፉ ጋር ተያይዞ ሊከሰስ እንደሚገባው የሚጠይቁ ተነስተውበት ነበር። እነዚህን ሰዎች ጠቅሶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው፤ የቡርቃ ዝምታ ደግሞ የካቡጋ ሬዲዮ RTLM ነው” ብሏል። አያይዞም ያነጋገራቸውን ጠቅሶ “ሆላንዳዊው” ተስፋዬ እንደ ካቡጋ “ወደ አባት አገር” በመሄድ ከመሸሸጉ በፊት ውጤታማ ሥራ መሰራት ያለበት አሁን ነው ይላሉ” ሲል ዘግቦ “አክትቪስት ነን” ለሚሉት ሁሉ ህዝብን ለፍጅት በማነሳሳት ወንጀል እንዲከሰስ አሳስቦ ነበር። እንደተባለው ይሁን በሌላ ምክንያት ተስፋዬ አገሩ ገብቶ የኢንተርኔት ሱቅ በመክፈት ሲሰራ እንደነበር ከዚያው አካባቢ የመጡና የሚያውቁት ይናገራሉ። ተስፋዬ አስመራ እያለም ከሕገወጥ የሰው ዝውውር (human trafficking) ጋር በተያያዘ ታስሮ እንደነበርም ስለጉዳዩ የሚያውቁ አመልክተዋል።

ተስፋዬ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ ሲያትል ይገኛል። እዚያም ብዙ እንደሚቆይ ከመናገሩ ውጪ ከሻዕቢያ ጋር ስለመለያየቱ ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም አሁን እያሳተመ ያለው ታሪክ የሻቢያን “ምስጢር” የሚያጋልጥ እንደሆነ መናገሩን ዜናውን ያቀበሉን ጠቁመዋል። ጥሩ የመጻፍና የመፈጠር ችሎታ ያለውን ተስፋዬን ኮሎኔል ከማል ገልቹ “የተወለድኩባትንና ያደኩባትን አርሲን ከኔ በላይ የሚያውቅ ሆኗል” ሲሉ አስተያየት እንደሰጡበት አይዘነጋም። ተስፋዬ አሁን እያሳተመ ያለው መጽሃፍ እንዲተዋወቅለት የኢትዮጵያኖችን ሚዲያና ለመጠቀም ቢፈልግም እንደፈለገው ሊሳካለት እንዳልቻለ በዚሁ ጉዳይ ያወያያቸው ለዛጎል አመልክተዋል።

ኢሳትን ለማስታወቂያነት ቢመርጥም እንዳልተሳካለት የጠቆሙት ምንጮች፣ ኢሳት ተስፋዬን ቃለ ምልልስ አድርጎ የመጽሃፉን ማስታወቂያ ከሰራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሳበት ገሃድ በመሆኑ ሊሳካለት እንደማይችል ተናገረዋል። ሌሎች የሚዲያ ተቋማትንም ለማነጋገር የሞከረ ሲሆን አንዳንዶቹ ጥያቄውን አንቀበልም ባይሉም እንደወትሮው እጃቸውን እንዳልዘረጉለት ነው የተሰማው።

በሌላም በኩል ኦነግን ሻቢያ እንዳፈራረሰው ሁሉንም አብጠርጥሮ የተናገረውን ሰናይን ለማስተባበብል ሆን ተብሎ የተዘጋጀና የሻዕቢያን እውቅና ያገኘ መጽሃፍ እንደሆነ ግምት ያላቸውም አሉ። ተስፋዬ ሻዕቢያን ሙሉ በሙሉ የሚያጋልጥ መጽሃፍ ለንባብ ካበቃ፣ የኤርትራን ምድር እንደማይረግጥ ግልጽ በመሆኑ “እመለሳለሁ” ማለቱ በመጽሃፉ ላይ ከወዲሁ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ተስፋዬን በወጉ የሚረዱት እንዳሉት “አሁን ወቅቱ ኢትዮጵያዊነት የተነቃቃበት በመሆኑ ሃሳብ ለማስቀየርና ሌላ አጀንዳ ለማስቀመጥ ነው” ባይ ናቸው። በዚሁ መነሻ የሚዲያ ረሃቡን ማጠናከርና ፊት መንሳት አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል።

ሊነበብ የሚገባው፤ “ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ” – የቡርቃ ዝምታ፤ “RTLM” ሬዲዮ!” በሚል ርዕስ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ያዘጋጀውን ሃተታ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Comments

 1. ውድ ጎልጉል፣ ተስፋዬ ሁሌም ምሥጢር እንዳጋለጠ ነው። ችግሩ ሁሌም ምሥጢር የሚያወጣው ከነፈሰበት በኋላ ነው። እዚህ ጠምዘዝ እዚያ ቆልመም ያደርግና ይኸውላችሁ ይለናል። ወደ ኋላ ሄዶ መጽሐፍቱን ላየ “አወይ መታለል!” ብሎ ይቆጫል። ያን ጊዜ የህወሓትን ነው፤ ዛሬ ተስፋ የገባልን የሻቢያን ምሥጢር! እስቲ አንዴ ደግሞ ላተራመስ ብሎ ነዋ።

 2. Kill him and let him get rest from his consciencial charges and nightmares.

 3. Dear Golgul,
  I just came across a comment I had made to your site. Tesfaye’s relocation to Seattle area makes more sense than I had anticipated. http://www.goolgule.com/tesfaye-gebreab-and-kabuga/

  Alem says:
  October 6, 2013 03:32 pm at 3:32 pm
  I was thinking along the line of what Washeraw is saying. In fact, Tesfaye and Dr. Birhanu are for some reason very close [both born in Debre Zeit and both recommended each other’s books and share a book publishing website]. What is even more surprising is that the views the two of them have on Eritrea is identical. Would Dr. Birhanu publicly distance himself from Tesfaye? That is the question. Another point is that all Ethiopia-oriented sites should not allow space to Tesfaye’s divisive ideas. You may also check if and what Tesfaye, Ethiopian Review, Ethiopian National Council, G-7, etc have in common.

 4. የህወሃቱን ሰላይ ሰናይን አንደ ደህና ሰው አድርጋቹህ ማቅረባቹህ ገርሞኛል።ሰናይ በኢትዮጵያውያን ትግል ላይ የፈፀመውን ደባ አታቁትም ወይስ ዝምድናቹህ ይይዛቹሀል

 5. ተፈራ ድንበሩ says:

  በተስፋዬ ገብረኣብ ድርሰት የሚመሩ፤ ከዚህ በመነሣት የዘር ጥላቻ ያለው ጎታች አስተሳሰብን ያዘለ እና ለማኅበራዊ እኩልነትና ዲሞክራሲያዊ መርህ ጠንቅ የሆነ የእባብ ትምህርት ሀውልት በመሥራት በራሳቸው መመራት የማይችሉ እንሰሳት እንጂ እንኳን የተማሩ አእምሮ ያላቸው ስዎችም ሊባሉ አይችሉም፡፡
  ተስፋዬ ምን ያድርግ የሚነዳ በግ ሲያገኝ፡፡

 6. ተፈራ ድንበሩ says:

  በተስፋዬ ገብረኣብ ድርሰት የሚመሩ፤ ከዚህ በመነሣት የዘር ጥላቻ ያለው ጎታች አስተሳሰብን ያዘለ እና ለማኅበራዊ እኩልነትና ዲሞክራሲያዊ መርህ ጠንቅ የሆነ የእባብ ትምህርት ሀውልት በመሥራት በራሳቸው መመራት የማይችሉ እንሰሳት እንጂ እንኳን የተማሩ አእምሮ ያላቸው ስዎችም ሊባሉ አይችሉም፡፡
  ተስፋዬ ምን ያድርግ የሚነዳ በግ ሲያገኝ፡፡
  ሐውልት ይሠራ ቢባል ክራያ ጀምሮ ቅላማውን ወሎ ይዞ እስከ ጅሌ ድረስ ሲሰለብ ለኖረው ሕዝብ ሐውልት ይሠራ ቢባል ከመቶ የሚብልጡ ሀውልቶች ይሠሩ ነበር፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለአገሩ ሰው ለፋሽት ኢጣሊያ ዜጎች እንኳ የዘር ቂም የማይዝ ይቅርታ ማድረግን የሚያውቅ ሃይማኖተኛና ሆደሰፊ ሕዝብ ነው፡፡

 7. Micael D.Solomon says:

  Ethiopians just begging for your freedom by X symbol it never kill Beggars Agame.What is wrong about Tesfaye Gebrab he open your eyes to struggle for your freedom.

 8. Ethiopian News Papers, and any medias like TV, Radios please don’t let Tesfaye spread his poison again on the Ethiopian Unity. Now I am sure that he may be the messenger of Oromo extremists lead by jihadist Jawar Mohammed to disdain the work of our Galant Ethiopian Teddy Kassahun. After the song called “Ethiopia” came into the air by Teddy, all extremists of Oromos, Tigreans, and Shaebia are Frustrated. Because it’s the renaissance of Ethiopia and Ethiopians that was undermined by Weyane fascists for twenty-five years. True Ethiopians let’s march behind Teddy and fight these mercenaries of our Motherland Ethiopia. The Oromo extremists are burned down our heroes, AtseTeodrose Atse Menelik, Atse Haile Selassie who awaits the sovereignty and dignity of Ethiopia and our hero Teddy Afro pictures that we see on facebook and youtube. I understand that they can’t represent the innocent Ethiopian Oromos like Mesfin Faisa, Biftu and others. But these who called ‘Qeros” lead by jihadist Jawar Mohammed, Weyane gangs, and Shaebia are first enemies of our Sovereign Country Ethiopia and Ethiopians. So, let Unite more than ever. God bless Ethiopia.

 9. እንደ እዉነቱ ከሆነ ተስፋዬ ገ/አብ ባመለካከት የተጎዳ መሀይም በመሆኑ እሱና የ ታብሎይድ ስራዉ ቶሎ እንደሚደርቁ አሳስበን ነበር፡ ግለሰቡ ከምንም በላይ መሀይምነቱ ጠቅሞታል ከመጻፉና ከመናገሩ በስተቀር የእረሱ ጽሁፍና ንግግር ምን እንደሚያመጣ መገመት አይችልም የእዉቀት ክፍተት ስላለበትም ሃሳብን በተለያየ መልኩ ይከብደዋል በአናሳ ስራአዉ በእጅጉ ይኮራል ለማንኛዉም ሊታዘብለት የሚገባ ፍጥረት ነዉ።

 10. ስለ ተስፋዬ የኔዘርላንዱ የጻፈውን ጉግል ሳደርግ ይህን ሊንክ አገኘሁና ላካፍላችሁ።http://ethiopianchurch.org/en/books_reviews/198-%E1%88%B5%E1%8B%B0%E1%89%B0%E1%8A%9B%E1%8B%8D%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%88%8B%E1%8A%A9.html

 11. ስለ ተሰፋዬ ቀድመን ተፍተነዋል እኛ ስንቃወም ነፍጠኞች ተብለናል ፣ የለፈውን መፅሃፎቹን በይፋ ሲያስተዋውቁለት የነበሩት እንደነ አበበ ያሉት የግንቦት ሰባት ዐመራሮች አሁንም መጽሃፍ ቢያወጣ እንደሚያስተዋዉቁለት አልጠራጠርም ፣ ተስፋዬን የመሰሉ አሁንም የሚጨበጨብላቸው ሞልተዋልና እያንዳንዳቸው እንደዚህ ፀረ ኢትዮጵያ የእንግዴ ልጅ ሴራቸው እስከሚጋለጥ ድረስ ወደፊትም ስለሚኖሩ መመርመር ፣መጠየቅ ፣አሁንም መጠየቅ የሁሉም ሃላፊነት ይሆናል ።

 12. let him rust. Let him grow fungus. we now his evil missions and we will revenge him.

Speak Your Mind

*