በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በልዩ ይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቅዳሜ እለት መግለፁን ተከትሎ ከትንናት ሰኞ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መፈታታቸውን ሲጠብቁ ቆይተው ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ተለቀዋል። በቤተሰባቸው ቤት ከቅዳሜ ጀምረው ሲጠባበቁ ለነበሩት ወዳጆቻቸው ባደረጉት ንግግር አቶ አንዳርጋቸው ''እኔ ተፈትቻለሁ ኢትዮጵያ ግን ያልተፈቱ ብዙ ችግሮች አሉባት'' ብለዋል። ከእስር ተፈተው ቤታቸው ሲደርሱ የተመለከቱት ነገር ያልጠበቁት እንደሆነ የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው። "ምንም መረጃ ባይኖረኝም ኢትዮጵያዊያን እኔን ለማስፈታት ጥረት እንደሚያደርጉ ይሰማኝ ነበር" ብለዋል። ለዚህ ቀን መምጣት ለደከሙ ለሁሉም ሰዎች ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ገብቶበት ካለው አስቸጋሪ ሁኔታ አንፃር፤ እንዲህ … [Read more...] about “ፍቱኝ ብዬ አልጠይቃችሁም አብሬያችሁ የሰራሁበትን ጊዜ እንደውለታ ቆጥራችሁ የሞት ፍርዱን ተግባራዊ አድርጉ”