ታሪክ የወረሰ ትውልድ፣ ያልተወለዱ ህልሞችና የማዋለጃው መንገድ

የዛሬ 150 ዓመት በሕይወት ብንኖር ኑሮ ብዙዎቻችን ምንአልባት ሁላችንም በዘመኑ ከኖሩት አባቶቻችን ጋር በአንድ የአስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ ምህዋር ላይ እንደምንተም እገምታለሁ። የነበረውን የህይወት ከባቢ እንደዘላለማዊና የማይቀየር እውነት በመቁጠር እንደምንመላለስ አስባለሁ። ፈጣሪ በማይቋረጠው የዘመናት ጐዳና ላይ በየዘመኑ የሚያስነሳቸው ታላላቆች ግን ጨለማ ባጠቆረው ሰማይ ላይ እንደሚበር አብሪ ኮከብ ለሁሉም እንዲታዩ ሆነው ይምዘገዘጋሉ። ኢትዮጵያ በታሪክ ደርሳናቷ ላይ የሚንቦገቦጉ፣ […]

Read More...

የጠ/ሚ/ር አብይን የለውጥ መንገድ ለመርዳት ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

የሚፈለገው ለውጥ ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈለገውን አስተዳዳሪዎቹንና የአስተዳደር ሥርዓትን በነፃነትና በዴሞክራሲ መንገድ ሊመርጥ የሚችልበትን ሥርዓት መመሥረት ነው። ህወሃት የዘረፋ ሥርዓቱን ለማቀላጠፍ እንዲመቸው ዘንድ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መመሪያ በማድረግ ፖለቲካውን የማጭበርበሪያ፣ ኢኮኖሚውን የመዝረፊያ፤ ዳኝነትን የመበቀያ፣ ደህነነትን የማሸበሪያና መከላከያን የማጥቂያ መዋቅሮች አድርጎ ለሃያ ሰባት አመት በኢትዮጵያ ሕዝብና በአገር ላይ ከባድ ግፍና መከራ እየፈፀመ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጀመሪያ […]

Read More...

ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!

ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ጽ/ቤት አላፊ በነበሩበት ወቅት ኦህዴድ ሁሉንም ሰላም ወዳድ ዜጋን ያስደሰተ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ላሉ ተቃዋሚዎች አቅርቦ ነበር። ይህ ጥሪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ  የቀረበ በመሆኑ አንዳንድ በኦሮሞ ስም የሚታገሉ በውጪም  በውስጥም ያሉ ተቃዋሚዎች በደስታ የተቀበሉት ነበር። ነገር ግን ይህ የኦህዴድ ጥሪ ምንም ያህል ለሀገሪቱ ሰላም  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም ያለ […]

Read More...

ቋንቋን በቋንቋ

ስለ ቋንቋ የተለያዩ እይታዎች መኖራቸው አዲስ አይደለም። የሚገርመው ይልቅ፣ ብዙዎች እንደ ሹምና አቡን ትእዛዝ ሲሰጣጡ ማየት ነው። ትእዛዙን ማን፣ እንዴት ይፈጽም? እይታዎችን ማቀራረብና መተግበርስ ይቻላል? መቸ በምን ቅደም ተከተል? ወዘተ። ይህን ያሰቡበት ቢኖሩ ድምጻቸው አልተሰማም። የራስን አጉልቶ፣ የሌላኛውን ማድበስበስ የተለመደ በመሆኑ፣ የጽሑፌ ይዘት ለያንዳንዱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ የተዘነጉ ጥቃቅን አሳቦችን ማነጋገር ይሆናል። ቋንቋ ቢያንስ ሀ/ […]

Read More...

የአማራ ብሔረተኝነት ለስር ነቀል ለውጥ መሰረት፣ ለኢትዮጵያም መዳኛ መድሃኒት ነው

የአማራን ህዝብ በቃላት መሸንገል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል። የህዝቡ ንቃተ ህሊናው በስልጣን ላይ ከሚገኙት ከፓለቲከኞቹ ቀድሞ ሄዷል። ወጣቱ የነብር ጣቱ – እሳት ትውልድ ሆኗል። ገና ከመነሻው ወያኔ/ትህነግ በ1967 ዓ.ም ባፀደቀው በማኒፌስቶው ላይ አማራ ጠላቴ ነው በማለት የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ የትግራይን ሪፕብሊክ እመሰርታለሁ፣ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ ሰላም አሳጠዋለሁ ብሎ ሸፈተ። በርሃ ሳለ በአማራው ተወላጅ ላይ ከፍተኛ በደልና ወንጀል […]

Read More...

የዶ/ር አብይ አህመድ አዋላጅነት ጉዳይ

ቃሉ የሕዝብ ነው። ቃሉንም በተግባር የሚተረጉመው ሕዝብ ነው። የወንዝ ውሃ ሽቅብ እንደማይፈስ ሁሉ፥ ይህም ቃል ወደ ተግባር ሳይቀየር ይቀለበሳል ብሎ መጠበቅ ተገቢ አይደለም። ይልቁንስ ይህን ቃል ለመተግበር የዶ/ር አብይ ድርሻ ምንድነው ብሎ አውቆ በዚያው ሚዛን ብቻ እርሳቸውን መመዘን ያስፈልገናል። ለሕዝብ ታማኝ ባይሆኑ፥ እሳቸው ከታሪካዊነት ይጎድላሉ እንጂ የሕዝብ ቃል ዕውን መሆኑ አይቀሬ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ […]

Read More...

የጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ራእይ

እንደ መግቢያ ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ስለዶ/ር አብይ ያለኝ የጠለቀ እውቀት ወይም ከነበሩበትና ከተነሱበት ፓርቲና ፓርቲው ከሚያራምደው የፖለቲካ አመለካከት ጋር ያለኝ ጠብ ወይም ዝምድና አይደለም። ይልቁንም እንደ አንድሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ ባለው የህወሃት የበላይነትን የተከተለ ፍጹም ዘረኛ ጉዞ ሄደን ሄደን የደረስንበት ደረጃ በጣም አሳሳቢ መሆኑን በመመልከት ነው። በዘረኛው የወያኔ ከሩብ ምእተ አመት የዘለለ የጥፋት ጉዞ ውስጥ ከተጓዙና […]

Read More...

HR 128 መጽደቅ ለመሰረታዊ የመብት ትግላችን ታላቅ ድጋፍ ነው

ሸንጎ ህጉን ይደግፋል፤ ለተፈጻሚነቱም ተግቶ ይፋለማል HR 128 ተብሎ የሚታወቀው ባሜሪካ ኮንግረስ (ፓርላማ) ውስጥ ለውሳኔ ቀርቦ የነበረው በኢትዮጵያ መንግስት የመብት አያያዝ ላይ ያተኮረ የህግረቂቅ እነሆ ትናንት መጽደቁ ተነገረ። በውጭ አገር ያሉ የሰብዓዊ መበት ተከራካሪዎችና የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ይህ የህግ ረቂቅ እንዲጸድቅና በስራ ላይ እንዲውል ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያድርጉ ቆይተዋል። ሸንጎ ለዚህ ስኬት ታጥቀው ለታገሉ ሃይሎች […]

Read More...

አምቦ ትናንትና ዛሬ!

አምቦ ስሟ ሲጠራ የብዙዎቻችን ልብ በሃሴት እንደሚሞላ ሁሉ ወያኔዎችና አሽቃባጮቻቸው አጥንታቸው ድረስ የሚዘልቅ ብርድ እንደሚሰማቸው ግልፅ ነው። ያች ምድር የብዙ ጀግኖች መፈጠርያ ናት። ጣልያንን ብርክ ያስያዙ ጀግኖቿን ታሪክ ሲያስታውሳቸው ቢኖርም ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው የአባቶቻቸውን ጋሻ አንስተው የሃገር ጠላት የሆነን ስርዓት በመፋለም ለሌላውም አንቂና አበረታች ሆነው እነሆ እነሱም ታሪክ ሠሩ። አምቦዎች ወያኔን መፋለም የጀመሩት ገና ከመጀመርያው […]

Read More...

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሁን!

እነሆ ሰንበት ነበረ። ምዕመኑ በሚኖርበት ከተማ በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን እንዳለፉት አያሌ ሰንበቶች ሁሉ ባለፈው ሰንበትም ተገኝቷል። ቃሉን ሊሰማ፤ ስለ ቃሉም ለመኖር ብርታትን ሊያገኝ፤ ስለራሱና ስለቤተሰቦቹ፤ ስለ ህዝቦቹና ስለ ሀገሩም ሊፀልይ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ አንስቶ ሊለምን። ማረን ለማለት። እግዚኦታም ለማቅረብ። ከትጉሁና ትሁቱ ካህንም ቃለ ህይወት ሊሰማ። ቃለ ህይወትንም ሊማር። እነሆም ካህኑ ቅዳሴውንና […]

Read More...