የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት … [Read more...] about ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
midroc
በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል። የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ … [Read more...] about በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው። የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት … [Read more...] about ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!
ከሳምንታት በፊት የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ? በሚል ርዕር ላቀረብነው ጽሑፍ የድረገጻችን አንባቢ አሥራደው የሚከተለውን በግጥም የተከሸነ መልዕክት ልከውልናል፡፡ ተናገር መጋዶ ተናገር ሻኪሶ፤ ወርቅ ወዴት ተጋዘ ላንተ አፈሩ ደርሶ፤ ተናገር ሃዲማ ደግሞም ኡላኡሎ፤ እነማን ዘረፉት የወርቁን አሎሎ?! የወርቁን ቡችላ የለገ ደንቢውን፤ ደብዛውን ንገሩን የደረሰበትን?! እነማን ዘረፉት ? ማንስ ከበረበት?! እነማን ተዝናኑ? ማንስ ጨፈረበት?! ድሃ በደከመ ድሃ በሞተበት፤ ጦሙን እንደዋለ አፈር ተንዶበት:: አካፋና ዶማ ይዘው ሳይቆፍሩ፤ ጨለማ መግፈፊያ ሻማ ሳያበሩ፤ ጠብ ሳይል ላባቸው ባቋራጭ ከበሩ፡ ያገር አንጡራ ሃብት እየመዘበሩ:: በገዛ መሬቱ በተወለደበት፤ ዕትብቱ ተቆርጦ ለተቀበረበት፤ ለወርቁ ባለቤት ምንም ሳይሰሩለት … [Read more...] about የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!