የኦጋዴን ጉዳይ ሲነሳ ኢህአዴግ ይደነግጣል። ስለ ኦጋዴን አንዳችም ጉዳይ እንዲነሳበት አይፈልግም። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ በኦጋዴን ተፈጽሟል ያለውን ይፋ ሲያደርግ ኢህአዴግ በተለዩት መሪው፣ በህዝብ ግንኙነቱና እንግሊዝ አገር ባሉት አምባሳደሩ በኩል የማስተባበያ ዘመቻ ከፍቶ ነበር። በኬንያ ስደት ጣቢያ የሚገኙትን የክልሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረው የቢቢሲው መርማሪ ጋዜጠኛ ሪፖርት ብቻ ሳይሆን ሂውማን ራይትስ ዎችም የከረረ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከአገር በቀል የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መካከል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም በተመሳሳይ የኦጋዴንን አጀንዳ በማንሳት ጥሪ በማስተላለፍ ቅድሚያ እንደነበረው መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢህአዴግ በሃሰት ላይ የተመረኮዘ መረጃ በማዘጋጀት የሚመራውን ህዝብና የዓለም ህብረተሰብን እንደሚያወናብድ የሚያጋልጡ መረጃዎች በየጊዜው ይፋ ይሆናሉ። … [Read more...] about “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!
Middle Column
ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አወጪ ግንባር /ኦብነግ/ እና ኢህአዴግ ጀምረው የነበሩት ድርድር መጨናገፉ ታወቀ። ድርድሩ የተጨናገፈው በኢህአዴግ በኩል በቀረበ ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል። መግለጫው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስለተደረገው ንግግር በዝርዝር ሳያብራራ ህዝበ ውሳኔን በመፍትሄነት አስቀምጧል። 74 ንጹሃንን የገደሉት የኦብነግ ሰዎች ጉዳይ በድርድሩ ስለመካተቱ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። ኦብነግ በድረገጹ ኦክቶበር 17 ቀን 2012 በይፋ እንዳስታወቀው የሰላም ድርድሩ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ለኬኒያ መንግስት ባቀረበው የአሸማግሉኝ ጥያቄ መሰረት ነበር። በዚሁ ጥያቄ መሰረት የኬንያ መንግስት አሸማጋዮች ለግንባሩ አመራሮች ጥያቄውን አቅርቦ ቀና ምላሽ በማግኘቱ የመጀመሪያ ደረጃ ንግግር ተደርጎ ነበር። የግንባሩ አመራሮች በቀናነት የድርድር ሃሳቡን ተቀብለው እንደነበር … [Read more...] about ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!
ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
በማናቸውም የአገሪቱ ባለስልጣናትና ተቋማት ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ይፋ የማያደርጉት የአገር ውስጥ የጫት ፍጆታና ገቢ በውስጡ ከፍተኛ ዝርፊያ ይከናወንበታል። ከዝርፊያው ጋር በተያያዘ አቶ መለስን ጨምሮ ከፍተኛ ሹማምንትና ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቅድሚያ ስማቸው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የጎልጉል የኦህዴድ ምንጮች የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትርና የንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒስትሩ በጫት ንግድ ዙሪያ የሚጫወቱትን ሚና አጋልጠዋል። ያገኘነውን መረጃ ለንባብ ያመች ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። የጫት ንግድ ዝምድና - ወ/ሮ ሱራ በደርግ የአገዛዝ ዘመን ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት መደረግ የጀመረው ጫት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወያኔ አባላትን ቀልብ አልሳበም ነበር። ባለስልጣናቱና የቀድሞው ታጋዮች ጫት ተጠቃሚ ስላልነበሩ ስለ ጫት ንግድና ከፍተኛ ፍጆታ እንዳለው መረጃው … [Read more...] about ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!
ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም። ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት … [Read more...] about ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!
አዜብ መስፍን ፈርተዋል!!
መለስ የሚያቆላምጧቸው ወ/ሮ አዜብ ለመቀማጠልና ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤተመንግሥቱን “አልለቅም” ማለታቸውን የጎልጉል ምንጮች አረጋገጡ። የአዲስ አበባ መረጃ አቀባዮቻችን እንደሚሉት ከሆነ የቀድሞዋ “ቀዳማዊት እመቤት” ሶስት ቪላዎች እንዲያማርጡ ቢለመኑም አሻፈረኝ በማለት ባነሱት የደኅንነት ጥያቄ ገፍተውበታል። ከህወሓት መከፈል በኋላ አቶ መለስ ህወሓትን በመዳፋቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ገንነው የወጡት ወ/ሮ አዜብ የተባረሩት፣ የተባረሩት ደጋፊዎችና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ኢህአዴግ ውስጥ ጥርስ የነከሱባቸው ይበረክታሉ። የሥልጣን እርከን በመጣስ ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በተጨማሪ ለሚያካሂዱት የንግድ ስራ ሲሉ መመሪያ በመስጠት፣ የማይፈልጉትንና አልታዘዝ የሚሉዋቸውን ባለሥልጣናት በማስገደድ፣ በተለይም ተወላጅ ሳይሆኑ በህወሓት አመራሮች ላይ ሲያሳዩ … [Read more...] about አዜብ መስፍን ፈርተዋል!!
በለገጣፎ ገሃነምና ገነት አየሁ!
“የኦሮሞ እንግዴ ልጅ” በሚል ስያሜ የሚጠራው ኦህዴድ በ1997 መስቀለኛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጥያቄውን ያቀረቡት አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ነበሩ። ጥያቄው የቀረበው አዳማ /ናዝሬት/ ቀበሌ 11 አዳራሽ ውስጥ ነበር። ተጠያቂው የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ሲሆኑ ስብሰባው የተጠራው “ለምን አልመረጣችሁንም” በሚል ኦህዴድ ከህዝብ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ታስቦ ነበር። “ኦነግ ኦሮሞ ነው። እናንተም ኦሮሞ ከሆናችሁ ለምን አንድ አትሆኑም? እናንተ አንድ ብትሆኑ ልጆቻችን አይታሰሩም፣ አይገረፉም፣ አይሰቀሉም፣ የደረሱበት እየጠፋ ሃዘን አንቀመጥም፣ ኦሮሞ እስከመቼ ይታሰራል?” የሚል ጥያቄ ያቀረቡት አባት ንግግራቸውን መጨረስ አልቻሉም ቤቱ በጭብጨባ ተናወጠ። “በኔ ዘመን የኦሮሞ ልጆች እንዳይታሰሩ አድርጌያለሁ። በድሬዳዋና በቦረና በኩል የገቡትን ኦነጎች … [Read more...] about በለገጣፎ ገሃነምና ገነት አየሁ!
ኦህዴድ በ“መደብ ትግል” መተላለቅ ጀመረ!
በኦህዴድና በህወሓት መካከል የነገሰው ልዩነት ይፋ የወጣው ዛሬ አይደለም። አርሲ ላይ ማዕከል አድርጎ የተደራጀውን የጁነዲንን ኦህዴድ አባዱላ ሙሉ በሙሉ ከናዱት በኋላ ከፈጣጠሩ ጀምሮ ሰንካ ያልተለየው ራሱ ኦህዴድ ውስጥ ውስጡን ሁለት ቦታ ተገምሶ ቆይቷል። በዘመነ “ህንፍሽፍሽ” ህወሓት ለሁለት በተሰነጠቀበት ወቅት “በህወሓት የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት መግለጫ አናወጣም” በማለታቸው ከድርጅትና ከሃላፊነታቸው ተባርረው በነበሩት ኩማ ደመቅሳ ጠቋሚነት ጨፌ ኦሮሚያ አዳራሽ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሆነው በ1997 ዓም የተመረጡት አባዱላ ገመዳ ሥልጣን በያዙ ማግስት የጁነዲንን “አርሲ ተኮር” ካቢኔ ሲንዱት ጁነዲንና ደጋፊዎቻቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።ጁነዲን ስልጣን ባስረከቡ በደቂዎች ውስጥ ከጋዜጠኛ ቀርቦላቸው ለነበረ ጥያቄ “ከስልጣን እንደምወርድ ከሁለት … [Read more...] about ኦህዴድ በ“መደብ ትግል” መተላለቅ ጀመረ!
የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!
እ.አ.አ በ1997 በጨረታ ወደ ግል ንብረትነት ተዛወረ የተባለው የኢትዮጵያውያን ሀብት የተሸጠው 172 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ሽያጩ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ሽያጩን ተከትሎ በርካቶች አርረዋል፤ ተቃጥለዋል። “ዋይ ዋይ ወርቃችን” ብለው አንብተዋል። ህዝብ የፈለገውን ቢል ደንታ የሚሰጠው አካል ስለሌለ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ እጅ በአዋጅ ተነጠቀ። ሽያጩን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን አሊ ሲሆኑ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ አሰፋ አብርሃ የኤጀንሲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ። ሁለቱም ባለስልጣናት ዛሬ ሃላፊነት ላይ የሉም። ስለ እውነትና ስለ አገር ሲሉ የሚያውቁትን ለመተንፈስ እስከዛሬ ቢጠበቁም ያሉት ነገር የለም። ሃሰን አሊ ሲኮበልሉ፣ አቶ አሰፋ አብርሃ ከወንድማቸው ጋር … [Read more...] about የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!
ኦባንግ ለሃይለማርያም በግል ደብዳቤ ላኩ!
ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው እውነተኛ “ትራንስፎርሜሽን” ከሁከት ይልቅ ውይይት፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፣ ከብቀላ ይልቅ ይቅርታ መሆኑን በማስገንዘብ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በግል ደብዳቤ መላኩን አስታወቀ፡፡ ንቅናቄው በደብዳቤው መልካም ተግባር በመፈጸም በትውልድ ሁሉ “ታላቁና ደጉ መሪ” እንዲባሉ ምኞቱን ገልጿል። ንቅናቄው ለጻፈላቸው ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ይሰጣሉ የሚል ሙሉ እምነት እንዳለው ለጎልጉል በእርግጠኝነት ተናግሯል። ኢትዮጵያ የሁሉም አገር እንደሆነች በማስታወቅ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር ፊርማ የተላከው ደብዳቤ አቶ መለስ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥሪ ሲቀርብላቸው ባለመቀበል ለህዝብ መንገድ ንቀት ሲያሳዩ ማለፋቸውን ያስታውሳል። የአንድ ጎሣ፣ ብሔር፣ … [Read more...] about ኦባንግ ለሃይለማርያም በግል ደብዳቤ ላኩ!
ሶስት የህወሓት ሰላዮች ከዱ
ሶስት የብሔራዊ ስለላና የደህንነት ሰራተኞች አገር ለቀው መኮብላቸው ታወቀ። የኮበለሉት የህወሓት/ኢህአዴግ ሰዎች ስደት በጠየቁበት አንድ የአውሮፓ አገር አስቸኳይ ከለላ ማግኘታቸውም ታውቋል። በቅርቡ አገር እየለቀቁ ከሚኮበልሉት የህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ሰራተኞች መካከል የደኅንነት ሰራተኞች እንደሚገኙበት ያመለከተው የጎልጉል የአውሮፓ ሪፖርተር፤ ድርጊቱ አስቀድመው ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን አስደንግጧል። በህወሓትና አቶ መለስ በሾሙዋቸው በሻዕቢያ ሰዎች የበላይነት የሚመራውን የስለላ ተቋም ሲያገለግሉ የነበሩትና አሁን የኮበለሉት ሶስት የደህንነት ሰዎችን ስም ዝርዝር ለጊዜው ከመዘርዘር በመቆጠብ መረጃውን ለጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ የሰጡት ከሰዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት አብረዋቸው የሚኖሩ ስደተኞች ናቸው። ሪፖርተራችን ባጠናከረው መረጃ ሶስቱ የስለላ ሰራተኞች በመረጃ ትንተና ዲቪዥን … [Read more...] about ሶስት የህወሓት ሰላዮች ከዱ