ኤርሚያስ ለገሠ ... ዶ/ር ዐቢይ ላይ ድብቅ የ3 ሠዓት ቪዲዮ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ብዙዎች ለዶ/ር ዐቢይ የወገብ ቅማል ሆነባቸው እያሉ ሲጠይቁ … ገሚሱ ሲያሞግሱ፣ ገሚሱ ሲወቅሱ አየሁና እኔም የማውቀውን እውነት ላካፍላችሁ ወደድሁ። በነገራችሁ ላይ ዶ/ር ዐቢይ በቪዲዮ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው (ብላክ ሜል) ሲደረጉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ በመሆ ጉዳዩን በጥልቀት ለመርመሬ ምክንያት ሆኖኛል። ከዛሬ ዓመት በፊት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ለመወዳደር ዶ/ር ዐቢይ በእጩነት በቀረቡ ጊዜ የቀድሞው የደህንነቱ ሹም ጌታቸው አሰፋም ዶ/ር ዐቢይ ላይ በድብቅ የተቀረጸ የድምጽና የምስል ማስረጃ አለኝ በማለት ዶክተሩን በማስፈራራት ቀዳሚው ሰው ሲሆን አሁን ደግሞ ዓመቱን ጠብቆ ኤርሚያስ ይሄን የቪዲዮ ጌም ይዞ ብቅ ብሏል። ሚስጥር በተወሰነ መልኩም ስለማውቅ እና የሀገሪቱን ፖለቲካ በንቃት ስለምከታተል … [Read more...] about የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ
Left Column
“መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረቱን ቀጥሏል” – ኮሚሽኑ
በደንቢዶሎ ከወር በፊት የታገቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለአዲስ አድማስ የገለፀው የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን፤ መንግስት የተማሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ በማይጥል መንገድ ከእገታ የማስለቀቁን ተግባር እንዲያከናውን ጠይቋል። “የተማሪዎቹ እገታ ጉዳይ በዋነኛነት የደህንነት አካሉ ኃላፊነት ነው” ያሉት የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የመንግስት የፀጥታ ሃይል ልጆቹን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ከእገታው ማስለቀቅ መቻል አለበት ብለዋል። ኮሚሽኑ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ መንግስትም ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት ሚስጥራዊነትን የጠበቀ በመሆኑ ብዙ ጉዳይ ይፋ እንደማይደረግ ጠቁመዋል። በዚህ የማስለቀቅ ጥረት እስካሁን የተገኘ ውጤት አለመኖሩን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ … [Read more...] about “መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረቱን ቀጥሏል” – ኮሚሽኑ
ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አንዳንድ የውጭ አገር ዜግነት ከነበራቸውና በዶ/ር ዓቢይ ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ዜጋ ባለመሆናቸው ያጋጠማቸውን አስመልክቼ አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች አሳትሜ ነበር፡፡ ዛሬም ጥያቄው ወቅታዊ የሆነና ከሕግ አንጻር ትንታኔና ገለጻ እንደሚያስፈልገው ስለተረዳሁ በፊተኛው ጽሁፌ ላይ ተመርኩዤ ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ወሰንኩ፡፡ ዓላማዬም ዜግነትን የመሰለ ለማንኛውም ሰብዓዊ መብት ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ በቀላሉ እንዳናይና ይህንን በሕይወታችን ወሳኝ የሆነውን “ዜግነትን የመቀየር” እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከሕግ አንጻር ማድረግ ያለብንና መከተል ያለብንን ሂደት ችግሩ ላጋጠማቸውና ለወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሕጋዊ ምክር ለመስጠት ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
“እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
ታዬ ደንደኣ እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው። የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረግክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረግክ። ራስህ የሰራኸውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች። ለበርካታ ዓመታት በድራማ ከኦሮሞው ላይ ገንዘብ ሰበሰብህ። አሁን ግን ያን ጊዜ አልፏል፤ ድራማ አዘጋጅቶ የኦሮሞን ድጋፍ መጠየቅ ቀርቷል። ህዝቡ ያንተን አጀንዳ አውቋል። ሀበሻና ሚኒሊክ የአንተ ገበያ ናቸው። የኦሮሞ ድጋፍ ሲቀዘቅዝ ጠዋት ተነስተህ ሀበሻ እና ሚኒሊክ ብለህ ስድብ በመልቀቅ ገንዘብ ትሰበስባለህ። በዚህ መልክ የራስን ብሄር ታልባለህ። … [Read more...] about “እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ፈላስፋ ፍለጋ
ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት የተሰጠ ምላሽ ስለ ፈላስፋው ዘረ-ያዕቆብ ሙህራንና ጻህፍት በሁለት ተከፍለው ኢትዮጵያዊ ነው፣ ኢትዮጵያዊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። ኢትዮጵያዊ ነው ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ አብርሃም ደሞዝ፣ የኔታ አለማየሁ ሞገስ፣ ፈንታሁን ጥሩነህ፣ ብሩህ አለምነህ ይጠቀሳሉ። ኢትዮጵያዊ አይደለም ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ኮንቲ ሮሲኒ፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ ፍስሐ ታደሰ፣ ሰሎሞን አበበ ቸኮል፣ ካሳሁን አለሙ፣ ታሪኩ ውብነህ ይገኙበታል። ሁለቱም ቡድኖች የሚያሳምኑም የማያሳምኑም ሃሳቦችን ይሰነዝራሉ። ፈላስፋው ዘርዓ ያዕቆብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ከሚሉት ውስጥ ጥልቅ የሆነው እና የሌሎችን … [Read more...] about የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ፈላስፋ ፍለጋ
“ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት ላለመቅረብ ወስኛለሁ!…”
(ኤርሚያስ አመልጋ - ከቂሊንጦ) ድፍን አንድ አመት!... በህግ ሊያስጠይቀኝ የሚችል ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ባልፈጸምኩበት እና ለክስ የሚያበቃ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ለእስር ከተዳረግኩና ፍትህ አገኝ ብዬ ፍርድ ቤት መመላለስ ከጀመርኩ እነሆ ድፍን አንድ አመት ሞላኝ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤት በአንድ ሳምባ በሚተነፍሱበት ስርዓት እና አገር ላይ፣ ገለልተኛ ፍርድ እና ሚዛናዊ ፍትህ ማግኘት እንደማይቻል በአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታዬ ያረጋገጥኩት ሃቅ ነው!!! ከዚህ በኋላ ፍትህ አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ራስን ማጃጃል አንደሆነ ተገልጾልኛል፤ አሁን ከስርዓቱ ፍትህ የምጠብቅበት ሳይሆን በእኔ ከደረሰውና ዙሪያዬን ከማየው ተነስቼ የአገራችንን የፍትህ ስርዓት ነውረኛ ባህሪ ለህዝብ የምገልጽበት ወቅት ነው፡፡ “መርምረን … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት ላለመቅረብ ወስኛለሁ!…”
በአዜብ አስናቀ መከሰስ የትህነጎችና የዲጂታል ወያኔዎች መከፋት
የአዜብ አስናቀና የሙሉ ወ/ገብርኤል ክስ ትህነጎችን አበሳጭቷል፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ ባወጣው መረጃ መሠረት “የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ” ተመስርቶባቸዋል። በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበት 123,189 ሄክታር ስፋት የሪዘርቬየር ክሊሪንግና ባዮማስ ዝግጅት ስራ ደኖችን የመመንጠር፣ የማጽዳትና ከአካባቢው (ከግድቡ አርቆ) ወደ ተዘጋጀለት ቦታ የማጓጓዝ ሥራን ለመስራት ከኢፌዴሪ ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በብር 5,158,611,599.03 (አምስት ቢሊዮን … [Read more...] about በአዜብ አስናቀ መከሰስ የትህነጎችና የዲጂታል ወያኔዎች መከፋት
Jawar Mohammed is the Al-Baghdadi of Addis Not an Oromo Activist!
Political/Social activists fight against injustice, suppression, and inequality and in the process, they give their lives to make life a little better for millions of others. Two world-famous activists are Martin Luthor King and Nelson Mandela. While the former gave his life fighting for equality for African Americans in the USA, the latter spent twenty years of his life in prison fighting Apartheid. While activists may naturally belong to one religious group, they never encourage beheadings … [Read more...] about Jawar Mohammed is the Al-Baghdadi of Addis Not an Oromo Activist!
እንኳን ደስ ያለህ!
(ለመቶኛው የኖቤል የሰላም ሎሬት ለ ዶ/ር ዐብይ አህመድ) የሰው ዘር የምንጭ ህይወት - የዘመናት ታሪክ እናት፣ የነጻነት ቀንዲል ብርሃን - ያለም ማማ የእግዚአብሔር ቤት፤ የመለኮት ምስጢራቱ - ቅድስት አገር ኢትዮጵያ፣ መከራዋን አሸንፋ - ባለም ታየች ሃሌሉያ! ... ከበሻሻ መደብ - አልጋ የተነሳው ብላቴና፣ ቀጭን መንገድ በድክ ድክ - ውጣ-ውረድ.. አለፈና፣ በሰንበሌጥ ተመስሎ - ጎርፉን አልፎ ለጥ ብሎ፣ አሳር፣ ችግር፣ ሞትን ከድቶ - በተዐምር ህይወት ዘርቶ፣ ካለም ጫፍ ላይ በድል ታየ - የክብር አክሊል ወርቁን ደፍቶ። ያገር አድባር ግዙፍ ዋርካ፣ ስኬት ተስፋው እሚለካ፣ የይቻላል ትምህርት ቤት - ለትውልዱ አርአያ፣ ክብር ኩራት ለናት አገር ለእምዬ ለኢትዮጵያ! … [Read more...] about እንኳን ደስ ያለህ!
“ሽልማቱን የምቀበለው በአጋሬና የሰላም ጓድ በኾኑት ፕሬዚደንት ኢሣያስ አፈወርቂ ስም ነው” የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ አወደሱ። «ይኽን ሽልማት የምቀበለው በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስም ነው። በተለይ ደግሞ ለሰላም ሲሉ ከፍተኛውን መስዋእትነት በከፈሉት ስም። በተመሳሳይ ሽልማቱን የምቀበለው በአጋሬና የሰላም ጓድ በኾኑት ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ ስም ነው» ብለዋል። ይኽ ንግግራቸውም ከታዳሚያን ሞቅ ያለጭብጨባ ታጅቧል። የፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ «መልካም ፈቃድ፣ እምነት እና ቁርጠኝነት ለኹለት ዐስርተ-ዓመታት በሃገሮቻችን መካከል የዘለቀው መቆራረጥ እንዲያበቃ ወሳኝ ነበር።» በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጦርነቱ ሲከፈት ወጣት እንደነበሩ የተናገሩት ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ፦ በጦርነት አውድማ «ወንድም ወንድሙን … [Read more...] about “ሽልማቱን የምቀበለው በአጋሬና የሰላም ጓድ በኾኑት ፕሬዚደንት ኢሣያስ አፈወርቂ ስም ነው” የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ